Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ ድብደባ ነው። '…ኦሮሚያ ቡሌሆራ ያቤሎ አካባቢ ነው። መውሊድ ለምን ታከብራላችሁ? ለምንስ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዛሬ ድብደባ ነው።

"…ኦሮሚያ ቡሌሆራ ያቤሎ አካባቢ ነው። መውሊድ ለምን ታከብራላችሁ? ለምንስ ሱፍይ ሆንናችሁ? እኛ በምናምነው በወሃቢያ መንገድ ኢስልምናን ለምን አትከተሉም? በሚል ጽንፈኛ አመለካከት የተነሣ ዛሬ በመስጊድ ውስጥ ተሰብስበው የመውሊድን በአል በዚህ መልኩ ይፈጽሙ የነበሩ ሲፊዎችን ድብደባ ፈፅመውባቸዋል። ብዙ ሰዎችም መጎዳታቸው ተነግሯል። ወሃቢስቶቹ የሃጂ ኢብራሂም ቱፋ እስላሞች ሱፊዎችን ደማቸውን በመስጊድ ውስጥ አፍሰውታል። ይሄ ትክክል አይደለም። ነውር ነው።

"…95% ሱፊ ባለበት ሀገር በ17 መርፌ አፈላላጊ ኮሚቴ የሚመራ ፅንፈኛ ቡድን ዘመኑ የኦሮሞ ዘመን ነው በማለት እንዲህ አይነት ጋጠወጥ ተግባር መፈጸማቸው በእውነቱ አግባብ አይደለም። አሁን ወሃቢያ መጅሊሱንም ስለተቆጣጠረ፣ ዐቢይም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ፕሮጀክቱ ስለሚረዱት ባንክና ታንክም ፈቅዶላቸው የሌለ ሄጵ እንዲሉ አድርጓቸዋል ነው የሚሉት ሱፊዎቹ።

"…ወሀቢያ ማለት አይደለም ለክርስቲያኑ ለእስላሙ አይመለስም። ሃገራችንን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ የመሳሰሉ ሀገራትን እንዳያወደመው ከወዲሁ ሁሉም ሰው በተጠንቀቅ ሃገሩን ከነዚህ ፀረ ሃይማኖት ስብስቦች ሊጠብቅ ይገባል ነው የሚሉት ሱፊዎቹ።

"…አሁን የሽማግሌ እና የህጻናትን ደም ለምን መውሊድ አከበራችሁ ብሎ በዚህ መልክ ደማቸውን በመስጊድ ውስጥ ማፍሰስ ወንጀል ነው። ቁርዓኑም፣ ሀዲሱም የሚፈቅድ አይመስለኝም። በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከበርን በአል ለምን ይከበራል ብሎ ደም ማፍሰስ ምን የሚሉት ነገር ነው።

"…አያገባህም አትበለኝ ያገባኛል። አይመለከትህም አትበለኝ ይመለከተኛል። ደም እያፈሰስክ እንዴት ዝም እልሃለሁ። ገተት።

"…ደኅና እደሩልኝ።