Get Mystery Box with random crypto!

'…ሃገር ቀጥ አድርጎ የሚመግብ ገበሬ ዛሬ እንዲህ ተስገብግቦ ውኃ በስስት ለምኖ ሲጠጣ ከማየት በላ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ሃገር ቀጥ አድርጎ የሚመግብ ገበሬ ዛሬ እንዲህ ተስገብግቦ ውኃ በስስት ለምኖ ሲጠጣ ከማየት በላይ ምን የሚያስደነግጥ ነገር አለ። መጋቢህ የሆድህ ጌታ እንዲህ ተሰዶ ከተማ ከገባልህ ከተሜ ሜካፑን ትበላው እንደሁ ይታያል። ጤፍንና የጤፍን ዘር አጥፍቶ ኩታገጠም ማሳ ላይ ዐቢይ ዘራሁት የሚለው የበጋ ስንዴም የሚሸጥ ነው ተብሏል። ባይሸጥም እንኳ ከአንድ መንደር ቀለብነት አያልፍም። በየሰፈራችሁ የምታዩዋቸው እንደነዚህ ያሉ ስደተኛ ገበሬዎችን ቁራሽ በመስጠት ጽደቁባቸው። ቢያንስ በወተት አምገው ይበሉ የነበሩ፣ ቅቤ በአናታቸው፣ አንጀታቸውንም ያርሱበት የነበሩ ሰዎች ናቸውና ውኃ እንኳ አጠጣቸው።