Get Mystery Box with random crypto!

'…የምታየው ሶሪያ አይምሰልህ። እዚሁ ኢትዮጵያ ነው። ያውም ኦሮሚያ…!! …ወዳጄ አንተን ከዐማራና | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የምታየው ሶሪያ አይምሰልህ። እዚሁ ኢትዮጵያ ነው። ያውም ኦሮሚያ…!! …ወዳጄ አንተን ከዐማራና ከትግሬ ጋር አናክሰው ስትጠዛጠዝ፣ በክላስተር ስንዴ ዜና ሆድህን ነፋፍተው ቀብትተው በወሬ ቁንጣን እያዛጉህ እነሱ ግን በጓዳቸው መቋዲሾ ወሶሪያ ሆነውልሃል። ይሄ ይሄ በሚዲያ አይዘገብም። ማንም እንዲያየው እንዲሰማውም አይፈለገም። የሰሊጥ አክቲቪስቶችም አይደፍሩትም። እነሱ ወያኔ ብለው በምላሳቸው ላይ የተነቀሱትን ቃል ሲደሰኩሩት ነው የሚውሉት።

"…አቢቹ አራዳው ለሌላው ህዝብ ወያኔ፣ ክላስተር፣ የበጋ ስንዴ፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ፓርክ፣ ኢ መደበኛ ታጣቂ… ወዘተርፈ እያለ ያዝገዋል። ኦሮሚያ ግን ቅልጥ ያለ የከተማ ውስጥ ጦርነት ላይ ናት። ቀውጢ ነው።

"…ነገርየው የከፋ ነው። ከምትሰሙትም ከምታነቡትም በላይ ነው። በወለጋ የወሎ ዐማሮች የሚኖሩበት የነበረ ሙሉ ለሙሉ የፈረሰ፣ የነደደም የከተማ ፎቶም ደርሶኛል። አሁን እነሱ ዐማራውን ሙሉ ለሙሉ ሙልጭ ጥርግም አድርገው ኮሽታም፣ ተቃውሞም ሳይሰማ ከወለጋ እያጸዱት ነው። ለማንኛውም በምሽቱ የመረጃ ቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ አብረን እናያለን፣ እንፈርዳለንም።

"…የሚመጡት ወሴዎቹ ግን የሚምሩት ሰው የለም። የዐማራው መከራ እንዳለ ሆኖ ብልፅግናን ሙሉ በሙሉ ነው የሚያጸዱት። ዐቢይም ጎንደር ዐማቾቹ ጋር፣ ጎጃም የቢዝነስ አጋሮቹ ጋር፣ አርሲ፣ ጅማ፣ ሸዋ ብቻ የክላስተር እርሻ ከመጎብኘት በቀር ብዙ ነገር ከእጁ እየወጣ ነው። ሽመልስ አብዲሳ ወለጋ ከእጁ ወጥቶም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ነው። ። ወይ ፕሬዘዳንት እቴ። ትግራይ ከራያ ጋር እጁ ላይ የለም። ምዕራብ ሸዋም ለኦነግ እንጂ ለብልጽግና እንደወለጋ ኢሉአባቦርም ግብር አቁሟል። ሆያሆዬው ሸገር ብቻ ነው። ሶሪያን በኦሮሚያ ተመልከቷት…!!

"…አሻማ አለ አልነጃሺ…!!