Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 403.82K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 250

2022-10-31 16:15:43
ዜና ዋልድባ ፫

"…ቀደም ባለው በጻፍኩላችሁ ዜና ዋልድባ ላይ በዋልደባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ቤተ ሚናስ ውስጥ በሚኖሩ አበው መነኮሳት ላይ በህወሓት ታጣቂዎች ስለተፈጸመው ግድያ እና ስላወደሙት ንበረት መጻፋችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ የዋልድባ አብረንታንት ከቤተ ሚናስ አንድነት ገዳም የተዘረፉ ንብረቶችን እንደሚከተለው በጥቂቱ እንገልጻለን።

• ዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ በወራሪው ታጣቂ ቡድን የተዘረፉ፦

ሀ፦ከገዳሙ የተዘረፉ፦

1ኛ፦ሰሊጥ
2ኛ፦ተልባ
3ኛ፦ኑግ
4ኛ፦ስኳር
5ኛ፦በርበሬ
6ኛ፦አሞሌ ጨው
7ኛ፦ጥሬ ጨው
8ኛ፦ሶላሮች
9ኛ፦አቡጀዲ ጣቃ
10ኛ፦ የእጅ ባትሪና፣ ባትሪ ድንጋይ እነዚህ ሁሉ ቋርፍ እንጂ እህል ከማይበላበት ከህርመት ቦታ የተዘረፉ ሲሆን፦                    
ሁ፦ከእህል ቤት የተዘረፉ ደግሞ፦

1ኛ፦ ማሽላ
2ኛ፦ ዳጉሳ
3ኛ፦ ጤፍ
4ኛ፦ ሽንብራ
5ኛ፦ በርበሬና ጥሬጨው
6ኛ፦ ባቄላ
7ኛ፦ አቡጀዲ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም።

1ኛ፦ 46 የእርሻ በሬ
2ኛ፦ 19 ላሞች
3ኛ፦ 15 አህዮች
4ኛ፦ 32 ፍየሎችም በወራሪው ኃይል ተዘርፈው ተወስደዋል።

"…ከዚህ በተጨማሪም አባቶች እና እናቶች ከሚኖሩበት ዋልድባ አብረንታንት ቤተ ሚናስ የእርሻ ቦታ ዶንዶሮቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ አድርቃይ የገዳሙ መጋዝን፣ ማይጠብሪ ያለ ወፍጮ ቤት፣ ደለሳ ቆቃ አቡነ አረጋዊ፣ እጣኑ ማርያም፣ ማህርገጽ ጊዮርጊስ፣ እነዚህ የገዳሙ የእርሻ ቦታ ወይም ሞፈር ቤት ሲሆኑ ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች ሙሉ በሙሉ በወራሪው በድን መዘረፉ ተገልጿል።

"…በተሰማው ዜና ኢትዮጵያውያን ማዘናቸውንም የዋልድባ ሰምተዋል። ሰሞኑን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ድምጻቸውን እንዲያሰሟችሁ፣ በዚያውም እንዲባርኩን በሚዲያ ይዣቸው ለመቅረብ እሞክራለሁ።

"…በተረፈ የወደመው ንብረት ሁሉ በእኛው ይተካል።
64.0K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 13:41:23
ዜና ዋልድባ ፪

"…ቀደም ባለው ዜና በዋልደባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ስለተገደሉትና ስለቁስለኞቹ አበው መነኮሳት መጻፋችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ የዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ቤተ ሚናስ የወደሙ ንብረቶች እንደሚከተለው በጥቂቱ እንገልጻለን።   

ሀ፦ የንብ ቀፎ ውድመት፦             

1ኛ፦ ማይስየ ቀፎቤት
2ኛ፦ ላይ አቴና ቀፎቤት
3ኛ፦ ማይኮክ ቀፎቤት
4ኛ፦ ታች ስፍራ በጎይ ሁለት ቤት በአጠቃላይ አምስት መቶ አርባ (540) ቀፎ ንብ እንደያዘ ተቃጥሏል። ሙሉ በሙሉም ወድሟል። ማሩንም ዘርፈውታል ነው የተባለውይሄ የወደመው የንብ እርባታው ነው።

ሁ፦ ለገዳሙ ተከራይቶ ገቢ ያስገኛሉ ተብለው ከተማ ላይ ተሠርተው የነበሩና የወደሙ ቤቶች።

1ኛ፦ አዲዓርቃይ ከተማ አስጋዲት ማርያም ፊት ለፊት የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ 20 ክፍል ያለው ተከራይቶ የነበረ ቤት ተቃጥሎ ወድሟል።

2ኛ፦ አሁንም አደርቃይ ከተማ መናኸሪያ ጀርባ ሁለት ክፍል የሚከራይ ቤት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ተቃጥሏል። 

፫ኛ፦ ቁጥሩ ያልተገለጸ የመነኮሳቶች ቤት፣ ከነመጻሕቶቻቸው መቃጠላቸው ተገልጿል።  

"…ይሄ የወደመ ንብረት ነው። የቀለባቸው እና የእንስታቶቻቸውን ውድመትና ዘረፋ ደግሞ ቆይቼ እጽፍላችኋለሁ። ጠብቁኝ።
66.3K views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 12:29:48
ዜና ዋልድባ…፩

"…ባለፈው አንድ ዓመት ከአራት ወር በተደረገው ጦርነት በዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ  አባቶች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ የገዳሙም፣ የገዳማውያኑም ንብረት ተቃጥሏል፣ ተዘርፏል፣ ወድሟል። ቀጥሎ ገዳማውያኑ የደረሰባቸውን ጉዳቶች በስሱ እንመለከታለን።

• የተገደሉ በሰማእነት ያለፉ አባቶች፦

1ኛ፥ አባ አክሊለ ሰማእት ባህታዊ በፋስ የተገደሉ
2ኛ፥ አባ ገብረ ሚካኤል በጥይት የተገደሉ
3ኛ፥ መናኝ ገብረሥላሴ በጥይት የተገደሉ።
4ኛ፥ መናኝ ገብረማርያም በጥይት የተገደሉ።
5ኛ፥ አባ ገብረሥላሴ ወልደ ሳሙኤል በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ በዋልደባ አብረንታንት ገዳም ውስጥ በህወሓት ታጣቂዎች በጥይትና በፋሰ ተደብድበው በጭካኔ የገደሏቸው ናቸው።

• ክፉኛ የቆሰሉ አባቶች፦ 
                                
1ኛ፥ አባ ኪሮስ በጥይት ተመተው የቆሰሉ
2ኛ፦ ኃይለ ገላውዲዎስ በጥይት የቆሰሉ።
3ኛ፦ አባ ገብረ ህይወት ወ/ሳሙኤል በጥይት የቆሰሉ።
4ኛ፦ መናኝ ዳዊት በብትር በዱላ ተደብድቦ ሽባ የሆነ። 

"…የአባቶቻችን የከበረች በረከታቸው፤ ድል የማትነሣ ረድኤታቸው፤ ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው፤ ከእኛ ጋር ትኹን። አሜን።

• ቆይቼ ስለወደመው ንብረት በዝርዝር አለጥፍላችኋለሁ።
66.6K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 11:44:51
ዋልድባ…!!

"…እንደምን አደራችሁልኝ። ትናንት ድክም ብሎኝ ተኝቼ ዛሬ አርፍጄ ገና አሁን መነሣቴ ነው። በመቀጠል ላለፈው አንድ ዓመት ከአራት ወር በላይ በህወሓት ወራሪ ኃይል ቁጥጥር ስር የነበረው የታላቁ ዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም በቅርቡ ነጻ ከወጣ በኋላ የደረሰበትን ጉዳት፣ በወራሪ ቡድኑ በወረራ ስር በቆየባቸው ወራቶች በተለይ በዋልድባ ገዳም የተገደሉ፣ የቆሰሉ አባቶችን፣ የወደመ ንብረት በአይነት፣ የተዘረፉ፣ የተቃጠሉትን ሁሉ በዝርዝር እንመለከታለን።

#ማስጠንቀቂያ፦

"…ገዳሙ ተጎድቷል፣ አዎ ተጎድቷል። አበው መነኮሳት ተገድለዋል፣ ቆስለዋልም። ከበአታቸው ተገብቶ ተዘርፈዋል። በተለይ የቤተ ሚናስ አባቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል። ነገር ግን ይሄን ተከትሎ ይህ ዜና ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ሰበብ በዋልድባ ጉዳት ስም ምእመናን ላይ ዘረፋ፣ የኪስ አጠባ እንዳይከናወን እሰጋለሁ።

"…እንዲህ ዓይነት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርላቸው አንዳንድ አጭቤ የከተማ አውደልዳይ ቆብ ያጠለቁና፣ ወይባ ቀሚስ የለበሱ አጭበርባሪ መነኮስ መሳይ ማፍያዎች ከገዳሙ ሳይላኩ ተልከናል በማለት በዋልድባ ገዳም ስም በየመንደሩ፣ በየክርስቲያኑ ቤት ሁሉ እየገቡ የኪስ አጠባ እንዳያካሂዱ ልትጠነቀቁ ይገባል።

"…ገዳሙን ለመርዳት መፍትሄው ቀላል ነው። መፍትሄው በሕጋዊ መንገድ በገዳሙ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከፍቶ አገልግሎት በሚሰጠው በገዳሙ ሕጋዊ የባንክ አካውንት ማስገባት ብቻ ነው። መፍትሄው እሱ ነው። የገዳም እርዳታ፣ በተለይ እንደዋልድባ ገዳም ላለ እርዳታው በግለሰቦች እጅ በኩል ማለፍ የለበትም ባይ ነኝ። ይሄ የእኔ ጽኑዕ እምነት ነው።

• ቆይቼ የተገደሉትን እና የቆሰሉትን አባቶች ስም ዝርዝር፣ ስለተቃጠለውና ስለወደመው፣ ስለተዘረፈውም የገዳሙ ሃብት በዝርዝር አስቀምጥላችኋለሁ። ጠብቁኝ።
68.2K viewsedited  08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 22:55:22
ዜና እስር…!!

"…ደህና እደሩ ካልኩ በኋላ የመለሰኝ የእስር ዜና ነው። አንዳንዶች ነጭ ነጯን መስማቱ ባይመቻችሁም እኔ ግን ብሶብኝ ቀጥያለሁ። ብልፅግናዎች በተለይ እኔ ፔጅ ላይ የሚጻፈውን ባታዩት ሁላ ትመርጣላችሁ። እኔ ፔጁን የከፈትኩት ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ ልሆንበት ነው። ነጭነጯን ብቻ።

"…ዛሬ ጠዋት የኦሮሚያ መዝሙር አንዘምርም፣ የኦሮሚያ ባንዲራም አንሰቅልም ያሉና በቂርቆስ ክፍለከተማ የፈለገ ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቃውሞ ተከትሎ የአዳነች አቤቤ መንግሥት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ወደ ትምህርት ቤቱ ፎሊስ በመላክ የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መመህር ጨምሮ ሌሎች መምህራንን ወደ ዘብጥያ ማውረዱ ተሰምቷል።

"…በኦሮሚያ  ባንድራ የተነሳ የትምህርት ቤቱን  ዳሬክተሮችን እንዲሁም 3 መምህራኖችን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በፖሊስ ተይዘው አሁን ያሉበት ዘብጥያ እዚያው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በፖፖላሬ ፖሊስ ጣቢያ ሲሆን ፖሊስ ቃላቸውን ሳይቀበል በጣቢያው እንዲያድሩ እንዳደረጋቸውም ተስምቷል። አሁን ዘብጥያ ወርደው ያሉት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ኤርሚያስ፣ ምክትል ርእሰ መምህር አቶ እስጢፋኖስ፣ አቶ አለሙ እና ሌሎች 3 መምህራኖች በአዳነች አበቤ ትእዛዝ ተይዘው ወደ ዘብጥያ ወርደዋል። ዋናው ክሳቸው ሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን ትእዛዝ ተቀብለው ሲፈጽሙ በዚህ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ምን ብላችሁ ብታስተምሯቸው ነው ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና መዝሙር ጋር እንዲህ የተጣበቁት የሚል ክስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የአዲስ አበባ ህፃናት ከኦህዴድብአዴንኦነግ በለጡ እኮ።

• ኧረ ሰከን በል ኦህዴድ…!!
42.9K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 21:44:11
የተማሪዎች መደፈር እና የሞት ዜና…!!

"…በደብረ ታቦር እና በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ የዐማራ ሴት ታዳጊ ህፃናት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎቹ የፌደራል ፖሊስ አባላት መደፈራቸው ተሰምቷል። በረብሻው ወቅት የሞቱም አሉ። "…ከዱር ቤት ሰሜን አቸፈር ባህርዳር ለፈተና የሄዱ አምስት ህፃናት ተማሪዎች በንዘልማ ካምፓስ አምስት ታዳጊ የገጠር ልጆች በተለይ ባህርዳር የተደፈሩትን ዩኒቨርስቲው እያከመ፣ ኪኒን እና መርፌ የሰጠ ለፈተና ያቀርባቸው እንደነበርም ተሰምቷል።

"…በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ፖሊሶቹ በርካታ ተማሪዎችን የደፈሩ ሲሆን በተለይ የብጥብጡ መነሣት ለፖሊሶቹ ምቹ የመድፈር ሁኔታን እንደፈጠረላቸውም ነው እማኞቹ የሚናገሩት። የደብረታቦሮቹ የደቡብ ጎንደር ተማሪዎች አሁን ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን በባህርዳር ዘንዘልማ ካምፓስ ታፍነው የተደፈሩት ታዳጊዎች እስከአሁን ወደ ቤተሰቦች ያለመሸኘታቸው ታውቋል። "…ይሄ ደግሞ ግፍም፣ ኃጢአትም፣ ነውርም፣ ጭካኔም፣ ወንጀልም ነው። ችግሩ ተደፋሪው ተቆርቋሪ አልባው ዐማራ መሆኑ ነው።

"…በአዲስ አበባም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲ  የሁለት የዳግማዊ ሚኒሊክ ትምህርት ቤት ሴት ተማሪዎች መገደልም እየተነገረ ነው። እየቆየ ሲመጣ የሚወጡ አስደንጋጭ ዜናዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ሚንስትር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ ላለው ፈተና ፌደራል ፖሊሶቹ ህፃናትን እንዳይደፍሩ የሆነ ነገር ቢያደርግ መልካም ነው እላለሁ።

"…ደኅና እደሩ…!!
52.2K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 20:18:22
ኦነግ ሽሜ በኢሉአባቦር…!!

"…ኦነግ ሽሜ በደሌ ከተማ አፍንጫ ስር ከበደሌ በቅርብ ርቀት ላይ ያለችዋን ጨዋቃ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ሲዋጋ መዋሉ ተነግሯል። የኦሮሚያ ፖሊስ ልዩ ኃይሎች ለመዋጋት ቢሄዱም እንደድሮው ፖሊስ ሲያይ የሚሸሽ ኦነግ ሽሜ አይደለም የገጠማቸው። እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ ከባድ ኃይል ነው የገጠማቸው። ክላሽ ይዞ የሄደ ፖሊስ ነፍስ ይማር።

"…በዛሬው የጨዋቃ ላይ ውጊያ እስከአሁን ብዙ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት መገደላቸው፣ መቁሰልና መማረካቸውም የበደሌ የወሬ ምንጮቼ ነግረውኛል። ጨዋቃ ላይ እስከአሁን የሞተው በቁጥር አልታወቀም። የጨዋቃ ሕዝብ በአብዛኛው ተሰዶ በደሌ መጥቷል። ሊዋጋ ከሄደው የኦሮሚያ ፖሊስ መካከል እስከአሁን ቆስሎ እንኳ የተመለሰ አላየንም ነው የሚባለው። መኪናም፣ መሳሪያም ለኦነግ በምርኮ ስም ገብቶለታል። 

"…ዛሬ ረቡዕ ነው። የበደሌ ነጋዴዎች 77 የምትባል ወረዳ ረቡዕ ረቡዕ ሂደው ይነግዳሉ። 77 ለበደሌ በጣም ቅርብ ስፍራ ያለች የገጠር ከተማ ናት። ዛሬም ነጋዴዎች ለሥራ ሄደው ነበር። እናም ጠዋት ላይ ኦነግ ሽሜ ወደ ከተማዋ በመግባቱ ነጋዴዎቹ አምልጠው ወጥተዋል። በወለጋም ውጊያው ቀጥሏል።

"…በሰሜን ትግራይ በምዕራቡም በኩል ወደ ትግራይ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር እየገፋ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን በራያ በኩል ከትግራይም ከጥምር ጦሩም ብዛት ያለው ተዋጊና ከባድ የጦር መሣሪያዎችም መሰለፋቸው ተሰምቷል። ህወሓት ወደ አፋርም የተዋጊ ኃይል ማስጠጋቷም ተነግሯል። የህወሓትን መዳከም ያየችው አማሪካም ሩሲያ በአስመራ በኩል ሳትቀድመኝ በአውሮጳ ኅብረት በኩል ወልቃይት ላይ ልስፈር እያለች ነው። በሁለት ሀያላንና በ7 ዓረብ ሃገራት የሚባል ንግርትም አለ። ከኦሮሚያ በኩል ዝም ነው። ብአዴን ልጆቹን አስሮ ይሸልላል።

• ከበደሌ ጅማ ስንት ኪሎሜትር ይሆን…?
59.9K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 18:42:14
ደግሞ መጣሁ…!!

"…በፍኖተ ጽድቅ" ጉዳይ ብዙ ሰው ምርትነሽ ላይ ብቻ አፉን ሲከፍት አያለሁ። እኔ ግን ምርትነሽ ለምን በዚያ አዳራሽ ተገኘች የሚል ጥያቄ አላነሣሁም። አልጠይቃትምም። ጠሪው እኮ ሃብታም ነው። በዘመነ ህወሓት ጉራጌ፣ አሁን ደግሞ ኦሮሞ ነኝ የሚል ዲታ፣ ሃብታም እኮ ነው። ጠሪው እኮ ፋብሪካ ያለው ሰው ነው። የሮዳስ ቀለም ፋብሪካና የሮቶ ፋብሪካ ባለቤት። እነ በጋሻውና እነአሰግድ የጋጡት፣ መጨረሻ ላይ አኞው ሲቀር የአቡበከር ልጅ ከመተሃራ መጥቶ የተረከበው ባለሃብት ነው። በእኛ ቤት ደግሞ ለባለሃብት ያለን አክብሮት፣ ፍቅርና አድናቆት የታወቀ ነው። ደሀን ይጭነቀው እንጂ ለሃብታም ቀን በቀን ጠበል ቢረጭለትስ? ምንሺጊር?

"…እደግመዋለሁ እኔ ምርቴን የተቸሁት ለምን ወደ አዳራሹ ሄደች ብዬ አይደለም። አቡነ ሳዊሮስ እዚያ ተገኝተው እየባረኩ፣ አቡነ ዮሴፍ፣ አቡነ መቃርዮስ እዚያ ተገኝተው እየባረኩ፣ መምህር ጳውሎስ፣ መምህር ብርሃኑ አድማስ ከማኅበረ ቅዱሳን፣ ተስፋዬ ሞሲሳ፣ ዘማሪ ቴዎድሮስ፣ ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ፣ ዘማሪ በሱፍቃድ፣ ዘማሪ ልዑልሰገድ ቋንቋዬነሽ፣ ዘማሪት አዜብ ከበደ፣ እነ ዘማሪ ማንትስዮና እነ መምህር ቅብጥርስዮ በአዳራሹ ተገኝተው እሷ ለምን ተገኘች ብሎ ሄጵ ማለት ግፍም፣ ነውርም፣ ወንጀልም፣ ኃጢአትም ነው። እኔ ምርቴን ያልኳት የቆዩ እና የተከበሩ መዝሙራትን እንደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቆማምጠሽ፣ ሰባብረሽ አትጣዪ ነው። ቢያንስ የቀደሙ መዝሙራት እንኳ እንደተከበሩ ለትውልድ ይተላለፉልን ብዬ ነው የተማጸንኳት።

• አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይል ነበር አጎቴ ሌኒን። ሌሎቹን መውቀሱ ቢከብዳችሁ እንኳ ምርትነሽን ብቻ መርጦ መቀጥቀጡ "ኢዴየቢራል"። ሼም ነው። ምርትነሽ ቢያንስ ልምድ አላት ጠፍቶ የመመለስ፣ ይቅርታም የመጠየቅ። በቃ ተፋቷት።

"…ሂኢ… !!
63.2K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 18:40:48
"…ለምን ምርትነሽ ላይ ብቻ…? ሃኣ…?
58.9K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 09:48:05
የዘመነ ካሴ አጭር ደብዳቤ…!!

                                          ቀን፦ 01-02-2015
   ለዘመዴ…!     

"…እንዴት ሰነበትህ? እኔ በጣም ደህና ነኝ። በፍጥነት ልጻፍልህ:-

"…የውልህ ግብግቡ ቀጥሏል። የዛሬውን የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ሰምተህ ይሆናል። ልክ የፍ/ቤት ውሏችን አልቆ መኪናው ሲንቀሳቀስ መኪናውን አጥፈው የወረዳው ፍ/ቤት በር ላይ አቁመው "ውረድ" አሉኝ። "ልክ እግሬ ከመኪናው ወርዶ መሬት እንደነካ ግብግብ እጀምራለሁ። ወደ አንዳችሁ ጉሮሮ ነው የምመጣው። ይህ የነ ኮማንደር ዋናው እና የነ ኮማንደር ጥበበ ችሎት ነው።.........." አልኋቸው። ኮማንደር ዋናው መጥቶ "ውረድ" ሲለኝ "ያንተ ችሎት ላይ አታቆመኝም ወ.ዘ.ተ" አልሁት። ከ40 ደቂቃ በላይ ተፋጠን ቆምን፤ በመጨረሻ ወደ ወህኒ ቤት ተመለስሁ።

"…አሁን ከመሸ ደግሞ ወረዳ ፍ/ቤቱ ለአርብ ሦስት ሰዓት እንድቀርብ መጥሪያ ልኳል። በተዓምር እዚህ የቅጥፈት የነዋናው ችሎት እንደማልቀርብ ለማረሚያ ቤቱ ኮማንደሮችም አሁን ነግሬያቸዋለሁ። ለሚፈጠረው ቀውስ ሓላፊነት እንደማልወስድም ጭምር።.......... ሌላ ጊዜ ሰፋ አድርጌ እጽፍልሃለሁ
                                 ወንድምህ
                                 ዘመነ ካሴ
                 ከባህርዳር ወህኒ ቤት

"…ደብዳቤው ደርሶኛል። ጠበቃ እና ታዛቢ በሌለበት ለብቻው ወስደው ያደረሱበትን ወከባ ህዝቡ እንዲያውቀው ነው አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ለእኔ የጻፈልኝ። ከበረሀ ጀምሮ የሚጽፍልኝ የእጅ ጽሑፉ ነው።

"…ከምር ኮማንደር ጥበበ እና ኮማንደር ዋናው እነማን ናቸው? ፎቶአቸው ያላችሁ ወዲህ በሉልኝ እስኪ?
17.9K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ