Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ዋልድባ ፫ '…ቀደም ባለው በጻፍኩላችሁ ዜና ዋልድባ ላይ በዋልደባ አብረንታንት አንድነት ገዳ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዜና ዋልድባ ፫

"…ቀደም ባለው በጻፍኩላችሁ ዜና ዋልድባ ላይ በዋልደባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ቤተ ሚናስ ውስጥ በሚኖሩ አበው መነኮሳት ላይ በህወሓት ታጣቂዎች ስለተፈጸመው ግድያ እና ስላወደሙት ንበረት መጻፋችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ የዋልድባ አብረንታንት ከቤተ ሚናስ አንድነት ገዳም የተዘረፉ ንብረቶችን እንደሚከተለው በጥቂቱ እንገልጻለን።

• ዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ በወራሪው ታጣቂ ቡድን የተዘረፉ፦

ሀ፦ከገዳሙ የተዘረፉ፦

1ኛ፦ሰሊጥ
2ኛ፦ተልባ
3ኛ፦ኑግ
4ኛ፦ስኳር
5ኛ፦በርበሬ
6ኛ፦አሞሌ ጨው
7ኛ፦ጥሬ ጨው
8ኛ፦ሶላሮች
9ኛ፦አቡጀዲ ጣቃ
10ኛ፦ የእጅ ባትሪና፣ ባትሪ ድንጋይ እነዚህ ሁሉ ቋርፍ እንጂ እህል ከማይበላበት ከህርመት ቦታ የተዘረፉ ሲሆን፦                    
ሁ፦ከእህል ቤት የተዘረፉ ደግሞ፦

1ኛ፦ ማሽላ
2ኛ፦ ዳጉሳ
3ኛ፦ ጤፍ
4ኛ፦ ሽንብራ
5ኛ፦ በርበሬና ጥሬጨው
6ኛ፦ ባቄላ
7ኛ፦ አቡጀዲ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም።

1ኛ፦ 46 የእርሻ በሬ
2ኛ፦ 19 ላሞች
3ኛ፦ 15 አህዮች
4ኛ፦ 32 ፍየሎችም በወራሪው ኃይል ተዘርፈው ተወስደዋል።

"…ከዚህ በተጨማሪም አባቶች እና እናቶች ከሚኖሩበት ዋልድባ አብረንታንት ቤተ ሚናስ የእርሻ ቦታ ዶንዶሮቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ አድርቃይ የገዳሙ መጋዝን፣ ማይጠብሪ ያለ ወፍጮ ቤት፣ ደለሳ ቆቃ አቡነ አረጋዊ፣ እጣኑ ማርያም፣ ማህርገጽ ጊዮርጊስ፣ እነዚህ የገዳሙ የእርሻ ቦታ ወይም ሞፈር ቤት ሲሆኑ ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች ሙሉ በሙሉ በወራሪው በድን መዘረፉ ተገልጿል።

"…በተሰማው ዜና ኢትዮጵያውያን ማዘናቸውንም የዋልድባ ሰምተዋል። ሰሞኑን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ድምጻቸውን እንዲያሰሟችሁ፣ በዚያውም እንዲባርኩን በሚዲያ ይዣቸው ለመቅረብ እሞክራለሁ።

"…በተረፈ የወደመው ንብረት ሁሉ በእኛው ይተካል።