Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ዋልድባ ፪ '…ቀደም ባለው ዜና በዋልደባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ስለተገደሉትና ስለቁስለ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዜና ዋልድባ ፪

"…ቀደም ባለው ዜና በዋልደባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ስለተገደሉትና ስለቁስለኞቹ አበው መነኮሳት መጻፋችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ የዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ቤተ ሚናስ የወደሙ ንብረቶች እንደሚከተለው በጥቂቱ እንገልጻለን።   

ሀ፦ የንብ ቀፎ ውድመት፦             

1ኛ፦ ማይስየ ቀፎቤት
2ኛ፦ ላይ አቴና ቀፎቤት
3ኛ፦ ማይኮክ ቀፎቤት
4ኛ፦ ታች ስፍራ በጎይ ሁለት ቤት በአጠቃላይ አምስት መቶ አርባ (540) ቀፎ ንብ እንደያዘ ተቃጥሏል። ሙሉ በሙሉም ወድሟል። ማሩንም ዘርፈውታል ነው የተባለውይሄ የወደመው የንብ እርባታው ነው።

ሁ፦ ለገዳሙ ተከራይቶ ገቢ ያስገኛሉ ተብለው ከተማ ላይ ተሠርተው የነበሩና የወደሙ ቤቶች።

1ኛ፦ አዲዓርቃይ ከተማ አስጋዲት ማርያም ፊት ለፊት የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ 20 ክፍል ያለው ተከራይቶ የነበረ ቤት ተቃጥሎ ወድሟል።

2ኛ፦ አሁንም አደርቃይ ከተማ መናኸሪያ ጀርባ ሁለት ክፍል የሚከራይ ቤት ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ተቃጥሏል። 

፫ኛ፦ ቁጥሩ ያልተገለጸ የመነኮሳቶች ቤት፣ ከነመጻሕቶቻቸው መቃጠላቸው ተገልጿል።  

"…ይሄ የወደመ ንብረት ነው። የቀለባቸው እና የእንስታቶቻቸውን ውድመትና ዘረፋ ደግሞ ቆይቼ እጽፍላችኋለሁ። ጠብቁኝ።