Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ዋልድባ…፩ '…ባለፈው አንድ ዓመት ከአራት ወር በተደረገው ጦርነት በዋልድባ አብረንታንት አ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዜና ዋልድባ…፩

"…ባለፈው አንድ ዓመት ከአራት ወር በተደረገው ጦርነት በዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ  አባቶች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ የገዳሙም፣ የገዳማውያኑም ንብረት ተቃጥሏል፣ ተዘርፏል፣ ወድሟል። ቀጥሎ ገዳማውያኑ የደረሰባቸውን ጉዳቶች በስሱ እንመለከታለን።

• የተገደሉ በሰማእነት ያለፉ አባቶች፦

1ኛ፥ አባ አክሊለ ሰማእት ባህታዊ በፋስ የተገደሉ
2ኛ፥ አባ ገብረ ሚካኤል በጥይት የተገደሉ
3ኛ፥ መናኝ ገብረሥላሴ በጥይት የተገደሉ።
4ኛ፥ መናኝ ገብረማርያም በጥይት የተገደሉ።
5ኛ፥ አባ ገብረሥላሴ ወልደ ሳሙኤል በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ በዋልደባ አብረንታንት ገዳም ውስጥ በህወሓት ታጣቂዎች በጥይትና በፋሰ ተደብድበው በጭካኔ የገደሏቸው ናቸው።

• ክፉኛ የቆሰሉ አባቶች፦ 
                                
1ኛ፥ አባ ኪሮስ በጥይት ተመተው የቆሰሉ
2ኛ፦ ኃይለ ገላውዲዎስ በጥይት የቆሰሉ።
3ኛ፦ አባ ገብረ ህይወት ወ/ሳሙኤል በጥይት የቆሰሉ።
4ኛ፦ መናኝ ዳዊት በብትር በዱላ ተደብድቦ ሽባ የሆነ። 

"…የአባቶቻችን የከበረች በረከታቸው፤ ድል የማትነሣ ረድኤታቸው፤ ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው፤ ከእኛ ጋር ትኹን። አሜን።

• ቆይቼ ስለወደመው ንብረት በዝርዝር አለጥፍላችኋለሁ።