Get Mystery Box with random crypto!

ዋልድባ…!! '…እንደምን አደራችሁልኝ። ትናንት ድክም ብሎኝ ተኝቼ ዛሬ አርፍጄ ገና አሁን መነሣ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ዋልድባ…!!

"…እንደምን አደራችሁልኝ። ትናንት ድክም ብሎኝ ተኝቼ ዛሬ አርፍጄ ገና አሁን መነሣቴ ነው። በመቀጠል ላለፈው አንድ ዓመት ከአራት ወር በላይ በህወሓት ወራሪ ኃይል ቁጥጥር ስር የነበረው የታላቁ ዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም በቅርቡ ነጻ ከወጣ በኋላ የደረሰበትን ጉዳት፣ በወራሪ ቡድኑ በወረራ ስር በቆየባቸው ወራቶች በተለይ በዋልድባ ገዳም የተገደሉ፣ የቆሰሉ አባቶችን፣ የወደመ ንብረት በአይነት፣ የተዘረፉ፣ የተቃጠሉትን ሁሉ በዝርዝር እንመለከታለን።

#ማስጠንቀቂያ፦

"…ገዳሙ ተጎድቷል፣ አዎ ተጎድቷል። አበው መነኮሳት ተገድለዋል፣ ቆስለዋልም። ከበአታቸው ተገብቶ ተዘርፈዋል። በተለይ የቤተ ሚናስ አባቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል። ነገር ግን ይሄን ተከትሎ ይህ ዜና ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ሰበብ በዋልድባ ጉዳት ስም ምእመናን ላይ ዘረፋ፣ የኪስ አጠባ እንዳይከናወን እሰጋለሁ።

"…እንዲህ ዓይነት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርላቸው አንዳንድ አጭቤ የከተማ አውደልዳይ ቆብ ያጠለቁና፣ ወይባ ቀሚስ የለበሱ አጭበርባሪ መነኮስ መሳይ ማፍያዎች ከገዳሙ ሳይላኩ ተልከናል በማለት በዋልድባ ገዳም ስም በየመንደሩ፣ በየክርስቲያኑ ቤት ሁሉ እየገቡ የኪስ አጠባ እንዳያካሂዱ ልትጠነቀቁ ይገባል።

"…ገዳሙን ለመርዳት መፍትሄው ቀላል ነው። መፍትሄው በሕጋዊ መንገድ በገዳሙ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከፍቶ አገልግሎት በሚሰጠው በገዳሙ ሕጋዊ የባንክ አካውንት ማስገባት ብቻ ነው። መፍትሄው እሱ ነው። የገዳም እርዳታ፣ በተለይ እንደዋልድባ ገዳም ላለ እርዳታው በግለሰቦች እጅ በኩል ማለፍ የለበትም ባይ ነኝ። ይሄ የእኔ ጽኑዕ እምነት ነው።

• ቆይቼ የተገደሉትን እና የቆሰሉትን አባቶች ስም ዝርዝር፣ ስለተቃጠለውና ስለወደመው፣ ስለተዘረፈውም የገዳሙ ሃብት በዝርዝር አስቀምጥላችኋለሁ። ጠብቁኝ።