Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 248

2022-11-06 14:54:29
ሰበር ዜና…!!

"…ኦነጎቹ በአሁን ሰዓት ከነቀምቴ ከተማ የዓመት ቀለባቸውን ከባንኮችና ከመንግሥታዊ ተቋማት የሚዘረፈውን ሁሉ ዘርፈው ወደ ጫካቸው እየተመለሱ መሆኑ ተነግሯል።

"…የቴሌዋ ፍርዬ እስከአሁን ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የስልክም፣ የኢንተርኔት አገልግሎትም ባለማቋረጥ ኦነጎቹ በመገናኛ እጦት እንዳይቸገሩ ከፍተኛውን ትብብር እንዳደረገችላቸው ተሰምቷል። ብራቮ ፍርዬ። መከላከያው እንዲያፈገፍግ፣ ልዩ ኃይሉ እንዲሸሽ የተደረገው ትናንት ነው ተብሏል። ቁማሩ ያልተነገራቸው እና ያልገባቸው ምስኪን ወታደሮችን ተረፍርፈዋል ነው የተባለው።

"…አሁን ኦነግ ከነቀምቴ ከተማ የመንግሥት የሆኑትን በብልፅግና የተሾሙ ሹማምንት ባለሥልጣናትን የሚገድላቸውን ገድሎ፣ ሌሎቹንም አፍኖ እየተመለሰ ነውም ተብሏል። እስከ አሁን ድረስ እንደበፊቱ ኦነጉ የዐማራ የሆነ ንብረትም ሆነ ህይወት እንዳልነኩም ተነግሯል። ነቀምትን ጥለው ይውጡ እንጂ ዙሪያ ገባው በእነርሱ እጅ መሆኑም ተሰምቷል።

"…ታዲያ ይሄ ሁላ ሲሆን አንድም አክቲቪስትም ሆነ ጋዜጠኛ ከኦህዴድ መንግሥት ጋር ላለመጣላት ሲል በጉዳዩ ላይ አለመተንፈሱ ነው የሚታየው። የሚገርመው ነገር ሽመልስ አብዲሳ እስከአሁን የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ነው። ዐቢይ አህመድም ስብሰባ ለመሳተፍ፣ በዚያውም ሪፖርት ለማቅረብ ወደ ግብፅ ነክቶታል። አዲስ አበቤ ከነገጀምሮ በክፍያ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀውን የህጻናት መዝናኛ ጊዜው ሳያልፍበት ለመጠቀም ሲል በባዶ ሆዱ ልጆቹን እያዝና ይገኛል። በሚሊንየም አዳራሽ አዲስ አበባ በብራዚል ተሸልማለች ተብሎ ድግስ ላይ ናት። ቸበርቻቻ።

• በኦሮሚያ ያለህ ዐማራ ግን በተለይ በወለጋ የምትኖሩ ዐማሮች መተኛት ሲያምራችሁ እንኳ በአንድ ዓይናችሁ ብቻ ተኙ። ሰምታችኋል።

• ቆይቼ እመለሰላሁ…!
50.8K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 14:02:34 መረጃ ነቀምት
እንዲህም ሆነ....

"…ሰሞኑን ኦነግ ሸኔ ከመንግሥት ተብዬው ወታደር ይልቅ የዐማራ ታጣቂ አላፈናፍን ብሎ ያስቸግረዋል። ኦነጎቹም ወደ ዐማሮቹ ሽማግሌ ይልካሉ። "…ዐማሮች አሳልፉን። እናንተን አንነካም። አሁን ነቅተናል። አስከዛሬም አጥፍተናል። አሁን ግን መንቃት እና መግባባት አለብን። እያፋጀን ያለው የፒፒ መንግሥት ስለሆነ እናንተም ኦሮሞን አትንኩ እኛም ዐማራን አንንካም ብለው ለዐማራው የሽምግልና መልክት ላኩ። 

"…ዐማራውም ማመን አቃተው። እነሱ ግን አበክረው መለመን፣ ማግባባትም ያዙ። እመኑን፣ ቃል ቃል ነው። ቃላችንን አናጥፍም። እናንተ በፍፁም እኛን እመኑን። ጠላታችን መንግሥት ብቻ ነው። እንዲያውም ትንሽ ትንሽ የቤት ሥራ ሰጡን። ፈትኑን በማለት ሽምግልናውን አጠናክሮ ቀጠለ። ዐማራውም እነሱን ማመኑን ትቶ የራሱን በቂ ዝግጂት በማድረጉ ላይ ቀጠለ። ከተኮሱብን አንምራቸውም። ካልነኩን ምን አገባን ብሎ በአይነ ቁራኛ እየተመለከተ ዝም አለ። እነሱም መልሰው ዐማራንና የዐማራን ንብረት አንነካም። የዐማራ ተወላጅ የሕግ ታራሚዎችንም አንነካም። እናንተ ብቻ ወደኛ እንዳተኩሱ። እንዳትመጡም ብለው ትናንት ስብሰባ ዋሉ።

"…በስምነታቸውም መሰረት ዐማራው የማርያም መንገድ ለኦነግ ሸኔው ሰጠ። እናም ትናንት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ በሁሉም አቅጣጫ ወደ ነቀምት ከተማ መትመም ጀመሩ። ነቀምት ከተማውንም ከበው የተኩስ እሩምታ ማዝነብ ጀመሩ። ከባድ ውጊያም ተደረገ ከፒፒ ጋር ተደረገ። በየሰዓቱ ግን ለዐማራው እየደወሉ ቃላችን እንደተጠበቀ ነው እያሉ ያረጋግጡ ነበር። ዐማራውም ቀለበት ውስጥ ስለከተታቸው ዝም ብሎ ያያቸው ነበር። እስከአሁን በቃላቸው መሰረት ከዐማራው ወገን ከኗሪውም ይሁን የሕግ ታራሚ የተነካ የለም።

"…ውጊያውም ቀጠለ በጉትን መግቢያ፣ በአዲስ አበባ መግቢያ፣ በሻንቡ መግቢያ፣ በበደለሌ መግቢያ በሁሉም በኩል የሚሠማው ተኩሥ ብቻ ሆነ። የመንግሠት አካል የሆኑት ወታደሮች ምንም መቋቋም አቃታቸው። ብዙዎቹም ከጀርባም ተመቱ። ዐማራው እየወጣ ወደማረሚያ ቤቱ መሸሽ ጀመረ። ማረሚያ ቤቱ ጃቶ ይባላል። ዘመዴ ዐማሮቹ ለምን ወደዛ ሸሹ ካልክ እዚያ የመንግሥት ኮማንዶና ጥምር ጦር ስለነበረ ነው። እነሱ ግን ለራሳቸውም ሳይሆኑ ቀሩ። ጧት አንድ ሰዓት ላይ ኦነጎቹ ማረሚያ ቤቱን ያዙት። ዐማራውንም አይዟቹህ ተባራሪ ጥይት ብቻ እንዳይመታችሁ እየተጠነቀቃችሁ ወደ ቤታቹህ ተመለሱ ብለው ሸኙት።  ውጊያው ቀጠለ የመሣሪያ ግምጃ ቤትም ተዘረፈ። የዞን አስተዳደሩ፣ ሁሉም ባንኮች፣ ተቋማት በሙሉ ተዘረፉ። አሁን ሙሉ ከተማውን ይዘውታል። ዐማሮቹ ግን በተጠንቀቅ ቆመዋል። መንግሥትም፣ ሸኔም ገዳያቸው ቢሆንም ሸኔ ቃሉን ቢያፈርስ ለመግጠም ዝግጁ ሆነው ቆመዋል። ከወለጋ ዩኒቨርስቲም እስከአሁን የተነካ እንደሌለም ተነግሯል።

• አዲስ አበባ ግን ከብልፅግና ጋር ወደፊት ብሎ ጭፈራ ላይ ነው። ወደ አሶሳም ሽግር አለ። ጅባትና ሜጫም ውጊያ ላይ ናቸው።

"…ቆይቼ እመለሳለሁ…!!
49.9K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 13:59:02
"…የነቀምቴ መረጃ ነው። ሊንኩን ከፍታችሁ አንብቡት

http://t.me/ZemedkunBekeleZ
47.0K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 13:18:19
"…አላችሁ ወይ…?

"…አሁን ገና ስልክ ዘጋሁ። የነቀምቴውን ውጊያ ምስጢር ከቦታው ከስፍራው ያለ ወዳጄ ላከልኝ። የዐማራውንና የኦነግን ስምምነትም አጫወተኝ። ወያኔ የተሸወደችውን ኦነግ አርሞ፣ አስተካክሎ ከዐማራው ጋር የተስማሙበትን ነገረኝ። ጻፈልኝም። እኔም ለእናንተ ልነግራችሁ ወደድኩ አላችሁ ወይ…?

"…አላችሁ…!!
48.5K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 13:04:38
"…የነቀምቴ ፖሊስ ጣቢያዎችን እና የመንግሥት ተቋማትን አውድመዋል። ከ4ሺ በላይ እስረኞችንም በዕለተ ሰንበት ወደምትፈልጉበት ሂዱ ብለው ለቀዋል።

"…ተባራሪ ጥይት ከመታው በስተቀር እስከአሁን ሆን ብለው ንፁሐን ዜጎችን አለመግደላቸውም የደረሰኝ መረጃ ያሳያል። እስረኞች ባስፈቱበት ሰዓት ለእስረኞቹ የየትኛውም ብሔር ብትሆኑ ግድየለንም። እኛ ፀባችን ከመንግሥቱ ጋር ነው። እስከአሁን የመጣንበትን መንገድ ገምግመናል። ስህተትም እንደነበር አምነናል። እናም ንፁሐን በእኛ ከእንግዲህ አይገደሉም እንዳሏቸው ተሰምቷል። ህዝቡንም ከቤታችሁ ወጥታችሁ በሌባ፣ በዱርዬ እንዳትዘረፉ ከቤት አትውጡም ብለዋል ተብሏል።

"…ኦነጎቹ ወለጋ ዩኒቨርሲቲም የገቡ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ለተማሪዎቹ ምንም ዓይነት ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ እና ተረጋግተው እንዲቀመጡ መናገራቸውን የመረጃ ምንጮቼ አሳውቀውኛል።

"…የሚገርመው ነገር የኦሮሚኛ ፔጆች በሙሉ ስለሁኔታው እያወሩ ነው። በቲክቶክ ላይ ሳይቀር Live እየገቡ እየጨፈሩ ነው። የብልፄ የአማርኛ ክፍል አክቲቪስቶች ግን ስለ ነቀምቴ ምንም ትንፍሽ አይሉም። የሰሊጥ ብር ያሰከረው ጫታም ሆድ አምላኩ አክቲቪስት ስለ ኦነግ ካወራ ስለሚቀነደብ ትንፍሽ አይልም። ስለ ስንዴ፣ ስለ ሂዊ፣ ስለ ፓርክ ነው ወሬው። እነሱ ሃገር ወዳድ ሌላው ባንዳ መሆኑ ነው። የሚያሳዝነኝ ወታደሩ ነው። ከኋላ ከፊት እንደቅጠል እየረገፈ ነው። ህዝቤ አይደለም ስለ ጉዳዩ አስተያየት ለመስጠት ይቅርና በጉዳዩ ላይ ኮመንት ለመስጠት ከጥቂቶች በቀር ሲያልባቸው ይታያል። "የጌታ ልጆችማ" ደንታቸውም አይደል።

•…ቆይቼ እመለሳለሁ።
49.1K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 12:34:39
ምስኪን ወታደር…!!

"…በነቀምቴው ጦርነት ከኦነግ ጋር የሚዋጋው የኢትዮጵያ ወታደር ነው። ከጀርባ ከፊት እንዲህ አድርገው ረፍርፈውታል። በጣም ያሳዝናል። ስለዚህ የሚዘግብ፣ የሚነግራችሁም የለም። እናንተም መስማት አትፈልጉም። በሰሜኑም እንዲሁ ነው ወታደሩ ያለቀው። በምዕራቡም እንዲሁ እያለቀ ነው። እነ ደርቤ ይሄንን አይዘግቡም።

• የሞተ ተጎዳ…!!
48.2K views09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 12:25:00
ነቀምቴ… !!

"…የከተማ ውስጥ ጦርነት ማለት ይሄንን ነው የሚመስለው። ፊልም ላይ ብቻ የምታውቁት ካላችሁ የከተማ ውስጥ ጦርነት ማለት እንደዚ ኖ። ኦነግ የሚተኩሰው ብሬን እቤትህ እያለህ ሊጎበኝህ ይችላል። አዲስ አበባ ሰምተሻል።

"…ሂዊና ብልፄ፣ ጄ ታዴ ወረደ እና ጄ ብሬ ጁላም ኬኒያ ድረስ ሄደው ህወሓት ትጥቅ ስለሚፈታበት ጉዳይ ሊወያዩ ነው። ከተስማሙ 250 ሺ የህወሓት ጦር መሳሪያውን አስረክቦ እንደ ደርግ ወታደር የተሃድሶ ካምፕ ይገባል ማለት ነው። ኦነግ ግን ቤተሰብ ስለሆነ ተቆጪም፣ ገልማጭም የለበትም። አዲስ አበባ ግን የሌማት ቱሩፋት መርሀ ግብር ላይ ናት።

• ቆይቼ እመለሳለሁ።
49.2K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 11:38:05
ነቀምቴን ይዘውታል ተብሏል…!!

"…ከምዕራብ ወለጋ የተነሣው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት (ኦነግ) ያለምንም እንከን ይዞታውን በማስፋት ዛሬ ጠዋት ምሥራቅ ወለጋ ገብቶ ነቀምቴን መቆጣጠሩን ከስፍራው የሚወጡ ተንቀሳቃሽ ምሥሎችና ፎቶግራፎች ያሳያሉ።

"…ኦሮሞ መሩ ማዕከላዊ መንግሥቱ ግን የኦነግ ጉዳይ እንዲወራ አይደለም እንዲተነፈስ አይፈልግም። ለመንግሥቱ ያደሩት ሆዳም አክቲቪስቶችም ሆኑ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችም የሥልጣን ፍርፋሪ፣ የገንዘብ ብጣቂ፣ ለሆዳቸው እንጀራን፣ ለነውራቸው ጭምር ድርጎ ይከለክለናል ብለው ስለሚሰጉ ትንፍስ አይሏትም።

"…ትን ያድርጋቸውና አዳሜ የሂዊን የፊርማ ጉዳይ ሲተነትን ይውላል። ሂዊም ትጥቋን አልፈታችም። ውጊያውም እንደቀጠለ መሆኑ እየተሰማ ነው። ጠቅላየይ ሚኒስትሩ የስንዴ ማሳ ሲጎበኝ ውሎ ያድራል። በየፓርኩ ዘጭ ብሎ ሲንፈላሰስ ይውላል። የአዲስ አበባ ህዝብ (ሀብታሞቹን ማለቴ ነው) ለልጆቻቸው የመጫወቻ ፓርክ ስለተሠራላቸው የሌለ ፈንጠዝያ ላይ ናቸው።

"…ሀረርጌ ኩርፋ ጨሌ ጦርነት ላይ ናት። በምሥራቅ ሸዋ ውጊያ ላይ ናቸው። በሰሜንና ምዕራብ ሸዋ አንዳንድ ወረዳዎችን ኦነጎቹ ማስተዳደር ጀምረዋል። ዲያቆናት ይታረዳሉ፣ ካህናት ይታፈናሉ፣ ይገደላሉም።

"…በዶክመንተሪ ፊልም ጮቤ የሚረግጠውን ስታይ፣ የገበሬ እርሻ መጎብኘትን እንደ ሥራ የሚቆጥር የክልል መሪ እና የሚንስትሮች መንጋን ስታይ፣ ያን ተከትሎ ከስር ከስር እያቶሰቶሰ ያልበላውን የሚያክ መንጋ ስታይ ሰዉ ምን ነካው ሳይሆን ሰዉ አዕምሮውን እንደአጣ ይሰማሃል። እንደሚሰማው መከላከያው ከኦነግ ጋር አይዋጋም። ልዩ ኃይሉ ይሸሻል። ኦነግ ወደ አዲስ አበባ ጉዞውን ቀጥሏል። ምንአልባት አምቦ ሲደርስ ወይ ድርድር ይባላል አልያም ተአምረኛው አቢቹ ጦር ሜዳ ዘምቶ ኦነግን ደምስሶ ፒፕሉ ላይ ድራማ ይሠራል።

• ቆይቼ እመለሳለሁ።
54.3K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 14:25:04
ድሉ የማነው…?

"…ስምምነቱን እና የተገኘውን ድል በተመለከተ ህወሓት እንዲህ እያለች ነው። "…የዚህ ስምምን መሠረታዊ ዋነኛ ድል ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ መከበሩ ነው።…ወደ ጦርነት የገባነውም ተገደን እንጂ ጦርነት ምርጫችን ሆኖ አልነበረም። ጦርነቱን የጀመርነው (በአዲስ አበባ) በኩል" ተቀባይነት በማጣታችን ነው። (አዲስ አበባ የሚለው የቀድሞውን ወራሪ፣ ፋሽስቱ ዐቢይ አሕመድ፣ መሸረፈት፣ ባንዳ፣ የሚለውን ነው። እሱን አሻሽሎ አዲስ አበባ ብሎታል የመቐለው መንግሥት የአዲስ አበባውን መንግሥት። የሁለት ሃገራት መንግሥት መሆናቸው ነው በእነሱ አጠራር። ወገኛ።)

"…ደቡብ አፍሪካ የተደረገው ስምምነት " ሕገ መንግሥቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲከበር የጋራ ሥምምነት የተደረሰበት ሆኖአል ካለ በኋላ ይህ የእኛ ጥያቄና ፍላጎት ሆኖ አፈጻጸሙ ግን ቀጣይ ውይይት ይፈልጋል ይሏል በመግለጫው።

"…ከድሉ በኋላ ገና ውይይት አለ ማለት ነው። እንጠብቃለን። እና ህወሓት ሕገ መንግሥቷን አስከብራ ዳግም ኢህአዴግ ቁጥር 2 ሆና ልትገለጥ ነው ማለት ነው…? "…ትልቁ ድላችን ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማስከበራችን ነው። ወደ ጦርነት የገባነውም ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ስለተጣሰ ነበር ብላለች ሂዊ።"

"…ሕገ መንግሥቷን አስከብራለች። ከዚያስ ቀጥሎ የሚሆነው ምንድነው…? አንቀፅ 39…

"…እስቲ ተወያዩበት። በዚህ ድርድር ያሸነፈው ማነው…? አሸናፊም፣ ተሸናፊም የለም የሚለውን ፉገራ እናቆየውና አሸናፊው ማነው…? ሕወሓት? ዐማራ…? ኦሮሞ…? ኢትዮጵያ…?

• የተቀበል ሰዓታችን እስኪደርስ እንወያይ…!!
23.9K views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 12:26:50
ተቀበል…!!

"…እንደተለመደው ዛሬ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ አዝናኙ የተቀበል መርሀ ግብራችን ይቀጥላል… አዝማሪው መሰንቆውን ወልውሎ፣ ድምጡን አሳምሮ ይጠብቃችኋል። ከእናንተ የሚጠበቀው ከወዲሁ ግጥም ጥፋችሁ በማዘጋጀት ሰዓቱ ሲደርስ ለአዝማሪው ማቀበል ነው። ግጥማችሁን ጽፋችሁ አዘጋጁ።

ተቀበል…

ይብላኝ ለተራበች ልጇን ላጣች እናት
ይብላኝ ለዛች እህት ክብሯ ለጠፋባት 
            "አዎን ይብላኝለት"
የዘመን ድካሙን ለተነጠቀ አባት
በጫካ በዱሩ ለመከነው ወጣት።
አዋጊማ ይሄው ተቃቅፎ  ታረቀ
ሟች አጥንቱ ሳይፈርስ ገዳዩ ቦረቀ
•••
ብሽቅ ፖለቲካ ቅጥ የለሽ ድርድር
ዕልፍ ህዝብ ፈጅቶ መባባሉ ይቅር
        "ሟችን ቢያሰኝም ቅር"
•••
ጦርነት ቀጥሎ ከምናጣ ሌላም
ያለፈው ቢያመንም ይበጀናል ሰላም
    ቢረፍድም ገብቷችሁ
     ደግ ታረቃችሁ
እስኪ እውን ይሁን የይቅርታው ወሬ
መቸም የኛ ነገር ሁኗል እያደሩ ጥሬ

ሰላም…!  ሻሎም…!
37.1K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ