Get Mystery Box with random crypto!

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 249

2022-11-04 20:33:01
ታርሟል…!!

"…ትናንት አሚኮ "አሸባሪው ወያኔ" ብሎ ዜና ሠርቶ ነበር። ይሄንን የትግራይ ልጆች አቁም እኛ አሸባሪ አይደለንም፣ አሸባሪ ልንጠራ አይገባም ብለው ቅሬታ አቅርበው ነበር። እናም ዛሬ አሚኮ አሸባሪው ወያኔ የሚለውን አውጥቶ አርሞ አስተካክሎ ጽፎታል።

• ነገ…

"…በአገኘሁ ተሻገር እና በዶ/ር ይልቃል ከፋለም የወልቃይት ጉዳይ ቀይ መስመር ነው ተብሎ መነገሩና በአሚኮም መዘገቡ ይታወሳል። ነገስ ይሄም ይታረም ይሆን…?

• በነገራችን ላይ ፓርላማው በይፋ አሸባሪ ያለውን ህወሓት ፓርላማው በይፋ አሸባሪነቱን ባላነሳበት ሁኔታ አሚኮ ምነው ፈራ? የሚል አይጠፋም። ከስምምነቱ አንዱ በሁለቱም ተደራዳሪዎች ወገን እርስ በእርስ ነቆራ ይቅር ተባብለው በመስማማታቸው ነው።

"…ከዚያ ከመቀሌም ፋሽስቱ ዐቢይ፣ ተስፋፊው ዐማራ፣ መሸረፍት ወዘተ የሚለውን ነቆራ አቁመው ይሆን…? ካቆሙ መልካም ነው። ትግራይ ትስዕር፣ ሃለዋትናን ድሕነትናን ብቕልፅምና የሚሉትስ ቀርቷል ወይ…?

• ለማንኛውም " አሸባሪው ወያኔ" ታርሟል።
71.0K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 18:00:56
ጥያቄ ነው…?

"…መንግሥት የተደራደረው፣ የተወያየው፣ ተደራድሮና ተወያይቶም ከስምምነት ደርሶ የተፈራረመው ከማን ጋር ነው…? ከህወሓት ጋር ነው ወይንስ ከ ቲዲኤፍ ጋር…?

"…ጌታቸው ረዳ እና ጀነራል ጻድቃን የማን ወኪሎች ናቸው…? ህወሓትን ወይስ ቲዴኤፍን ወክለው ነው የተፈራረሙት…?

• ኦነግ አዲስ አበባ ቢሮ ከፍቶ፣ በአንደኛው ክንፉ የባህልና የስፖርት ሚንስትር ሆኖ ደግሞ በሌላኛው ክንፉ ኦነግ ሆኖ ጫካገብቶ እንደሚዋጋው ዓይነት ያለ ነገር ከሆነ ብዬ እኮ ነው…?

• አሁን ትጥቅ ይፈታል ተብሎ የሚጠበቀው የህወሓት ሠራዊት ነው ወይስ ቲዲኤፍ የሚባለው…?

• የገባው ያስረዳኝ… ተወያዩ… እንጠይቅ…እንጠያየቅ። በጨዋ ደንብ እንወያይ።
76.0K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 13:51:05
"…ከሰሜን ዕዝ ጀምሮ በዐማራና በአፋር በትግራይም ያንን ሁሉ ህዝብ አስጨፍጭፎ የራያው ተወላጅ ጀነራል ጻድቃን በመጨረሻ ህንፃዎቹና ቪላዎቹን የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንኩንና የራያ ቢራ ፋብሪካ ፋብሪካውን አድኗል። ማንሞኝ አለ።

"…በሉ እናንተም በረሃ ከርሞ የመጣ ጄነራል ስለሆነ በአንበሳ ባንኩ ገንዘባችሁን አስገቡለት። በጦርነቱ ምክንያት ምርት አቁሞ የነበረው የራያ ቢራም በቅርቡ ሥራ ይጀምራልና ቶሎቶሎ እየጠጣችሁ አቋቁሙት። ዳሽን፣ በደሌ፣ ምናምንን ለጊዜው አቁሙና የራያውን ልጅ ራያ ቢራን ጠጡለት። አፍርአባክ ደም ያስጠጣችሁና ልል ብዬ ከአፌ መለስኩት። ለጥቂት ልሳሳት ነበር።

"…ቦሌ መንድኃኔዓለም 2 ህንፃ፣ ራያ እና ጋምቤላ የእርሻ ባለቤት ነው ጻድቃን። እስከ አሁን ዐቢይ ደብቆ ህይወቱን አቆይቶለታል ሻአቢያ ግን የሚፋታው አይመስለኝም። ለጊዜው እንደተወራው አዲስ አበባ ከሆነ አርፏል ከሚባልበት ከእስካይ ላይት ሆቴል ባይወጣ ጥሩ ነው።

"…ሁለቱ የራያ ልጆች ጌቾና ጻድቃን ህወሓትን ሜዳ ላይ አስጥተው እነሱ አዲስ አበባ ገብተዋል። በሸነና እያሉም ነው። ወዳጄ እደግመዋለሁ። የሞተ ተጎዳ።

"…ያለ ባል የቀሩ ሚስቶች፣ ያለ አባት የቀሩ ልጆች፣ በዱላ ከስናይፐር ጋር ተናንቆ የረገፈው ምስኪን ገበሬ፣ ትምህርት ቤታቸው ወድሞ መማር ያቆሙ ተማሪዎች፣ ማስተማር ያልቻሉ መምህራን፣ ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያው የወደመበት ህዝብ፣ ውኃ ያጣው፣ በጦርነቱ የተደፈሩ እናቶች። የታረዱ ካህናት፣ የተረሸኑ ዲያቆናት፣ ሼኮች፣ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትና መስጂዶች፣ በበሽታ፣ በረሃብ ያለቀው፣ የተፈናቀለው፣ ቤተሰቡ የተበተነው ምስኪን ህዝብ፣ እሱ ተጎዳ። እንጂማ የጦርነት መጨረሻው የታወቀ ነው። በኢትዮጵያ ደግሞ ሚልዮኑን ትገድላለህ በእርቅ ሰበብ ነፃ ሆነህ ተንፈላሰህ ትኖራለህ።

• ጧ በል እደግመዋለሁ የሞተ ተጎዳ…!!
82.3K views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 10:46:39
ታርደዋል…!!

"…ጥቅምት 23/2015 ዓም ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሁሩታ ዶሬ ቀበሌ አዲስ ሕይወት በምትባል የገጠር ከተማ ላይ ኦነግ ሌሊቱን በሙሉ ሲገድል እና ሲዘርፍ አድሯል። በዚህም 5 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የሞቱትን አስከሬን እንኳን የሚያነሣ ጠፍቶ እስከቅርብ ሰዓት ድረስ ማን ከማን እንደሆነ ባይታወቅም የተኩስ እሩምታ እንደሚሰማ ተነግሯል። ገዳዮቹ ያስቀሩት ንብረት የለም። ከብቶች፣ በጎች፣ ሞተር ሳይክል ሳይቀር ዘርፈው ወስደዋል። እንደተለመደው ከጭፍጨፋው በፊት ቀደም ብሎ ቴሌ የስልክ ኔትወርክ በማጥፋት ገዳዮቹን ተባብሯል። ይሄ በኦሮሚያ የተለመደ ነው)

"…ይህ አካባቢ የላይኛው አዋሽ አግሮ እንደስትሪ ያለበትና ጥንታዊው የመንግሥት እርሻ ልማት የሚገኝበት እና እሁን አልአሙዲን የገዛው እርሻ ያለበት አካባቢ ነው። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ለሥራ መጥተው ከ80 ዓመት በላይ የኖሩበት ያለሙት ሥፍራ ነው። አሁን ግን ሕገ በመንግሥቱ መሠረት እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ።

"…ከሶደሬ በታች ከዶኒ ከተማ ጀምሮ አዲስ ሕይወት፣ ተስፋ ሕይወት፣ አቦምሳ፣ መርቲ፣ መታሃራ የሚገኙ ከኦሮሞ ውጪ ያሉ ነገዶች በሙሉ በጅምላ እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ። ጥቅምት በ19/2015 ዓም አሸብር አለማየሁ የሚባል ወጣት ገድለው አስፓልት ላይ ጥለው ሄደዋል። ኦነግ ነው የተባለው ኃይል ከመጨፍጨፉ በፊት የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች በቦታው የነበሩ ሲሆን ልዩ ኃይሎቹ ጠዋት ሲለቁ ነው ሌሊት ሸኔ የተባለው ማታ ገብቶ ጨፈጨፋቸው የተባለው። ገዳዩ ግን ራሱ ልዩ ኃይሉ ነው የሚሉም አሉ።

"…ጥቅምት 23/2015 ዓም በአዲስ ህይወት የታረዱ ዐማሮች ስም ዝርዝር…
፩. ዳምጠው አዘነ
፪. ፀጋው ባልከው
፫. ገዛኸኝ በላይ
፬.  እታትዬ ላቀው
፭.  መላኩ አባተ

• እንደተለመደው ነፍስ ይማር በሉ።
85.5K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 18:11:26
"…ገባ ገባ በሉማ ልንጀምረው ነው።




• https://rumble.com/v1ralza--ethiobeteseb-.html

• በዛሬው የኢትዮቤተሰብ የእኛ ቤተሰብ ሚዲያ መርሀ ግብር ላይ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ከሃገረ አማሪካ ሜሪላንድ (ሃገረ ማርያም) እኔ ዘመዳችሁም ከሃገረ ጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ ሆነን በወቅታዊው ጉዳይ እንደተለመደው "ነጭ ነጯን" ሃሳባችንን "…በሕገ መንግሥቱ መሠረት… እናወጋለን፣ እናንሸራሽራለን። ጠብቁን።

"…በሌላ በኩል የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈልጉ ወገኖች በሙሉ ከታች በተቀመጡት ሊንኮች አማካኝነት በልገሳ መሳተፍ ትችላችሁ። አመሰግናለሁ። 

https://donorbox.org/zemedemedia

https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB

… ሻሎም !  ሰላም !
62.7K viewsedited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 00:05:16
"…በቁማርተኞቹ ተታለው የሞቱት ተጎዱ።

• ክብር ሃገር ተደፈረች ብለው በአረመኔው ዐቢይ አሕመድ ሴራ በየዱሩ እንዲህ እንደቅጠል ለረገፉት ለሃገሬ ልጆች።

• ክብር ለእናንተ። ገዳያችሁማ ትጥቅ ፍታ ብቻ ተባለ እኮ። ገዳያችሁማ ተመልሶ ሥልጣን ላይ ሊወጣ ነው ተባለ እኮ። ገዳያችሁማ አሸባሪ የተባለው ስሙ በአስቸኳይ በፓርላማው ይነሣለት ተባለ እኮ። ክብር ለእናንተ ለሃገሬ ጀግኖች።

• ቀጥሎ ግን ደማችሁ ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም። እንዲህ በሴራ ያስገደሏችሁ፣ ያስጨፈጨፏችሁ በሙሉ እንዲሁ ይገደላሉ። ዓይናችን እያየ፣ ጆሮአችን እየሰማ ይገደላሉ። ቀኝ ትከሻዬን የሚሸክከኝ ነገር የሚነግረኝ ይሄንኑ ነው።

• አቦ በሰላም እረፉ…!!
19.5K viewsedited  21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 22:25:51
ሄሮድስና ጲላጦስ

… ሄሮድስና ጲላጦስ ብዙ ጊዜ ጸበኞች ቢሆኑም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለመፍረድ ግን ስምም ሆነው የታዩ የቦለጢቃ መሪዎች ነበሩ። ሉቃ 23፥12።

"…ደብረፂ እና አብይም በአደባባይ ፀበኛ ይምሰሉ እንጂ በዐማራ ሞት እና ውድመት ግን ስምም ናቸው። እደግመዋለሁ የሄሮድስ እና የጲላጦስ ጠብ ክርስቶስን በማስገደሉ ላይ ሽግርም ሳንካም አልነበረበትም።

"… ሄሮድስና ጲላጦስ ሥራ ላይ ናቸው። እኔም ከአቋሜ ወይ ፍንክች። ቅር የሚልህ ካለህ ጧ በል።

• ወልቃይት ጠገዴ ራያና ጠለምት እንደምን ደኅና እደሩልኝ።
33.6K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 20:04:43
"…በመጨረሻም የሚጠበቀው ተፈጽሟል…!!

• ክብር እናት ሃገሬን ብለው ለተሰዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁሉ ይሁን…!!

• የእነ እሸቴ ሞገስንም ነፍስ ይማር…!!
61.6K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 19:51:30
"…የሞተ ተጎዳ…!!
62.6K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 19:22:44
"…አባቴ እሱ ጣጣ አለው እንዴ? ዝንጥ ብሎ ሸማኔ እየጎበኘልህ ነው።

ዐቢይን ያመነ
ጉም የዘገነ
64.0K viewsedited  16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ