Get Mystery Box with random crypto!

የዘመነ ካሴ አጭር ደብዳቤ…!!                                          | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዘመነ ካሴ አጭር ደብዳቤ…!!

                                          ቀን፦ 01-02-2015
   ለዘመዴ…!     

"…እንዴት ሰነበትህ? እኔ በጣም ደህና ነኝ። በፍጥነት ልጻፍልህ:-

"…የውልህ ግብግቡ ቀጥሏል። የዛሬውን የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ሰምተህ ይሆናል። ልክ የፍ/ቤት ውሏችን አልቆ መኪናው ሲንቀሳቀስ መኪናውን አጥፈው የወረዳው ፍ/ቤት በር ላይ አቁመው "ውረድ" አሉኝ። "ልክ እግሬ ከመኪናው ወርዶ መሬት እንደነካ ግብግብ እጀምራለሁ። ወደ አንዳችሁ ጉሮሮ ነው የምመጣው። ይህ የነ ኮማንደር ዋናው እና የነ ኮማንደር ጥበበ ችሎት ነው።.........." አልኋቸው። ኮማንደር ዋናው መጥቶ "ውረድ" ሲለኝ "ያንተ ችሎት ላይ አታቆመኝም ወ.ዘ.ተ" አልሁት። ከ40 ደቂቃ በላይ ተፋጠን ቆምን፤ በመጨረሻ ወደ ወህኒ ቤት ተመለስሁ።

"…አሁን ከመሸ ደግሞ ወረዳ ፍ/ቤቱ ለአርብ ሦስት ሰዓት እንድቀርብ መጥሪያ ልኳል። በተዓምር እዚህ የቅጥፈት የነዋናው ችሎት እንደማልቀርብ ለማረሚያ ቤቱ ኮማንደሮችም አሁን ነግሬያቸዋለሁ። ለሚፈጠረው ቀውስ ሓላፊነት እንደማልወስድም ጭምር።.......... ሌላ ጊዜ ሰፋ አድርጌ እጽፍልሃለሁ
                                 ወንድምህ
                                 ዘመነ ካሴ
                 ከባህርዳር ወህኒ ቤት

"…ደብዳቤው ደርሶኛል። ጠበቃ እና ታዛቢ በሌለበት ለብቻው ወስደው ያደረሱበትን ወከባ ህዝቡ እንዲያውቀው ነው አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ለእኔ የጻፈልኝ። ከበረሀ ጀምሮ የሚጽፍልኝ የእጅ ጽሑፉ ነው።

"…ከምር ኮማንደር ጥበበ እና ኮማንደር ዋናው እነማን ናቸው? ፎቶአቸው ያላችሁ ወዲህ በሉልኝ እስኪ?