Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለዶር ብርሃኑ ነጋ '…እነ ሌቦ ጀዋር መሀመድ ሌብነትን እንደ ትግል ስልት አድርገው ወደ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይድረስ ለዶር ብርሃኑ ነጋ

"…እነ ሌቦ ጀዋር መሀመድ ሌብነትን እንደ ትግል ስልት አድርገው ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ጎትተው ካመጡ ወዲህ ጨዋ፣ እንደ ቤተ መቅደስም ይፈራ የነበረውን የኢትዮጵያን የፈተና ሥርዓት ብልሽትሽቱን ማውጣታቸው ይታወቃል። ውሻ በቀደደው ጅቦቹ ገብተው ይባስ ብለው የክልል ሓላፊዎች፣ መምህራንና ባለሥልጣናት ሁሉ ተሳታፊ ሆነው በችርቻሮ ሳይሆን በጅምላ በተሰረቀ ፈተና ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲያግዙም ከርመዋል።

"…እናም ዶክተሩ ሆይ፣ ይሄን የገረረ፣ የከረረ፣ የገነገነ፣ የደነደነ ሌብነት ለመቀነስ፣ ከተቻለም ለማጥፋት የወሰዱት እርምጃ በእኔ እይታ የሚደገፍ ነው። 1 ቢልዮን ብር ኪሳራም ቢኖረውም ሙከራው የሚበረታታ ነው። በሂደቱ የተፈጠሩት ያረገዙ ተማሪዎች መውለዳቸው፣ የመኪና አደጋ፣ የድልድይ መሰበር፣ የሞትና መቁሰሉ ሁኔታም የፈጣሪ ሥራ እንጂ የእርስዎ ሴራ ነው ብዬም አላምንም። የሞቱትን ነፍስ ይማር። የቆሰሉትን ምህረት ፈውሱን ይላክላቸው።

"…የሆነው ሆኖ ዶፍተር ሆይ ሙከራዎ በአንዴ ባይጠራም በሂደት መቀነሱ ግን አይቀሬ። ነገር ግን ዘንድሮም ቢሆን እዛው ኦሮሚያ ውስጥ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ተሰርቆ የወጣ ነው የተባለ የእንግሊዝኛና የሂሳብ የፈተና ወረቀት በኢንተርኔት ሲዟዟር ታይቷል። ከፈተና በኋላ የተነሣ ይሁን ከፈተና በፊት ብቻ እንደ ድሮው በቴሌግራም በኅብረት ይሠሩታል ባልልም የተወሰኑ የሌባ ልጆች ስልክ አጭበርብረው ይዘው ገብተው ፎቶ አንሥተው መበተናቸው አልቀርም። ለዚህ ደግሞ ፍቱን መድኃኒቱ አለ። እሱም ለፍርዬ መንገር ነው። ኦነግ ዐማራን ሊያርድ ሆሮጉዱሩ ሲገባ ብቻ አይደለም ኢንተርኔት መዝጋት ፈተናው እስኪያልቅ ቢያንስ ከባልቦላው ምናለ አጥፍታ ብታግዝዎት። ደፍረው እንደ ዐቢይ አሕመድ ይጠይቋት። ወይ እሺ፣ ወይ እምቢ ነው የምትልዎት።

• ፈጣሪ ይርዳዎት።