Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Samitech
Cloudbridge
Traininginstitute
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.23K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-24 20:25:22
ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የስራ ርክክብ ተደረገ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የሥራ ርክክብ መደረጉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የጥገና ሥራውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በመጠበቅ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን ተከትሎ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የጠቆሙ ሲሆን የጥገና ሥራውም በተቀመጠለት የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡

@TikvahethMagazine
27.0K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 19:09:38
#Update: ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
27.5K views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 18:22:54
#Update: እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን እንደሚችሉ ተገለፀ

እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማከናወን ይፋ በተደረጉት የኢትዮቴሌኮም  የአገልግሎት ማዕከላት በአካል በመገኘት፣ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደ ፦

ቀበሌ መታወቂያ፣
የታደሰ የመንጃ ፈቃድ፣
ፓስፖርት የመሳሰሉ ሰነዶችን በመያዝ ወይም የሰው ምስክር በማቅረብ በነጻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከሎቻችን የትኞቹ ናቸው?

በአዲስ አበባ፦ ውሃ ልማት (ሃያ ሁለት)፣ ልደታ፣ ስታዲየም፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ገርጂ፣ አያት፣ ስድስት ኪሎ፣ ጉርድ ሾላ፣ ሽሮሜዳ፣ ሳሪስ፣  ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ ጀሞ፣ ለቡ፣ ቤተል፣ አራዳ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ እና ቲፒኦ (ጥቁር አንበሳ) ናቸው።

በሪጅኖች ደግሞ ፦ በሐረር፣ ደብረብርሀን፣ ፊቼ፣ ለገጣፎኣ፣ አምቦ፣ ሰበታ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ አዘዞ፣ መቀሌ(ሁለት)፣ ባሕርዳር፣ ዓባይ ማዶ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሐዋሳ(ሁለት)፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ጅማ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ጋምቤላ ነቀምቴ እና አሶሳ ናቸው።

ከከተማ እና የገጠር ነዋሪዎች በተጨማሪ የዩኒቨርስቲ፣ የከፍተኛ እና የብሔራዊ 2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኞች፣ በተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች እና በሀገራችን የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች ምዝገባ ማከናወን ይችላሉም ተብሏል።

@TikvahethMagazine
27.1K viewsedited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 17:16:59
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ዜጎችም ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በማስጀመር በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት ማቀዱም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
23.7K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 17:16:45
ኬንያ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የፕላስቲክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያን መጠቀም ከለከለች

የኬንያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር የፕላስቲክ ብክለት እያስከተሉ ነው ያላቸውን ቆሻሻን ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ የሚያገለግሉትን ፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እገዳውን በኤፕሪል 8 ያስተላለፈ ሲሆን ኬንያውያን ዜጎች የእገዳ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በ90 ቀናት ውስጥ መጠቀም ማቆም አለባቸው ተብሏል።

በመሆኑም ሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃን እና ጤናማ የቆሻሻ አወጋደድን ለማረጋገጥ በባህሪያቸው ሊበሰብሱ የማይችሉትን የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም በማቆም፣ ቆሻሻ አስወጋጅ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው ሙሉ በሙሉ ሊበሰብስ የሚችል ቆሻሻ ማጠራቀሚያ (biodegradable bags) ብቻ እንዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱ ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
23.6K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 12:17:29
በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ

የካላዛር ሕሙማንን ለማከም ለ17 ቀናት የሚሰጠውን የመርፌና የእንክብል መድኃኒት ሙሉ ለሙሉ በእንክብል ብቻ ለመተካት የሚያስችለው መድኃኒት፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 44 በሚደርሱ 52 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ሙከራው ተጀመረ።

በምርምሩ 15 የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩ ተጠቁሟል።

በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱ የ “LXE408” በአፍ  የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ በዓመት ከ2 እስከ 3 ሺ ሰዎች በካላዛር በሽታ ይያዛሉ ሲባል በበሽታው ተይዘው ሕክምና ካላገኙት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ እንደሚሞቱ ተጠቁሟል።

Credit: Sheger, reporter

@TikvahethMagazine
25.9K viewsedited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 12:17:15
በአዲስ ከተማ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ 7 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ በአቅራቢያው ያለ መኖሪያ ቤት ላይ በመናዱ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸዉ አለፈ።

አደጋው የደረሰው በዛሬው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 11 :00 ሰዓት ላይ ነው። የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን የአደጋዉን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
24.0K views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 12:16:50
ታላቅ ቅናሽ

ድርጅታችን ድሪም ቢዉልደርስ በካሬ 90,000 ሲሸጥ የነበረውን ውደ 79,900 ብር ቅናሽ  አድርጓል።

በ10% ቅድመ ክፍያ፣ በ9 ዙር፣ በ2 አመት ከ6 ወር ከፍለዉ የሚጨርሱት።

በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት

በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች፣ ከተሟላ መገልገያዎች ጋር

ባለ 1 መኝታ  79.92ካሬ  91.56ካሬ 
ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ   127.44ካሬ 
ባለ 3 መኝታ  169.92ካሬ

ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን 0974388888
22.3K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 12:16:50
በወር 15,000 ብር ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
ብስክሌት
ሞተር
E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-


ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

https://t.me/DriversRegistration_bot

ወይም

9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
23.7K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 17:55:25
#Update: በዲላ ከተማ ሚያዝያ 5 በጣለው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በከተማው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም መመለሱ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
19.4K viewsedited  14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ