Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞ | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ

የካላዛር ሕሙማንን ለማከም ለ17 ቀናት የሚሰጠውን የመርፌና የእንክብል መድኃኒት ሙሉ ለሙሉ በእንክብል ብቻ ለመተካት የሚያስችለው መድኃኒት፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 44 በሚደርሱ 52 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ሙከራው ተጀመረ።

በምርምሩ 15 የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩ ተጠቁሟል።

በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱ የ “LXE408” በአፍ  የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ በዓመት ከ2 እስከ 3 ሺ ሰዎች በካላዛር በሽታ ይያዛሉ ሲባል በበሽታው ተይዘው ሕክምና ካላገኙት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ እንደሚሞቱ ተጠቁሟል።

Credit: Sheger, reporter

@TikvahethMagazine