Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ ከተማ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ 7 ሰዎች ህይወት አ | TIKVAH-MAGAZINE

በአዲስ ከተማ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ 7 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ በአቅራቢያው ያለ መኖሪያ ቤት ላይ በመናዱ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸዉ አለፈ።

አደጋው የደረሰው በዛሬው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 11 :00 ሰዓት ላይ ነው። የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን የአደጋዉን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine