Get Mystery Box with random crypto!

ኬንያ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የፕላስቲክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያን መጠቀም ከለከለች የኬንያ የአ | TIKVAH-MAGAZINE

ኬንያ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የፕላስቲክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያን መጠቀም ከለከለች

የኬንያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር የፕላስቲክ ብክለት እያስከተሉ ነው ያላቸውን ቆሻሻን ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ የሚያገለግሉትን ፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እገዳውን በኤፕሪል 8 ያስተላለፈ ሲሆን ኬንያውያን ዜጎች የእገዳ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በ90 ቀናት ውስጥ መጠቀም ማቆም አለባቸው ተብሏል።

በመሆኑም ሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃን እና ጤናማ የቆሻሻ አወጋደድን ለማረጋገጥ በባህሪያቸው ሊበሰብሱ የማይችሉትን የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም በማቆም፣ ቆሻሻ አስወጋጅ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው ሙሉ በሙሉ ሊበሰብስ የሚችል ቆሻሻ ማጠራቀሚያ (biodegradable bags) ብቻ እንዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱ ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine