Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ዜጎችም ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በማስጀመር በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት ማቀዱም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine