Get Mystery Box with random crypto!

#Update: እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከና | TIKVAH-MAGAZINE

#Update: እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን እንደሚችሉ ተገለፀ

እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማከናወን ይፋ በተደረጉት የኢትዮቴሌኮም  የአገልግሎት ማዕከላት በአካል በመገኘት፣ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደ ፦

ቀበሌ መታወቂያ፣
የታደሰ የመንጃ ፈቃድ፣
ፓስፖርት የመሳሰሉ ሰነዶችን በመያዝ ወይም የሰው ምስክር በማቅረብ በነጻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከሎቻችን የትኞቹ ናቸው?

በአዲስ አበባ፦ ውሃ ልማት (ሃያ ሁለት)፣ ልደታ፣ ስታዲየም፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ገርጂ፣ አያት፣ ስድስት ኪሎ፣ ጉርድ ሾላ፣ ሽሮሜዳ፣ ሳሪስ፣  ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ ጀሞ፣ ለቡ፣ ቤተል፣ አራዳ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ እና ቲፒኦ (ጥቁር አንበሳ) ናቸው።

በሪጅኖች ደግሞ ፦ በሐረር፣ ደብረብርሀን፣ ፊቼ፣ ለገጣፎኣ፣ አምቦ፣ ሰበታ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ አዘዞ፣ መቀሌ(ሁለት)፣ ባሕርዳር፣ ዓባይ ማዶ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሐዋሳ(ሁለት)፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ጅማ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ጋምቤላ ነቀምቴ እና አሶሳ ናቸው።

ከከተማ እና የገጠር ነዋሪዎች በተጨማሪ የዩኒቨርስቲ፣ የከፍተኛ እና የብሔራዊ 2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኞች፣ በተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች እና በሀገራችን የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች ምዝገባ ማከናወን ይችላሉም ተብሏል።

@TikvahethMagazine