የሰርጥ አድራሻ:
ምድቦች:
ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች:
196.15K
የሰርጥ መግለጫ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524
Ratings & Reviews
Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.
5 stars
0
4 stars
1
3 stars
1
2 stars
0
1 stars
1
የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5
2024-04-08 18:09:28
የስብሰባ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መኮንኖቸች ማህበር (PHOA-E) 11ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ሚያዝያ 4-5 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒንስቲዩት (EPHI) አዳራሽ ያካሂዳል።
በጉባኤው ላይ የጤና ሚኒስቴር ፣ የጤና ቢሮ ፣ የዩኒቨርስቲ መምህራን ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ፣ ከተለያዩ የጤናና የምርምር ተቋማት የተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል።
@TikvahethMagazine
22.6K views15:09
2024-04-08 18:08:49
ከ7 እስከ 18 ለሆኑ ልጆች የኦንላይን ኮዲንግ ስልጠና
ስልጠና April 13 , 2024 ቅዳሜ ይጀምራል።
ከ7 እስከ 13 ለሆኑ ህጻናት የ6 ሳምንታት የscratch ስልጠና( ጌም እና አኒሜሽን እየሰሩ ነው ሚማሩት)።
ከ14 እስከ 18 ለሆኑት የ website ስልጠና ለ 2 ወር።
የምስክር ወረቀት ያገኛሉ
ክፍያ ለ6 ሳምንት ፕሮግራም 2500 ብር ነው።
ክፍያ ለ 2 ወር ፕሮግራም 3500 ብር ነው።
በቴሌግራም መረጃ ለማግኘት ያግኙን
@koderlabtrainingcenter ወይም በ 0940121072 ይደውሉ።
ይህንን ሊንክ በመጠቀም ሬጅስተር ያርጉ።
https://forms.gle/J3CeN5XE4vQW3MF49
23.1K views15:08
2024-04-08 16:13:51
የአፍሪካ ኅብረት ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ የዘር ማጥፋትና የጅምላ ጭፍጨፋን ለመከላከል ልዩ መልዕክተኛ ሾመ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ለመከላከል ሴኔጋላዊውን አዳማ ዲዬንግ የመጀመሪያ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ አድርገው ሾመዋል።
ልዩ መልዕክተኛው የተሾሙት በአፍሪካ አህጉር የጥላቻ እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ለመዋጋት የተያዘውን የህብረቱን አጀንዳ ለማስፈፀም ሲሆን ዲዬንግ በቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን የጅምላ ጭፍጨፋ መከላከል ልዩ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ተብሏል።
@TikvahethMagazine
25.3K views13:13
2024-04-08 15:20:30
#ጥቆማ
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ህክምና ክፍል እና ኤች.ሲ.ፒ ኪዩር ብላይንድስ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 11 ፥ 2016 ዓ/ም ድረስ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ለ 450 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን ነፃ ህክምና እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ስለሆነም የህሙማን ቅድመ ልየታ ስራ ከፊታችን ሐሙስ ሚያዝያ 3 ፥ እስከ 4 - 2016 ዓ.ም በሆስፒታሉ ውስጥ የሚከናወን ሲሆን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህመም ያለባችሁ ታካሚዎች በተጠቀሱት የቅድመ ልየታ እና የህክምና ቀናት በሆስፒታሉ ውስጥ በመገኘት የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥቆማ ቀርቧል።
አድራሻው አዲስአበባ ፤ ጉለሌ ክ/ከተማ ፤ ወረዳ 1፣ ከሽሮሜዳ ወደ ቁስቋም በሚወስደው መንገድ ላይ ሲሆን ታካሚዎች ለበለጠ መረጃ በሆስፒታሉ ነፃ የስልክ መስመር 998 ላይ መደወል ይችላሉ ተብሏል።
@TikvahethMagazine
26.5K viewsedited 12:20
2024-04-06 16:39:54
አንድ የታሪክ ተመራማሪ በመቅደላ ጦርነት የተሰረቁት የአፄ ቴዎድሮስ አልባሳት የት እንዳሉ ለማወቅ እየጣሩ ነው ተባለ
በእንግሊዝ አንድ የታሪክ ተመራማሪ ከ156 ዓመታት በፊት የተሰረቁት የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ አልባሳት የት እንዳሉ ለማወቅ እየጣሩ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ ወረራ ወቅት እጅ አልሰጥም ብለው መቅደላ ላይ የራሳቸውን ሽጉጥ ጠጥተው ከሞቱ በኋላ ለብሰውት የነበረው የክብር ካባ እና የአንገት ልብስ ከአስክሬናቸው ላይ ተገፍፎ ተወስዷል።
አልባሳቱ ወደ እንግሊዝ ከተወሰዱ በኋላም በስታሊይብሪጅ፣ ስታምፎርድ ፓርክ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጠው እንደነበር ሲገለፅ ሙዚየሙ በ1950ዎቹ ከፈረሰ በኋላ ግን እነዚህ ጥንታዊ ቅርሶች የት እንዳሉ አይታወቅም ተብሏል።
በጉዳዩ ላይ መጽሐፍ የጻፉት ሔቨንስ የተባሉት የታሪክ ተመራማሪ እንደሚሉት በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰዱ ቅርሶች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአገሪቷ ውስጥ ይገኛሉ። ከሐር የተሠራው የንጉሡ ትንሽ የአንገት ልብስም ስታሊይብሪጅ ውስጥ በሚገኘው ሰታምፎርድ ፓርክ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጦ ነበር።
ሙዚየሙ በ1950ዎቹ ከፈረሰ በኋላ የንጉሡ የአንገት ልብስ ወይም የካባው ክፍል በሆነ ሰው ቤት ውስጥ እንደሚገኝ ሔቨንስ እምነት እንዳላቸው እና የተረፉት ሌሎች ቅርሶችም ወደ ሌሎች የአካባቢው ሙዚየሞች መሰራጨታቸውን ገልፀዋል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የታሪክ ምሁሩ ለታሜሳይድ የአካባቢ ጥናት ተቋም፣ ለመዘክሮች እና ለማንቸስተር ሙዚየም ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች የጥንታዊ ዕቃዎች ማስቀመጫዎቻቸውን እንዲፈትሹ እያሳሰቡም ነው ተብሏል።
@TikvahethMagazine
20.1K views13:39
2024-04-06 14:25:58
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ የጀመረበትን 78ኛ ዓመት በማስመልከት ልዩ በረራ ሊያደርግ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነገው እለት ምሽት በረራ የጀመረበትን 78ኛ ዓመት በማስመልከት በታሪኩ የመጀመሪያ በረራ ወዳደረገበት ካይሮ ልዩ በረራ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ የመጀመሪያ በረራውን በአሥመራ በኩል ወደ ግብጽ ካይሮ ያደረገው ከ78 ዓመት በፊት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1946 ነበር። (ENA)
@TikvahethMagazine
23.4K views11:25
2024-04-06 14:25:34
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕዳሴ ግድብ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ 19 ቢሊዮን ብር መዋጣቱ ተነገረ
ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 193 ቢሊዮን ብር ወጪ የሆነ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ የካቲት 30 - 2016 ዓ/ም ድረስ ለግድቡ 19.2 ቢሊዮን ብር ማዋጣቱን ዶይቼ ቨለ ዘግቧል።
የሕዳሴ ግድብን ቀሪ አጠቃላይ ስራዎች ለማጠናቀቅ 50 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የሲቪል ግንባታው በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ ሲገለፅ የመካኒካል ሥራዎች ደግሞ በ2017 ይጠናቀቃሉ ተብሎ እቅድ መያዙን ተጠቁሟል።
የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎና ድጋፍ አሰባሳቢ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር የግድቡ አፈፃፀም 95.8 ከመቶ መድረሱን የገለፁ ሲሆን አንዳንድ ሚዲያዎች የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 99.8 ከመቶ ደርሷል ብለው የሚዘግቡት #ስህተት ነው ብለዋል፡፡
@TikvahethMagazine
21.3K viewsedited 11:25
2024-04-06 14:24:39
ከ7 እስከ 18 ለሆኑ ልጆች የኦንላይን ኮዲንግ ስልጠና
ስልጠና April 13 , 2024 ቅዳሜ ይጀምራል።
ከ7 እስከ 13 ለሆኑ ህጻናት የ6 ሳምንታት የscratch ስልጠና( ጌም እና አኒሜሽን እየሰሩ ነው ሚማሩት)።
ከ14 እስከ 18 ለሆኑት የ website ስልጠና ለ 2 ወር።
የምስክር ወረቀት ያገኛሉ
ክፍያ ለ6 ሳምንት ፕሮግራም 2500 ብር ነው።
ክፍያ ለ 2 ወር ፕሮግራም 3500 ብር ነው።
በቴሌግራም መረጃ ለማግኘት ያግኙን
@koderlabtrainingcenter ወይም በ 0940121072 ይደውሉ።
ይህንን ሊንክ በመጠቀም ሬጅስተር ያርጉ።
https://forms.gle/J3CeN5XE4vQW3MF49
20.6K views11:24
2024-04-05 18:53:09
በኢትዮጵያ ለአስከፊ ችግር ለተጋለጡ እርዳታ ፈላጊ ዜጎች 1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ በጄኔቫ ስብሰባ ሊካሄድ ነው
በመጪው ሚያዝያ 8 በጄኔቫ በኢትዮጵያ አስከፊ የምግብ ዋስትና ችግር በገጠማቸው ዜጎች ጉዳይ ላይ ለመምከር እና ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ በአጋር አካላት እና ሀገራት መሃከል ስብሰባ ሊደረግ መሆኑን ኦቻ አስታወቀ።
ስብሰባው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ እጅግ አሳሳቢ የሆኑ የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው ዜጎች የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲያገኙ የሚያስችል 1 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ለማሰባሰብ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በ 2024 በኢትዮጵያ 21 ሚሊዮን ዜጎች የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፀ ሲሆን ለዜጎቹ እርዳታ ለማድረግ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ቀደም ሲል ባወጣው ሪፖርት መግለፁ አይዘነጋም።
@TikvahethMagazine
26.6K views15:53
2024-04-05 18:46:57
#እንድታውቁት
ነገ ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲሱ ገበያ፣ ቀጨኔ፣ ደራ ሰፈር፣ ጥበብ ዕድገት ት/ቤት፣ ችሎት፣ ራስ ደስታ ሆስፒታል፣ እንቁላል ፋብሪካ፣ ገዳመ እየሱስ ቤ/ክ፣ ጭላሎ ኮካ፣ ቤሊየር ሆቴል፣ ቀበና እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል።
በተጨማሪም በፊሊጶስ ቤ/ክ፣ እስላም መቃብር፣ ሎሚ ሜዳ፣ ጠሮ መስጊድ፣ አቃቂ ኬላ፣ ገላን ኢንዱስትሪ መንደር፣ ወሰርቢ እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 4:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል እንደሚቋረጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ደምበኞች ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ተቋሙ አሳስቧል።
@TikvahethMagazine
25.6K views15:46