Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.28K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-04-10 12:12:08
#አዲስአበባ: የ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በፎቶ

አቤል ጋሻው

@TikvahethMagazine
28.5K views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 14:38:51
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የተማሪዎችን አጠቃላይ መረጃ የሚይዝና ጥራት አመላካች አሃዶችን የሚተነትን ኢ ስኩል ሶፍትዌር በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ሊሆን ነው።

ሥርዓቱ በሁሉም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን ሲጠቆም በትምህርት ቤቶች ከመረጃ አያያዝና ትንተና ጋር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲሁም ለተማሪዎች ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ለማቅረብ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መሟላታቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ገልፀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

@TikvahethMagazine
14.3K viewsedited  11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:01:33
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ በኋላ 9ኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ህብረት አባል ሀገር ልትሆን ነው

ኢትዮጵያ ፥ ሶማሊያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ህብረት (EAC) ከገባች ከጥቂት ወራት በኋላ ኢትዮጵያም ህብረቱን ለመቀላቀል የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተሰምቷል።

የህብረቱ ፀሐፊ ማሎንዛ የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ መሪዎች ንግግር የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን በቅርቡም ኢትዮጵያ የህብረቱ አባል እንደምትሆን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አባል ለመሆን ከጫፍ ከመድረሷ ጋር ተያይዞ የህብረቱ አጋር ሀገራት ወሳኝ የሚባሉ ፖሊሲዎችን በማውጣት፥ በዚህ አመት መጨረሻ በህብረቱ የገንዘብ ፖሊሲ መሰረት የጋራ መገበያያ ገንዘብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሀገራት ብሩንዲ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ሲሆኑ ሶማሊያና ኢትዮጵያ 8ኛ እና 9ኛ አባል ይሆናሉ ተብሏል።

@TikvahethMagazine
17.6K viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 12:11:40
ባለፉት 9 ወራት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦን ላይን ተሠጥቷል ተባለ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1,816,041 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን መሰጠቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ በኦን ላይን እና በባክ ኦፊስ 2,034,787 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች መሰጠቱ ሲገለፅ ከተሠጡት አገልግሎቶች ውስጥ አዲስ የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ ማሻሻያ፣ የንግድ ስም እንዲሁም መሠል 19 የተለያዩ አገልግሎቶችን ይገኙበታልም ተብሏል።

@TikvahethMagazine
17.9K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 11:40:01
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የቡና ቅጠል በሸታን የሚለይ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን ገለፀ

የቡና ቅጠል ምስልን በመጠቀም ብቻ የቡና ቅጠል በሸታን ለመለየት፣ የጉዳት መጠንን ለማወቅ የሚያስችል ኮፊኔት የተሰኘ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር መስክ በሆነው ኮምፒውተር ቪዥን መበልፀጉ ተሰምቷል። ቴክኖሎጂው ሶስት የቡና ቅጠል በሽታዎችን መለየት ይችላልም ነው የተባለው።

@TikvahethMagazine
17.3K viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 11:39:36
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያልተቀናጀ አሰራር ድርጅቱ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አጥቷል ተባለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በዋናነትም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት ባለመሥራቱ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014/15 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮጀክት አፈጻጻም የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን በትላትናው እለት ገምግሟል።

ኃይል ሲቋረጥ በድርጅቱ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መካከል ኃላፊነት ወስዶ ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ በእቅድ ላይ የተመሠረተ ሥራ አልተሠራም ሲባል ፤ በዚህም ከአገልግሎቱ ጋር በቅንጅት ባለመሥራቱ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገሮች ባለመሸጡ በአማካኝ 1 ቢሊዮን 271 ሚሊዮን 244 ሺህ 977 ብር ገቢ አለመገኘቱን በ2013 ዓመታዊ ሪፖርት መገለፁ በኦዲት ሪፖርቱ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በተለያዩ ጊዜያት በመገናኘት የእቅድም ሆነ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በቅንጅት ተወያይቶ ይሠራል ሲሉ ነገር ግን ቋሚነት ያለው የተፈረመ ሰነድ በሁለቱ ድርጅቶች መካከል እንደሌለ ገልፀዋል። ይህም እንደ ክፍተት የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል። ችግሩ በሁለቱ ተቋማት መገፋፋት የመጣ አለመሆኑንም አስረድተዋል።

Credit : EPA

@TikvahethMagazine
15.4K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 11:39:07
DMC REAL ESTATE
ከ 8% እስከ 25% ልዪ ቅናሽ!!!

በመሃል ከተማ በሚገኝው ነፋሻማ በሆነው በለቡ መብራት ሃይል ከቻድ ኢምባሲ ጎን በ65,395 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ እጅግ ቅንጡ እና ዘመኑ በደረሰበት የአልሙኒየም ፎርምዋርክ ቴክኖሎጂ  በመገንባት ላይ ያለ የጋራ ሂል ሳይድ የመኖሪያ መንደር ከ DMc real estate.

ከሰቱዲዮ 56 ካሬ እስከ 186 ካሬ ባለ 4 መኝታ ቤቶች እና ከ25 ካሬ እስከ 1000 ካሬ ስፋት ያላቸው ሱቆችን ያካተተ

  በውስጡም 5 አሳንሰሮች፣ በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ፣ የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ ፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ፣ ዘመናዊ ኢንተርኮም አገልግሎት፣ የጋራ መናፈሻ፣  የአደጋ ጊዜ መጥሪያ፣ የደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ፣ 24 ሰአት የእንግዳ መቀበያ፣  ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች ያለው።


                    ለበለጠ መረጃ
               +251 922 628 537
               +251 934 475 656
13.1K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 11:39:07
ከ7 እስከ 18 ለሆኑ ልጆች የኦንላይን  ኮዲንግ  ስልጠና

ስልጠና April 13 , 2024 ቅዳሜ ይጀምራል።

ከ7 እስከ 13 ለሆኑ ህጻናት የ6 ሳምንታት የscratch ስልጠና( ጌም እና አኒሜሽን እየሰሩ ነው ሚማሩት)።

ከ14 እስከ 18 ለሆኑት የ website ስልጠና ለ 2 ወር።

የምስክር ወረቀት ያገኛሉ

ክፍያ ለ6 ሳምንት ፕሮግራም 2500 ብር ነው።
ክፍያ ለ 2 ወር ፕሮግራም 3500 ብር ነው።

በቴሌግራም መረጃ ለማግኘት ያግኙን
@koderlabtrainingcenter ወይም በ 0940121072 ይደውሉ።

ይህንን ሊንክ በመጠቀም ሬጅስተር ያርጉ።
https://forms.gle/J3CeN5XE4vQW3MF49
15.2K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 21:52:23
" ባለፉት 9 ወራት በተፈፀመ ስርቆት 22 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ወድቀዋል " #EEP

ባለፉት 9 ወራት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ሽቦ ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈፀመ #ስርቆት 22 ምሰሶዎች መውደቃቸውን እና ከዚህ ውስጥ ሰባቱ በሰሜን ምዕራብ ሪጂን በተፈፀመ ስርቆት የወደቁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።

ባለፉት 9 ወራት በሁሉም ሪጂኖች በሚገኙ የኃይል ማስተላለፈያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ስርቆት እንደተፈፀመ ሲነገር በስርቆት ምክንያት ከወደቁ ምስሶዎች በተጨማሪ ከመሬት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዙ እና በሌሎች ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ደግሞ 13 ምሰሶዎች መውደቃቸው ተጠቁሟል።

እየተባባሰ የመጣው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች አካላት ስርቆት በኦፕሬሽን ሥራው ላይ ፈተና እየሆነ ይገኛል ሲባል የኦፕሬሽንና ጥገና ኃላፊዎች ችግሩ ከመደበኛ ሥራቸው ይልቅ በአስቸኳይ የጥገና ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ እያስገደዳቸው ስለመሆኑ አመልክተዋል።

ወንጀሎቹን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች ቢከናወኑም ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከተቋሙ አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ነው ኃላፊዎቹ ያነሱት። ችግሩን ለመፍታት ተቋሙ ከከፍተኛ የመንግስት አካላት ጋር በመወያየት ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ማስቀመጥ ይኖርበታል ብለዋል። የተንሰራፋው ስርቆት ኃይል ከማቆራረጥ ባለፈ ተቋሙን ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረገው እንደሚገኝም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
24.7K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 20:01:09
የኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ የስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ

በኬንያ ደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ይጨመርልን በማለት የስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጥሪ አቀረቡ፡፡    
                                                                          
ፕሬዝዳንቱ 1500 አዲስ ዶክተሮችን እንደሚቀጠሩ ቃል የገቡ ሲሆን ነገር ግን ሀገሪቱ እየከፈለችው ካለው ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ አኳያ ለህክምና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ አሳውቀዋል፡፡

ከ700 በላይ የህክምና ባለሙያዎችን የወከለው የኬንያ ህክምና ባለሙያዎች ህብረት ከመጋቢት 6 ጀምሮ በሀገሪቱ አዲስ የህክምና ባለሙያዎች እንዲቀጠሩ፤ ደሞዝ እንዲጨመር እና ተያያዥ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ግፊት ለማድረግ የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

@TikvahethMagazine
28.0K viewsedited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ