Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያልተቀናጀ አሰራር ድርጅቱ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አጥቷል ተባለ | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያልተቀናጀ አሰራር ድርጅቱ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አጥቷል ተባለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በዋናነትም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት ባለመሥራቱ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014/15 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮጀክት አፈጻጻም የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን በትላትናው እለት ገምግሟል።

ኃይል ሲቋረጥ በድርጅቱ እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መካከል ኃላፊነት ወስዶ ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ በእቅድ ላይ የተመሠረተ ሥራ አልተሠራም ሲባል ፤ በዚህም ከአገልግሎቱ ጋር በቅንጅት ባለመሥራቱ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገር ውስጥ እና ለጎረቤት ሀገሮች ባለመሸጡ በአማካኝ 1 ቢሊዮን 271 ሚሊዮን 244 ሺህ 977 ብር ገቢ አለመገኘቱን በ2013 ዓመታዊ ሪፖርት መገለፁ በኦዲት ሪፖርቱ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በተለያዩ ጊዜያት በመገናኘት የእቅድም ሆነ የኦፕሬሽን ሥራዎችን በቅንጅት ተወያይቶ ይሠራል ሲሉ ነገር ግን ቋሚነት ያለው የተፈረመ ሰነድ በሁለቱ ድርጅቶች መካከል እንደሌለ ገልፀዋል። ይህም እንደ ክፍተት የሚወሰድ ይሆናል ብለዋል። ችግሩ በሁለቱ ተቋማት መገፋፋት የመጣ አለመሆኑንም አስረድተዋል።

Credit : EPA

@TikvahethMagazine