የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የቡና ቅጠል በሸታን የሚለይ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን ገለፀ የቡና ቅጠል ምስልን በመጠቀም ብቻ የቡና ቅጠል በሸታን ለመለየት፣ የጉዳት መጠንን ለማወቅ የሚያስችል ኮፊኔት የተሰኘ መተግበሪያ እያበለፀገ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት ነው የተባለው ይህ መተግበሪያ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር መስክ በሆነው ኮምፒውተር ቪዥን መበልፀጉ ተሰምቷል። ቴክኖሎጂው ሶስት የቡና ቅጠል በሽታዎችን መለየት ይችላልም ነው የተባለው። @TikvahethMagazine 17.3K viewsedited 08:40