Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 9 ወራት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦን ላይን ተሠጥቷል ተ | TIKVAH-MAGAZINE

ባለፉት 9 ወራት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦን ላይን ተሠጥቷል ተባለ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1,816,041 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን መሰጠቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ በኦን ላይን እና በባክ ኦፊስ 2,034,787 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች መሰጠቱ ሲገለፅ ከተሠጡት አገልግሎቶች ውስጥ አዲስ የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ ማሻሻያ፣ የንግድ ስም እንዲሁም መሠል 19 የተለያዩ አገልግሎቶችን ይገኙበታልም ተብሏል።

@TikvahethMagazine