Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ በኋላ 9ኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ህብረት አባል ሀገር ልትሆን ነው ኢት | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ በኋላ 9ኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ህብረት አባል ሀገር ልትሆን ነው

ኢትዮጵያ ፥ ሶማሊያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ህብረት (EAC) ከገባች ከጥቂት ወራት በኋላ ኢትዮጵያም ህብረቱን ለመቀላቀል የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተሰምቷል።

የህብረቱ ፀሐፊ ማሎንዛ የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ መሪዎች ንግግር የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን በቅርቡም ኢትዮጵያ የህብረቱ አባል እንደምትሆን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አባል ለመሆን ከጫፍ ከመድረሷ ጋር ተያይዞ የህብረቱ አጋር ሀገራት ወሳኝ የሚባሉ ፖሊሲዎችን በማውጣት፥ በዚህ አመት መጨረሻ በህብረቱ የገንዘብ ፖሊሲ መሰረት የጋራ መገበያያ ገንዘብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሀገራት ብሩንዲ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ ሲሆኑ ሶማሊያና ኢትዮጵያ 8ኛ እና 9ኛ አባል ይሆናሉ ተብሏል።

@TikvahethMagazine