#AddisAbaba በአዲስ አበባ የተማሪዎችን አጠቃላይ መረጃ የሚይዝና ጥራት አመላካች አሃዶችን የሚተነትን ኢ ስኩል ሶፍትዌር በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ሊሆን ነው። ሥርዓቱ በሁሉም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን ሲጠቆም በትምህርት ቤቶች ከመረጃ አያያዝና ትንተና ጋር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲሁም ለተማሪዎች ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ለማቅረብ እድል ይፈጥራል ተብሏል። ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መሟላታቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ገልፀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው። @TikvahethMagazine 14.3K viewsedited 11:38