Get Mystery Box with random crypto!

' ባለፉት 9 ወራት በተፈፀመ ስርቆት 22 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ወድቀዋል | TIKVAH-MAGAZINE

" ባለፉት 9 ወራት በተፈፀመ ስርቆት 22 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ወድቀዋል " #EEP

ባለፉት 9 ወራት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ሽቦ ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈፀመ #ስርቆት 22 ምሰሶዎች መውደቃቸውን እና ከዚህ ውስጥ ሰባቱ በሰሜን ምዕራብ ሪጂን በተፈፀመ ስርቆት የወደቁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።

ባለፉት 9 ወራት በሁሉም ሪጂኖች በሚገኙ የኃይል ማስተላለፈያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው ስርቆት እንደተፈፀመ ሲነገር በስርቆት ምክንያት ከወደቁ ምስሶዎች በተጨማሪ ከመሬት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዙ እና በሌሎች ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ደግሞ 13 ምሰሶዎች መውደቃቸው ተጠቁሟል።

እየተባባሰ የመጣው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች አካላት ስርቆት በኦፕሬሽን ሥራው ላይ ፈተና እየሆነ ይገኛል ሲባል የኦፕሬሽንና ጥገና ኃላፊዎች ችግሩ ከመደበኛ ሥራቸው ይልቅ በአስቸኳይ የጥገና ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ እያስገደዳቸው ስለመሆኑ አመልክተዋል።

ወንጀሎቹን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች ቢከናወኑም ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከተቋሙ አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ነው ኃላፊዎቹ ያነሱት። ችግሩን ለመፍታት ተቋሙ ከከፍተኛ የመንግስት አካላት ጋር በመወያየት ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ማስቀመጥ ይኖርበታል ብለዋል። የተንሰራፋው ስርቆት ኃይል ከማቆራረጥ ባለፈ ተቋሙን ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረገው እንደሚገኝም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine