Get Mystery Box with random crypto!

የኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ የስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ | TIKVAH-MAGAZINE

የኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ የስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ

በኬንያ ደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ይጨመርልን በማለት የስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጥሪ አቀረቡ፡፡    
                                                                          
ፕሬዝዳንቱ 1500 አዲስ ዶክተሮችን እንደሚቀጠሩ ቃል የገቡ ሲሆን ነገር ግን ሀገሪቱ እየከፈለችው ካለው ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ አኳያ ለህክምና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ አሳውቀዋል፡፡

ከ700 በላይ የህክምና ባለሙያዎችን የወከለው የኬንያ ህክምና ባለሙያዎች ህብረት ከመጋቢት 6 ጀምሮ በሀገሪቱ አዲስ የህክምና ባለሙያዎች እንዲቀጠሩ፤ ደሞዝ እንዲጨመር እና ተያያዥ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ግፊት ለማድረግ የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

@TikvahethMagazine