Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Tikvahfamily
Update
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.00K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-04 12:20:03
በሀገራችን ስላምን ለማፅናት፣ ሁላችንም የራሳችን ድርሻ አለን። ለመሆኑ ሰለ አገራችን ሠላም ምን የሚሉት አለ? ስለ አጋራናችሁ  የሰላም ጥሪ መልዕክትስ የሚሰጡን አስተያየት ካለ @Utopiaadd ላይ ያጋሩን። ለሠላም ለመስራት መቼም ረፍዶ አያውቅም!
15.9K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 12:20:03
ከቅርብ አመታት ወዲህ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለትምህርት አሰጣጥ ዘዴ መፍትሄዎችን ማምጣት ችሏል። ተቋማችንም ከዘመኑ ጋር አብሮ በመጓዝ የተለያዩ ቋንቋዎችን  በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እድገት ተማሪና አስተማሪን በቀላል መንገድ በማስተሳሰር መማርን ቀላልና ተደራሽ አድርጎ መቷል።እርሰዎም ፈጥነው በመመዝገብ ፍላጎትዎን ያሳኩ!
   እንግሊዘኛ
   አረብኛ
   አፋን ኦሮሞ
   አማርኛ  ቋንቋን ባሉበት ሆነው ይማሩ!!

ለበለጠ መረጃ፦ 0933666662ወይም
                        0932878889 ይደውሉ

በአካል መምጣት ከፈለጉ
አ.አ፡ቤተል፡ AJ ሞል አራተኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል

  ብራይት የስልጠና ማዕከል
  ለብርሀናማ ህይወት ትክክለኛ ቦታ!!

https://t.me/brighttraining90
18.6K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 23:10:32
#inShort : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ግንባታዎችን በሚመለከት ያስተላለፈው ውሳኔ

@TikvahethMagazine
26.6K viewsedited  20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 20:35:20
የትራፊክ አደጋ መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመሰብሰብ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የመንገድ ደኅንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለመተግበር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

በሀገራችን የሚደርሱ የመንገድ ትራፊክ አደጋዎች ዳታ አያያዝን በቴክኖሎጂ ለማገዝ ጥናትና ሶፍትዌር የማበልፀግ ሂደቱ አልቆ በተግባር ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ቴክኖሎጂው መረጃዎች በአግባቡ ተሰብስበው ፖሊሲዎች እንዲዘጋጁ እና አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ መፍትሄዎችንም ለማስቀመጥ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

@TikvahethMagazine
28.6K views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 17:14:01
ጁምዓና ከተራን ጨምሮ አራት ቀናት ሥራ ዝግ ሆኖ እንዲከበሩ ጥያቄ ቀረበ

ጁምዓ፣ ከተራና ቃና ዘገሊላ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ እንዲሁም የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በዓላት ሥራ ዝግ ሆነው እንዲከበሩ በፓርላማ ጥያቄ መቅረቡን ሪፖርተር አስነብቧል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጤና፣ የሕዝብ በዓላትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የሕዝብ ውይይት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ምሁራንና ሌሎች ተቋማት ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹ ምን ጥያቄ አቀረቡ?

- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በመወከል የተገኙት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ በእስልምና አንድ ሰው 3 ተከታታይ ጁምዓ ካልተገኘ በመናፍቅነት የሚያስፈርጅ ከባድ ጉዳይ በመሆኑ፣ ዓርብ (ጁምዓ) ቀን ሥራ ዝግ እንዲሆን፣ ወይም ደግሞ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ከአምስት ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት ተኩል በአዋጁ መካተት አለበት ብለዋል።

- ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያሪክ የሕግ መምርያ ኃላፊ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት፣ እየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ ሄዶ መጠመቁን የሚያሳየው የቃል ኪዳኑን ታቦት በመያዝ ጥር 10 ቀን የሚከበረው ከተራና ከጥምቀት በኋላ ጥር 12 ቀን የሚከበረው ቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ከሥራ ዝግ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

- በተጨማሪም የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ታስቦ ከመዋል ይልቅ ከሥራ ዝግ ሆኖ መከበር ይገባዋል ያሉት ደግሞ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ናቸው፡፡

የተሰጡ አስተያየቶች ረቂቅ አዋጁን ለማጎልበት እንደሚያግዝ ሲገለፅ፣ አዋጁ ኢትዮጵያውያንን እንዲመስል ዘላቂነት ያለው ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
30.1K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 17:13:16
በወልቂጤ ተጣምረውና ተዋህደው የተወለዱ መንትዮች በተሳካ ቀዶ ህክምና እንዲለያዩ ተደረገ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የተዋሃዱ ወይም የተጣመሩ መንትዮችን በቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ እንዲለያዩ ማድረጉን አስታውቋል።

የቀዶ ህክምናው የተሰራው በሆስፒታሉ የህፃናት ስፔሻሊስት ሃኪም በሆኑት ዶ/ር ሙሉአለም አማረ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የተዋሃዱ ወይም የተጣመሩ መንትዮች ክስተት እርግጠኛ ያልሆነ ፅንስ መከሰትን የሚጠቁም እንደሆነና ባለሙያው ሞኖዚጎቲክ መንትዮች የሚፈጠሩት ከአንድ ቀደምት ፅንስ ክፍፍል እና መለያየት እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህ መሰረት በተደረገው የቀዶ ህክምና አገልግሎት አንደኛው ህጻን በህይወት የተወለደ ሲሆን ህፃኑ በተወለደ በአምስተኛ ቀኑ ከራሱ ጋር ተጣብቆ የተወለደውንና በህይወት ከሌለው መንትያ ጋር በመለየት በህይወት የተረፈው ህጻን በሰላም ወደ ቤቱ መመለሱን ባለሙያው ገልጸዋል።

ይህን መሰል ክስተት የስርጭት መጠኑ ቀደም ሲል ከ50,000 እስከ 100,000 ከሚወለዱ ሕፃናት መካከል በአንዱ የሚከሰት ሊሆን እንደሚችል ዶ/ር ሙሉአለም አማረ አብራርተዋል።

@TikvahethMagazine
26.6K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 17:12:57
Stay Connected to DStv Gojo.

Join us, Reconnect and Upgrade your package now!

Click on the link below!

https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #Gojo #ጎጆ
25.8K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 17:12:56
በሀገራችን ስላምን ለማፅናት፣ ሁላችንም የራሳችን ድርሻ አለን። ለመሆኑ ሰለ አገራችን ሠላም ምን የሚሉት አለ? ስለ አጋራናችሁ  የሰላም ጥሪ መልዕክትስ የሚሰጡን አስተያየት ካለ @Utopiaadd ላይ ያጋሩን። ለሠላም ለመስራት መቼም ረፍዶ አያውቅም!
24.2K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 12:02:33
ኬንያ የግል የኤሌክትሪክ ሀይል አስመጪዎች ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ሀይል ገዝተው እንዲሸጡ ልትፈቅድ ነው ተባለ

ኬንያ በሀገሪቱ በቂ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት እና የሀይል ዋጋ ታሪፍ እንዲቀንስ በማሰብ በሀገሪቱ የሚገኙ የግል የኤሌክትሪክ ሀይል ድርጅቶች ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ሀይል ገዝተው እንዲሸጡ ልትፈቅድ መሆኑ ተነግሯል።

ኬንያ ይህንን ለማድረግ ያቀደችው የኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለስልጣን (ኢፕራ) በሀገሪቱ ሀይል የሚሸጡ ነጋዴዎችን በማብዛት ለተጠቃሚው ታሪፍ እንዲቀንስ የሚያስችል ሃሳብ በማቅረቡ እንደሆነ ተጠቅሷል። ባለስልጣኑ የኢነርጂ ኤሌክትሪክ ሃይል ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ማውጣቱም ተሰምቷል።

ከዚህ ቀደም ከውጭ ሀገር የኤሌክትሪክ ኃይል ሻጮች ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል የመግዛት ስምምነትን መፈረም የሚችለው የኬንያ መንግስት ብቻ ነው። ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬንያ እየሸጡ ያሉ ሀገራት መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
29.2K viewsedited  09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 11:52:51
#IMF

የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ልዑክ ቡድን ተቋሙ ለኢትዮጵያ ሊያደርገው ባቀደው የብድር ድጋፍ ዙሪያ ለመነጋገር ከመጋቢት 10 ጀምሮ በአዲስ አበባ ያደረገውን የውይይት ጊዜ ማጠናቀቁን አስታውቋል።

በአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የተቋሙ ልዑክ የውይይት ጊዜውን ካጠናቀቀ በኋላ በውይይቱ አይኤምኤፍ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ማሻያ መርሃ ግብር ለመደገፍ በሚያስችልበት ሁኔታ ብዙ ለውጥ መታየቱን ገልጿል።

የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም እና ዓለም ባንክ በቀጣይ ወር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ድጋፉን አስመልክቶ ውይይቱ የሚቀጥል መሆኑንም ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
28.7K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ