Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-11 17:16:34
"በትምህርት ቤት ውስጥ ያልተጀመረ ነገር የትም አይደርስም" አቶ ክብረት አበበ የጠብታ አንቡላንስ መስራች

በኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዘርፍ ፈር ቀዳጅ የሆነው የጠብታ አንቡላንስ አዲስ ባቋቋመው ፋውንዴሽን በኩል በአዲስ አበባ ለሚገኙ 10 ትምሀርት ቤቶች በዚህ ዓመት የመንገድ ደኅንነት እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የጠብታ አንቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ማክሰኞ ዕለት በህብረት ፍሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ሐሙስ ደግሞ ኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ሥራውን በማስተዋወቅ በይፋ አስጀምረዋል።

አቶ ክብረት አበበ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ?

ጠብታ አንቡላንስ ከምናተርፈው ቀንሰን የማኅበረሰብ አገልግሎት ለማከናወን ፋውንዴሽን (East Afric Emergency Service Foundation) አቋቁመናል። በዚህ ብዙ ሥራዎችን ለመስራት አቅደናል። ይህ ፕሮጀከት አንዱ ነው።

ተማሪዎች ትን እንኳን ቢላቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው መማር አለባቸው። በመኪና አደጋ የወደቀን ሰው በቸልተኝነት ማንሳት ከአደጋው በላይ ገዳይ መሆኑን ማስተማር እንፈልጋለን። በአደጋ የወደቀን ሰው ማንሳት ሳይንስ ነው።

ይህ እውቀት በትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተካቶ መሰጠት ያለበት ነው። ይህ ባይሆን እንኳን ከመደበኛው ትምህርት ውጪ መሰጠት አለበት። ለዚህ ትብብር ያስፈልጋል፤ እንስጥ ስንልም መቸገር የለብንም። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይህንን ጥረታችንን አይቶ ተባብሮናል።

በትምህርት ቤት ውስጥ ያልተጀመረ ነገር የትም አይደርስም። ሰው ጥሩ ሀኪም የሚሆነው በፍቅር ሲያክም ነው ያንን ፍቅር የምትጨምረው ደግሞ በህጻናት ላይ ነው።

እነዚህ ት/ቤት ቤቶች እኔ የተማርኩባቸው ናቸው፤ ተመልሼ ላስተማረኝ ትምህርት ቤት መስጠት ስላለብኝ ነው ከዚህ የጀመርኩት።

በኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ የኮንስትራክሽን ሳይቶች አሉ ተብሎ ይታሰባል። ብዙ ለአደጋ ተጋላጭ ሆኑ የቀን ሰራተኞች በዚህ ሥራ ይሳተፋሉ እነሱን ለማስተማር ተንቀሳቃሽ 100 ኢንች ቴሌቪዥን የተገጠመለት መኪና ሥራ አስጀምረናል። ከስራ በፊት ለ30 ደቂቃ እነሱን ማስተማር እንፈልጋለን።

* በሁለቱም ት/ቤቶች ሮተሪያኖች የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ ታንብብ ኢኒሼቲቭ ለትምህርት ቤቶቹ መጽሐፍት አበርክተዋል።

@TikvahethMagazine
21.1K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 17:16:16
ስልኮትን ለመቀየር አስበዋል?

  አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/phonehub27

0996544119

inbox @kidaa3535

አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
17.2K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 17:16:15
አስደሳች ዜና ULTRA DATA RECOVERY እንባላለን:
አስፈላጊ የሚሉት 🅳 🅲🅤🅼🅴🅽🆃
                           🅵🅸🅻🅴(video, image, pdf, doc, excel,)
ጠፍቶ ተጨንቀዋል ?
እንግዲያውስ መፍትሄ ይዘን መተናል
ከማንኛውም 𝙨𝙩𝙤𝙧𝙖𝙜𝙚 𝙙𝙚𝙫𝙞𝙘e ማለትም
𝙝𝙖𝙧𝙙𝙙𝙞𝙨𝙠
𝙨𝙨𝙙
𝙢𝙚𝙢𝙤𝙧𝙮
𝙛𝙡𝙖𝙨𝙝 drive
የጠፋ,𝙘𝙤𝙧𝙧𝙪𝙥𝙩 ያረጉ,𝙙𝙚𝙩𝙚𝙘𝙩 አላረግ ካሉ,partition loss, system crush ካደረጉ storage device ላይ ..... በአስተማማኝ ሁኔታ ፋይልዎን እንመልሳለን .
በተጨማሪም bitlock protected, encrypted data recover እንደምናደርግ ስንገልፅ በደሰታ ነው::
አደራሻ: ከ ቦሌ ወደ 22 በሚወስደው መንግድ አዲሱ ስታዲየም ፊትለፊት HELMES TRADING ሀንፃ 4አኛ ፎቅ::
ይደውሉ:- +251940726275 ወይም https://www.tiktok.com/@ultra.data.recovery?_t=8kukrL3KVUM&_r=1
17.4K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 14:52:10
ደስታ የሚል መጠሪያ ያላት ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም የስታርት-አፕ አውደርዕይ ለዕይታ ቀረበች

ደስታ የሚል መጠሪያ ያላት ሮቦት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮ ቴሌኮም፣ አይኮግላብ እና ራይድ ቴክኖሎጂስ ትብብር በሳይንስ ሙዚየም ለሕዝብ ዕይታ ቀረበች።

ሮቦቷ ሳይንስ መዚየም ላይ ከተመልካች ለሚቀርብላት ጥያቄም በሀገር ውስጥና በውጭ ቋንቋዎች ምላሽ እየሰጠች እንደሆነ ሲገለፅ በሳይንስ ሙዚየም ኹነት እያቀረበች ትገኛለች ተብሏል።

Source : EAII

@TikvahethMagazine
21.4K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 13:24:30
ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ የሚላኩ የአበባ ምርቶች ያለ ቀረጥ ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ ፈቀደች

ብሪታኒያ ከኢትዮጵያ እና ከምስራቅ አፍሪካ  ሀገራት ጋር የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ ርካሽና ተመጣጣኝ ለማድረግ በማለም ከቀጠናው ሀገራት የሚላኩ አበቦች ትቆርጥ የነበረውን የቀረጥ ክፍያ ለ2 አመት አነሳች።

ከዚህ በፊት የአበባ ምርቶች ወደ ብሪታኒያ ሲገቡ 8 በመቶ ቀረጥ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የቀረጥ ክፍያው የሚነሳ መሆኑን ብሪታኒያ ባወጣችው መግልጫ አስታውቃለች።

ይህ የ 8 በመቶ የቀረጥ ክፍያ ከመላው ዓለም የአበባ ምርቶችም ወደ ሀገሪቱ የሚልኩ ሀገራትን ተጠቃሚ ያደርጋል ሲባል ነገር ግን ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ላሉ ዋና የአበባ አምራች ሀገራት ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት 23 በመቶ የሚሆነውን የአበባ ምርት ወደ ውጪ የምትልክ ሲሆን በአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ የአበባ አምራች ነች። በ 2023 ወደ ብሪታኒያ  የላከችው የአበባ ንግድ ዋጋ 12.6 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሆነም የብሪታኒያ መንግስት አሳውቋል።

@TikvahethMagazine
22.7K viewsedited  10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:21:08
" ያለቡና መኖር አንችልም " የኢትዮጵያ ቡና አምራች አርሶ አደሮች

የአውሮፓ ህብረት በ 2025 ተግባራዊ ሊያደይርገው ያቀደው የፀረ ደን ጭፍጨፋ ደንብ (EUDR)  የኢትዮጵያ የአነስተኛ የቡና ምርት አምራች ገበሬዎች ህይወት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ቡና አምራቾች ገለፁ።

የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የኑ ምርቶች #ብቻ ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት እንዲገቡ በሚፈቅደው የ EUDR ደምብ ምክንያት ከአውሮፓ ሀገራት የሚመጣው የቡና አቅርቦት ጥያቄ እየቀነሰ መሆኑን የከፋና ሲዳማ ቡና አምራቾች ለ ዘጋርዲን ተናግረዋል።

እንደ ህጉ መሰረት በአውሮፓ ህብረት ገበያ ላይ መቅረብ የሚችሉት ምርቶች ህጋዊ የሆኑ፣ ከደን መጨፍጨፍና መራቆት ጋር ያልተገናኙ ምርቶች ብቻ ናቸው። ከዚህ ጋር ተያይዞ " መስፈርቶቹን ማሟላት ትላልቅ ቴክኖሎጂ እና ብዙ የሰው ሀይል ይፈልጋል። እኛ ደግሞ ይህንን የለንም " ሲሉ የከፋ ቡና አምራች ህብረት ሀላፊ ገልፀዋል።

ከአውሮፓ ህብረት 27 አባል ሀገራት 20 ያህሉ የፀረ-ደን መጨፍጨፍ ህጉ እንዲዘገይ እና አነስተኛ የደን መጨፍጨፍ አደጋ አለባቸው ተብለው በሚታሰቡ አገሮች የሚገኙ አምራቾችን ታሳቢ በማድረግ ከህጉ ነፃ እንዲያደረጉ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ህብረቱን ጠይቀዋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በአይቮሪ ኮስት የሚገኙ የካካዎ አምራቾች እንዲሁም የፓልም ዘይት አምራቿ ኢንዶኔዥያ የህጉ ተፈፃሚነት እንዲዘገይ ይፈልጋሉ ተብሏል።

ይህንን አስመልክቶ ከቀናት በፊት የአውሮፓ የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ቨርጂኒጁስ ሲንኬቪሲየስ ህጉ ከ2025 መጀመሪያ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ የአውሮፓ ህብረት ህጉ ተግባራዊ የሚደረግበት ጊዜ እንደማይራዘም ለሮይተርስ ተናግረዋል።

@TikvahethMagazine
21.9K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:20:10
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ባለአክሲዮኖች ምን አይነት መብት እንደሚኖራቸው የሚወስን ድልድል አያደረገ ነው

ከ48 የኢትዮጵያ እና የውጭ ሀገር ተቋማት 1.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የኢንቨስተሮቹን የድርሻ ድልድል በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ዶይቸ ቨለ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሰነደ-ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር ሚካኤል ሐብቴ “አሁን የድርሻ ድልድል እያደረግን ነው። ገና አልተጠናቀቀም” ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ ሣምንት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሒደት በኩባንያው ድርሻ የገዙ ባለ አክሲዮኖች ምን አይነት መብት እንደሚኖራቸው የሚወስን ነው ተብሏል።

ከካፒታል ገበያው ድርሻ ከገዙ ሦስት የውጪ ሀገር ኢንቨስተሮች አንዱ የሆነው የናይጄሪያው ኤክስቼንጅ ግሩፕ፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ቴሚ ፖፖላ የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የቦርድ አባል እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ 25 በመቶው ድርሻ የመንግሥት ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና 4 የመንግሥት ተቋማት ለ25 በመቶው ድርሻ 225 ሚሊዮን ብር ከፍለዋል። የተቀረው 75 በመቶ ድርሻ በሀገር ውስጥ የግል ዘርፍ እና የውጭ ባለሀብቶች መያዙ ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
18.5K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:19:43
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፦ Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ለኢንትራንስ ፈተና ዝግጅታቹን አጠናክሩ፡፡ አፕሊኬሽኑ

ከ9 - 12ኛ ክፍል የኢንትራንስ እና የማትሪክ ፈተናዎችን ከነመልሳቸው እና ከነማብራሪያቸው የያዘ ነው፡፡
የ8 ዓመት የኢንትራንስ ፈተና ከ2008 - 2015ዓም የያዘ ሲሆን በተጨማሪ የ3ዓመት የማትሪክ ፈተና ከ2008 - 2010ዓም ይዟል፡፡
ጥያቄዎችን በየክፍሉ እና በየምእራፉ ከፋፍሎ ያስቀመጠ ነው፡፡

ከ300,000 በላይ ተማሪዎች የሚጠቀሙት አፕሊኬሽን ሲሆን ፤ አፕሊኬኑን ለመጠቀም ከታች ካለው ሊንክ ዳውንልድ ያድርጉ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
18.2K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:19:43
DMC REAL ESTATE
ከ 8% እስከ 25% ልዪ ቅናሽ!!!

በመሃል ከተማ በሚገኝው ነፋሻማ በሆነው በለቡ መብራት ሃይል ከቻድ ኢምባሲ ጎን በ65,395 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ እጅግ ቅንጡ እና ዘመኑ በደረሰበት የአልሙኒየም ፎርምዋርክ ቴክኖሎጂ  በመገንባት ላይ ያለ የጋራ ሂል ሳይድ የመኖሪያ መንደር ከ DMc real estate.

ከሰቱዲዮ 56 ካሬ እስከ 186 ካሬ ባለ 4 መኝታ ቤቶች እና ከ25 ካሬ እስከ 1000 ካሬ ስፋት ያላቸው ሱቆችን ያካተተ

  በውስጡም 5 አሳንሰሮች፣ በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ፣ የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ ፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ፣ ዘመናዊ ኢንተርኮም አገልግሎት፣ የጋራ መናፈሻ፣  የአደጋ ጊዜ መጥሪያ፣ የደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ፣ 24 ሰአት የእንግዳ መቀበያ፣  ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች ያለው።


                    ለበለጠ መረጃ
               +251 922 628 537
               +251 934 475 656
20.3K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 12:12:08
#አዲስአበባ: የ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በፎቶ

አቤል ጋሻው

@TikvahethMagazine
28.5K views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ