Get Mystery Box with random crypto!

ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የስራ ርክክብ | TIKVAH-MAGAZINE

ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የስራ ርክክብ ተደረገ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የሥራ ርክክብ መደረጉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የጥገና ሥራውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በመጠበቅ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን ተከትሎ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የጠቆሙ ሲሆን የጥገና ሥራውም በተቀመጠለት የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡

@TikvahethMagazine