Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰብ የነበረበትን ከ850 ሚሊዮን በላይ ብር እንዳልሰበሰ | TIKVAH-MAGAZINE

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰብ የነበረበትን ከ850 ሚሊዮን በላይ ብር እንዳልሰበሰበ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከ 5 እስከ 10 ዓመት ባለው ጊዜ ዉስጥ ሰብስቦ ወደ መንግስት ካዝና ማስገባት የነበረበትን 850 ሚሊዮን 911 ሺህ 237 ብር እንዳልሰበሰበ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የ2014/15 በጀት ዓመት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ላይ በተወያየበት ወቅት ነው። የኮርፖሬሽኑ የግብርና ኬሚካሎች፣ የእንስሳት መድኃኒትና የሌሎች ዘርፎች አፈጻጸም ዝቅተኛ እንደሆነም ተጠቁሟል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም በኦዲት ሪፖርቱ የተጠቀሱ ግኝቶች ለማስተካከል የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰደ እንደሚገኝ ሲገልፁ ኮርፖሬሽኑ በያዛቸው ቦታዎች ላይ የሚፈለገውን የልማት ስራ እያከናወነ ባለመሆኑም በክልሎች የወሰዳቸውን መሬቶች እስከ መቀማት መድረሱም ተመላክቷል።

@TikvahethMagazine