Get Mystery Box with random crypto!

በኬንያ በተከሰተው ከባድ ጎርፍ በትንሹ 32 ሰዎች ሞተው ከ40 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተነገረ | TIKVAH-MAGAZINE

በኬንያ በተከሰተው ከባድ ጎርፍ በትንሹ 32 ሰዎች ሞተው ከ40 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተነገረ

በኬንያ በተከሰተው ከባድ ጎርፍ በትንሹ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ የሚበልጡት ደግሞ ዝናቡ ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለመፈናቀል መገደዳቸው ተገልጿል።

በርዕሰ ከተማዋ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን በዚህ ከባድ ጎርፍ ምክንያት 15 ሰዎች ቆስለው፣ 1ሺ የሚጠጉ እንስሳትን እንደሞቱና በሺዎች ሄክታር ላይ ያረፉ ሰብሎችን መውደማቸው ተገልጿል። በሚቀጥሉት ቀናትም በመላ ሀገሪቱ መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ ይጠበቃልም ነው የተባለው።

@TikvahethMagazine