Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 94

2022-05-12 08:27:31
160 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘችው ባለሙያ ክስ ተመሰረተባት

ዐቃቤ ህግ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት መኔጅመንት ባለሙያ ሆና ስትሰራ 160 ሺ ብር ጉቦ በመቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል በፈፀመች ግለሰብ ላይ ክስ መስርቷል::

ወ/ሮ ሃብታምነሽ ሊሞና የተባለችው ተከሳሽ የሙስና ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10 (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፏ ነው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባት።

ተከሳሿ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 በተበዳይ ስም ተመዝግቦ ይገኝ የነበረ ይዞታ በሽያጭ ወደ 4ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በመተላለፉ የሥም ዝውውር እንዲደረግ ለጽ/ቤቱ በቀረበው የአገልግሎት ጥያቄ መሰረት አስፈላጊ መስፈርቶች ሁሉ ተሟልተው እያለ ሚያዝያ 03 ቀን 2014 ዓ.ም የሥም ዝውውር ከተፈጸመ በኋላ ገዢዎችን በመወከል ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን “ካርታው ተሰርቷል ገንዘብ ካላመጣህ ግን ወጪ አድርገን አንሰጥህም” በማለት 160,000 ብር ጉቦ በመጠየቅና ስትቀበልም እጅ ከፍንጅ የተያዘች በመሆኑ በፈፀመችው ጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባታል ፡፡

ተከሳሿ ትላንት ግንቦት 03/2014 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት ቀርባ የክስ ቻርጅ አንዲደርሳት ከተደረገ በኋላ ክሱ በንባብ ተሰምቷል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የምታቀርበው የክስ መቃወሚያ ካለ ለመጠባበቅ ለግንቦት 05/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰቷል ።።

ፍትሕ ሚ/ር

• @ThinkAbyssinia •
8.9K views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:30:43
የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በመቀለ ምን ይመስላል

በጦርነት እና አገዳ ውስጥ ባላችው ትግራይ ክልል አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሕዝቡን ኑሮ እያቃወሰዉ መሆኑም ተዘግቧል።

ዶቼቬሌ እንደዘገበው ከሆነ መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ)
ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል። የፉርኖ ዱቄት፣ የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ ሲል ዘግቧል።

የዚያኑ ያክል እዚያዉ ትግራይ
የሚመረቱ እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ዋጋ ብዙ ለዉጥ አላሳየም ባንፃሩ የከብትና የስጋ ዋጋ ግን ቀንሷል ተብሏል።

ዶቼቬሌ

• @ThinkAbyssinia •
10.1K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 18:46:20
ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በእጅጉ መባባሳቸውን ለፓርላማው ባቀረበው የ9 ወራት ሪፖርት ገለፀ

ጸጥታ ኃይሎች የሚፈጽሙት ከፍርድ ውጭ ግድያ፣ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀም፣ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዘፈቀደ እስር፣ የተራዘመ የቅድመ-ክስ እስር፣ ባንዳንድ የእስር ቦታዎች ያለ ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ የሕጻናት ሕገወጥ እስር እና ጋዜጠኞችን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችንና የማኅበረሰብ አንቂዎችን አስገድዶ መሰወር ተደጋግሞ መከሰቱን ኮሚሽኑ ገልጧል።

ከሰሜኑ ጦርነት፣ ከብሄር ማንነት፣ ራስን በራስ ከማስተዳደር፣ ከአስተዳደር ወሰንና ከሐይማኖት ጋር የተያያዙ ግጭቶች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስከተላቸውን ኮሚሽኑ ጨምሮ ጠቅሷል።

wazema radio

• @ThinkAbyssinia •
10.6K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 20:58:56
በሰሜን ህንድ በቡድን ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል ብላ ለመክሰስ ፖሊስ ጣቢያ የሄደችው የ13 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መደፈሯ ቁጣን ቀስቅሷል።

አሁን ላይ ታዳጊዋን የደፈረው ፖሊስ ከስራው የተገደ ሲሆን ፤ በቁጥጥር ስርም ውሏል።

ታዳጊዋ ባለፈው ወር በ4 ወንዶች መደፈሯን ተናግራለች፡፡ የታዳጊዋ የመደፈር ዜና በመላ ህንድ ትልቅ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።

የታዳጊዋ ወላጅ ባቀረቡት ክስ፤ አራቱ ወንዶች ሴት ልጃቸውን የደፈሯት ለአራት ቀናት ያክል ማደያ ወደ ተባለ ግዛት ወስደው እቤት ውስጥ በመዝጋት ነበር ብሏል፡፡

አራቱም ወንዶች ለአራት ቀናት ከደፈሯት በኋላ ወደ መኖሪያ አከባቢዋ መልሰው ጥለዋት መሰወራቸውንም ነው ወላጅ አባቷ የገለጹት፡፡

በሚቀጠለው ቀን ታዳጊዋ ከአክስቷ ጋር በመሆን ክስ ለመመስረት ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደች ቢሆንም፤ በፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ እንደተደፈረች ኤን-ዲቲ-ቪ የተባለ የህንድ ቻናል ዘግቧል፡፡

ዜናውን ተከትሎ በግዛቱ ያሉትን ህጎች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው በመነገር ላይ ያለው፡፡

የህንድ ኮንግረስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፕሪያንካ ጋንዲ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ‘‘ ፖሊስ ጣቢያዎች ለሴቶች ደህንነት አስተማማኝ ካልሆኑ ፤ ሴቶች ታዲያ የት ሄደው ይከሳሉ? ’’ የሚል ትችት አዘል መልእክት አጋርቷል፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ /ND TV

• @ThinkAbyssinia •
5.4K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 19:12:37
የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተገደሉ

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የደራሼ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጆበርና አሰፋ በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።ሀላፊው የተገደሉት ያለፈው ቅዳሜ ማለዳ ላይ ሲሆን፤የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንደተናገሩት ከአካባቢው ባለስልጣን ግድያ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአካባቢው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣት ላይ ግድያ ሲፈፀም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው በመጋቢት ወር በሰገን ወረዳ በኮንሶ ዞን ዙሪያ ወረዳ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ገረሙ ገለቦ በአንድ ሆቴል ውስጥ ከጓደኞቻቸው ጋር ሲመገቡ በጥይት መገደላቸው ታውቋል።

[DW]

• @ThinkAbyssinia •
7.0K viewsedited  16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 18:18:48
የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የ 7.2 ሚሊዮን ቤቶች አቅድ በዝርዝር ሲታይ

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በሪል ስቴት የልማት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ትላንት ማክሰኞ ሚያዝያ 25፤ 2014 ባደረጉት ንግግር፤ መንግስት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 7.2 ሚሊዮን ቤቶች በከተማ እና በገጠር ለመገንባት አቅዶ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል። በከተሞች ለመገንባት ከተያዘው 4.4 ሚሊዮን ቤት የግል ሴክተሩ 80 በመቶውን ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም በእቅድ የያዛቸውን የቤት ልማት ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መጨረስ አለመቻሉን የታዘቡ ባለሙያዎች፤ በሚኒስትሯ የተገለጸው እቅድ ተግባራዊነት ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ሲገልጹ ተስተውለዋል። ባለሙያዎቹ እቅዱ “ከምናብ የዘለለ” አለመሆኑን በቁጥር ጭምር አስደግፈው ቢሞግቱም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ዓመት ይፋ ያደረገው የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ ግን ከሚኒስትሯ ገለጻ ጋር የተስማማ አሃዝን አስቀምጧል።

በልማት እቅዱ መሰረት፤ ከ2013 እስከ 2022 ባሉት አስር ዓመታት ውስጥ በመላ ሀገሪቱ 7,800,000 ገደማ የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ። ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ ውስጥ 4.4 ሚሊዮኑ በከተማ፣ ወደ ሶስት ሚሊዮን ገደማ የሚጠጉት ደግሞ በገጠር ማዕከላት እንዲገነቡ መታቀዱን ሰነዱ ያመለክታል።


(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
• @ThinkAbyssinia •
7.3K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 18:03:28 #ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታው ከተጠበቀው በታች መሆኑ ተገለፀ።

በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር አትንኩት መዝገቡ ተፋላሚ ሀይሎች የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፉ ወዲህ ወደ ትግራይ የገባው የሰብዓዊ እርዳታ መጠን ከሚጠበቀው ከ5 በመቶ በታች ነው ብለዋል።
ሀላፊው እንደሚሉት ወደ ትግራይ በየቀኑ አንድ መቶ እርዳታ የጫኑ መኪኖች እንደሚገቡ የሚጠበቅ ቢሆንም፤ ተኩስ አቁሙ ከተደረገ ከአንድ ወር በላይ በሆነ ጊዜ በአጠቃላይ የገቡ እርዳታ የጫኑ መኪኖች ቁጥር 173 ብቻ ናቸው ያሉ ሲሆን በትግራይ በጦርነቱ ምክንያት ከ6 ነጥብ 3 ሚልየን በላይ ዜጎች እርዳታ ፈላጊ ናቸው ሲሉም አክለዋል።
ተስፋ የተጣለበት የሕይወት አድን ሰብዓዊ እርዳታ ስራ በሚፈለገው እናበተጠበቀው ሁኔታ እየሄደ አይደለም ብለዋል።

2፤ኢትዮጵያዊያን ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎችን በጋራ
እንዲቃወሙ አብን ጥሪ አቀረበ፡፡

ፓርቲው ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ ቢጸድቁ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ እና ረቂቅ ሕጎቹን ለማዘጋጀት ያስፈለገበትን ዓላማ በጥንቃቄ እና በተከታታይ መመርመሩን በመግለፅ መግለጫ አውጥቷል፡፡
መግለጫው ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ የከፋ ደም መፋሰስን፣ መቆሚያ የሌለው ግጭትን እና የከፋ አምባገነናዊ ሥርዓትን ከመፍጠር ውጭ የተሻለ መፍትሄ እንደማያመጡ ጠቅሶ በሀገሪቱ በተፈጠረው ችግር ተጎጂዎችን እና ጥፋተኞችን በአንድ የሚያይ በመኾኑ ጉዳቱ ሀገራዊ ነውና ተገቢነቱ ላይ እንደማያምን አብን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ረቂቅ የማዕቀብ ሕጎቹ እንዳይጸድቁ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ አሳስቧል።

3፤ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የወጪ ቅነሳን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ገንዘብ ሚኒሰቴር አሳሰበ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የወጪ ቅነሳ ጉዳይ የ2015 በጀት አመት አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በበጀት አመቱ አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩና ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸው ንብረት ታውቆ በአንድ የመረጃ ቋጥ ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ የክትትልና የቁጥጥር ስርአት እንደሚዘረጋ ገልጸዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒሰቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው የፋይናንስ ስርአቱን በህጉ መሰረት ተግባራዊ ባላደረጉ የተቋማት ኃላፊዎችና ባለሞያዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡

4፤ከሳዑዲ አረብያ 1ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ወደሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች ውስጥ አምስት ህጻናትና 1ሺህ24 ወንዶች መሆናቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል ተብሏል።

5፤ የዩክሬን አርሶ አደሮች የጥይት መከላከያ ለብሰው ወደ እርሻቸው መመለሳቸው ተነገረ።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የስንዴ ልማት ስራዎች የሚከናወኑበት ወቅት ላይ በመሆኑ ስንዴ አምራቾችን እየፈተነ ሲሆን በደቡባዊ ክልል የሚኖሩ የዩክሬን አርሶ አደሮች ማሳቸውን ለማረስ የጥይት መከላከያ እየለበሱ መሆኑ ታውቋል።
ይህ የስንዴ አዝመራ ወቅት እንዳያልፋቸው የሰጉ ዩክሬናዊያን ገበሬዎች የጥይት መከላከያ ጃኬት እና ሄልሜት አድርገው ስንዴ ማልማታቸውን ቀጥለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

6፤ሪያል ማድሪድን መግጠምና መበቀል እፈልጋለው ሲል መሀመድ ሳላ ተናገረ።

የመርሲሳይዱ ክለብ ግብፃዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሞሀመድ ሳላህ ሪያል ማድሪድን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ መግጠም እንደሚፈልግ ገልጿል ።
ሞሀመድ ሳላህ ሲናገር " በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሪያል ማድሪድን መግጠም እፈልጋለው ፤ በ 2018 በፍፃሜው በሪያል ማድሪድ ተሸንፈናል አሁን ከእነሱ ጋር ከተገናኘን የምናሸንፋቸውና የምንበቀላቸው ይመስለኛል" ሲል ተደምጧል ።
በ2018 ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳቱ ይታወሳል። ዛሬ ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን አሸንፎ ለፍፃሜ ከደረሰ ሊቨርፑል የሚገጥም ይሆናል።



• @ThinkAbyssinia •
6.9K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 17:00:56
ተስፈኛው ታዳጊ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገለት


የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ባርሴሎና ከተማ በሚገኘዉ ቢ1 አካዳሚ የመሰልጠን እድልን ላገኘው ታዳጊ ይበልጣል ኤልያስ የአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

የሊጉ የቦርድ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ "የሀገራችን ተጫዋቾች በውጭ ወጥተው እንዲጫወቱ ማድረግ አንደኛው ራዕያችን ነው። ለአንተም የምንመኝልህ ይህንን ዕድል ወደ ፍሬያማ ነገር እንድትለውጠው እና በአውሮፓ ክለቦች ላይ እንድንመለከተህ ነው።" ያሉ ሲሆን: ሌሎች ታዳጊዎች ይህንን መሰል ነገር ይዘው ከቀረቡ አክስዮን ማህበሩ የቻለውን ያክል ለማገዝ ሁሌም በሩ ክፍት ነው ሲሉም አክለዋል።

ከአክሲዮን ማህበሩ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ታዳጊው ይበልጣል ኤሊያስ በበኩሉ "እኔን ያገዙኝን ሰዎች የማስደስተው በትልቅ ደረጃ ራሴን በማብቃት መሆኑን ስለማምን: ጠንክሬ በመስራት በቅርቡ በሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና ዋናው ቡድን ትመለከቱኛላችሁ" ብሏል።


• @ThinkAbyssinia •
7.2K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 16:54:46
በዩክሬን ዶኔስክ ግዛት የሚገኘው የነዳጅ ማከማቻ ጥቃት ደረሰበት


በዶኔስክ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኘው ማኬዬቭካ ከተማ ላይ የዩክሬን ጦር ጥቃት በመፈጸሙ አራት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንኮች መቃጠላቸውን አር ቲ ኒዉስ የአካባቢው ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

እያንዳንዱ ታንክ እስከ 5 ሽህ ኪዩቢክ ሜትር ነዳጅ ሊይዝ እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፣ የዩክሬን መገናኛ ብዙሀን የነዳጅ ማከማቻዉ ጥቃት የተፈጸመበት ለሩሲያ ሃይሎች ነዳጅ እየሸጠ ስለነበር ነዉ ብሏል።

የዩክሬን መከላከያ ሰራዊት በፈጸመው ጥቃት አንድ ሰው መሞቱን እና ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውም ተገልጿል፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል በቀጠለው ጦርነት በከተማዋ ከፍተኛ የንብረት ዉድመት መከሰቱንና በርካታ ሰዎች ከተማዋን ለቀዉ ለስደት መዳረጋቸዉን መረጃዉ አመልክቷል፡፡

RT_News


• @ThinkAbyssinia •
7.2K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 16:15:08
ለጥንቃቄ


ነገ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል ተብሏል

የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል በነገዉ እለት ይከበራል፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ነገ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል ተብሏል፡፡

መድፍ የሚተኮሰዉም ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት መድፉ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ ለበዓሉ ክብር የሚተኮስ መሆኑን ገልጿል።


• @ThinkAbyssinia •
7.7K viewsedited  13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ