2022-05-15 19:30:55
#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች
1፥ወልድያ ከተማ የ"መቀመጭት ተራራን" በአቡነ ኤርምስ ስም መሰየሙን አስታወቀ።
የተራራውን ስያሜ የሰጠው ከተማ አስተዳደሩ አቡነ ኤርምያስ ያደረጉትን ውለታ በማሰብ እና ለአቡኑ ተያያዥ የልማት የቤት ሥራዎች ለመስጠት መሆኑን ገልጿል። የዕፅዋት ሳይንስ መድኃኒት ቅመማ ጋር ተያይዞ ለምርምር የሚሆኑ ሀገር በቀል ዕፅዋቶች በስፋት የሚገኙበት ተራራ በመሆኑ የጥንት መጻሕፍትን በመተርጎም የሚመራመሩ ሊቃውንትን በተራራው በማሰማራት የምርምር ማዕከል እንደሚያደርጉት ታላቅ ተስፋ ስለተጣለባቸው ስያሜው የተሰጠበት አንደኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል። ተራራው ከፍ ያለ ዕይታ ባላቸው አባት ስም መሰየሙ ክብሩ ለተሰየመለት ሰው ብቻ ሳይሆን የብፁዕነታቸውን አገልግሎት ለቀመሰው እና ላጣጣመው ለመላው የወልድያና አካባቢው ሕዝብ እና ከተማ አስተዳደሩ ጭምር ነው ሲል ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
2፤በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ20ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ በሽታ ሕይወታቸው ያልፋል ተባለ። በአለም ለ40ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ25ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የአለም የቲቢ ቀን በድሬዳዋም በከተማ ደረጃ ቀኑ የተከበረ ሲሆን በመድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ የበሽታው በትንፋሽ የሚተላለፍ መሆን ከአኗኗሯችን ሁኔታ ጋር ተዳምሮ የቁጥጥር ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል። በድሬዳዋ አስተዳደር ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ በ31 የህክምና መስጫ ማእከላት የቲቪ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ያሉት ሃላፊው፤ "አገልግሎቱን ካገኙት ተማሚዎች ውስጥ ሰባ ከመቶ ያህሉ ህክምናቸውን በስኬት ያጠናቀቁ ናቸው” ሲሉ አምልክተዋል። በመድረኩ በቀረበ ጽሑፍ በኢትዮጵያ በአመት 20 ሺህ ሰዎች በቲቪ በሽታ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተገልጿል። ቲቢ በኢትዮጵያ በገዳይነቱ በአንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።
3፤የቻይናው ባሉን የዓለም በከፍታ የመብረር ክብረ ወሰንን ሰበረ።የቻይናው ተንሳፋፊ ባሉን ከምድር 9 ሺህ 32 ሜትር ከፍታ ላይ መንሳፈፍ በመቻሉ ነው የዓለም የከፍታ ክብረ ወሰንን የሰበረው። በጉዙፍነቱ ምክንያት “ተንሳፋፊው መርከብ” ተብሎ የሚጠራው እና‹‹ጂሙ ቁጥር 1›› በሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ባሉን 2.625 ቶን የሚመዝን ሲሆን ሂሊየም በተሰኘ ጋዝ ተሞልቶ በአየር ላይ በሰከንድ 30 ሜትር የሚቀዝፍ እንደሆነ ተነግሯል። ከ8 ሺህ 840 ሜትር በላይ ከሚረዝመው እና በቻይና እና በኔፓል ድንበር አካባቢ ከሚገኘው ኮሞላግማ ተራራ ጫፍ ከሚገኘው የምርምር ጣቢያ የተለቀቀው ባሉኑ ከ9 ሺህ ሜትር በላይ በመንሳፈፍ ነው ክብረ ወሰኑን ለመስበር የቻለው።
4፤የፊንላንድ መሪዎች ሀገራቸው ኔቶን መቀላቀል እንደምትፈልግ በይፋ አሳወቁ።የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ከካቢኔያቸው ጋር ባደረጉት ስበስባ ላይ ፊንላንድ የኔቶ አባል ለመሆን በምታቀርበው የአባልነት ጥያቄ ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህን የካቤኒ ስምምነት ተከትሎም የአባልነት ጥያቄው ለመጽደቅ የፓርላማ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል ተብሏል። የፊንላንድ ጠ/ሚ ሳና ማሪን ውሳኔውን " ታሪካዊ ነው " ያሉ ሲሆን " ዋናው ነገር የፊንላንድና የህዝቦቿ ደህንነት ነው " ሲሉ ገልጸዋል። ውሳኔው የኖርዲክ አካባቢ ሃገራትን ፀጥታና ትብብር ያጠናክራልም ብለዋል። ሩስያ ሰሞኑን የፊንላንድ የኔቶ አባል የመሆን ፅኑ ፍላጎትን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ መስጠትዋም አይዘነጋም። ሩስያ በአሁን ሰዓት ከዩክሬን ጋር በጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሀገሪቱ የNATO አባል የመሆን ፍላጎት ማሳየቷን ተከትሎ እንደሆነ ይታወቃል።
5፤በሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሰይድ አብዱላሂ ዴኒ እየመሩ ይገኛሉ። የሀገሪቱ ፓርላማ በፀጥታ ስጋት በሀጋር አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እያካሄደ ባለው ምርጫ እስካሁን የመጀመሪያ ዙር ውጤት ታውቋል። በዚህም ሰይድ አብዱላሂ ዴኒ በ65 ደምጽ እየመሩ ሲሆን፤ ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በ61 ድምጽ በሁለተኝነት እየተከተሉ መሆኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል። ሀሰን ሼክ መሃመድ 52 ድምጽ እንዲሁም ሀሰን አሊ ካሂሬ 48 ድምጽ በማግኘት ለሁለተኛ ዙር ምርጫ ማለፋቸው ተነግሯል። እየተካሄደ ባለው ምርጫ ላይ ለመወዳደር በስልጣን ላይ ያሉትን መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ ፋርማጆን ጨምሮ 39 ሰዎች ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር በእጩነት ቀርበዋል። በተጨማሪም የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋውዚያ የሱፍ ሀጂ አደም ብቸኛዋ ሴት እጩ ሆነው ቀርበዋል።
6፤ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ተጋርቷል።የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሰላሳ ሰባተኛው ሳምንት ጨዋታ በለንደን ስታዲየም ቀጥሎ ሲካሄድ ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም ያደረገውን ጨዋታ 2 - 2 በሆነ ውጤት አጠናቋል ። የማንችስተር ሲቲን ግቦች ጃክ ግሪሊሽ እና ሶፊያን ኩፋል በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥሩ የዌስትሀምን ሁለት ግቦች ጃሮድ ቦውን ማስቆጠር ችሏል ። ጃሮድቦውን በዘንድሮ የውድድር አመት 18 ግቦችን በሁሉም ውድድሮች ላይ አስቆጥሯል ። ሪያድ ማህሬዝ ማንችስተር ሲቲ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት አባክኗል ። የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ሊጉን በ 90 ነጥብ ሊጉን መምራቱን ሲቀጥል ዌስትሀም በ 56 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።
7፤ቼልሲ የሴቶች ኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ መሆኑ ተረጋግጧል።የእንግሊዝ የሴቶች የኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በዌምብሌ ስታዲየም ሲካሄድ ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 - 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል ። ቼልሲ በሳማንታ ከር ሁለት ግቦች እና ኤሪክ ኩተበርት ሶስት ግቦች ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ ለአራተኛ ጊዜ የእንግሊዝ የሴቶች ኤፍ ኤ ካፕን ማሸነፋቸውን አረጋግጠዋል ። የቼልሲ የሴቶች ቡድን በባለፈው ሳምንት የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግን ማሸነፉ ይታወሳል ።
• @ThinkAbyssinia •
7.4K views16:30