2022-05-16 10:45:50
#ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች
1፤የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ በመግባት ላይ መሆናቸውን ተመድ ገለፀ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው በትግራይ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተጨማሪ 85 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ነው የገለጸው፡፡ ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህም በተያዘነው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በተመሳሳይ በሰሜን አፋር አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በሚቀጥሉት ቀናት በዓለም የምግብ ፕሮግም የተዘጋጀው የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚሰራጭ ተጠቁሟል፡፡
2፤ሱማሌ እና አፋር ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው አዋሳኝ ቀበሌዎች የሁለቱ ክልሎች ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች እንዲወጡ ስምምነት ላይ ደረሱ።ሱማሌ እና አፋር ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አዋሳኝ ቀበሌዎች ላይ በመካከላቸው የሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት እንደተስማሙ ዶይቸቨለ ዘግቧል። የሁለቱ ክልሎች ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች ከአወዛጋቢ አካባቢዎች እንዲወጡ እና የፌደራል ጸጥታ ኃይሎች ለጊዜው እንዲሰማሩባቸው ስምምነት ላይ እንደተደረሰ የሱማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ተናግረዋል። ክልሎቹ እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት፣ ሰሞኑን በጅግጅጋ ከተማ ባካሄዱት እና የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለም ጭምር በተገኙበት ውይይት ላይ ነው።
3፤በደቡብ ወሎ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ።አደጋው የደረሰው ከመካነ-ሠላም ወደ መርጦለማሪያም 26 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ መሆኑን የቦረና ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ በዚህም አሽከርካሪውን ጨምሮ የ6 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ 9 ተሳፋሪዎች ላይ ከባድ እንዲሁም 11 ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡ የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ንዑስ ክፍል ቁጥጥርና ክትትል የስራ ሂደት ሀላፊ ሳጅን ይርጋ ጀማል እንደገለፁት÷ ተሸከርካሪው ከአቅም በላይ መጫኑና 75 ሜትር የሚሆን ገደል ውስጥ መግባቱን መግለፃቸውን ከቦረና ወረዳ የመንግስት ኮሙንኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
4፤በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰሜን ኮሪያዊያን ቁጥር 15 ደረሰ።ከዓለም ተገልላ በቆየችው ሰሜን ኮሪያ ኮሮና ቫይረስ እንደ አዲስ በመስፋፋት ላይ ይገኛል። ከሶስት ዓመት በፊት በቻይናዋ ውሃን ከተማ ተከስቶ ዓለምን ያዳረሰው ኮሮና ቫይረስ አሁን ላይ ስርጭቱ እና የጉዳት መጠኑ እየቀነሰ ይገኛል። ይሁንና ባለ ኑክሌር አገሯ ሰሜን ኮሪያ እንደ አዲስ በዚህ ቫይረስ መፈተን የጀመረች ሲሆን በዚሁ ገዳይ ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ዜጎች ቁጥር 15 ደርሷል። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ስትልም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በዘመቻ መልክ አሰማርታለች። የእነዚህ ዜጎች ዋነኛ ስራ ከፍተኛ ሙቀት ያላቸውን ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ማድረግ፣ ስለ በቫይረሱ ሁኔታ ዜጎችን ማስተማር እና ሌሎች የጤና ስራዎችን መስራት ይሆናልም ተብሏል።
5፤ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ51 ብር ከ4738 ሳንቲም እየተገዛ ይገኛል። እንዲሁም መሸጫ ዋጋው 52 ብር ከ5033 ሳንቲም መሆኑን ከድረገጹ ተመልክተናል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋው 59 ብር ከ9328 ሳንቲም እንዲሁም መሸጫው 61 ብር ከ1315 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ53 ብር ከ4607 ሳንቲም እየገዛ በ54 ብር ከ5299 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን፣ አንድ የቻይና ዩዋን ደግሞ በ6 ብር ከ8581 ሳንቲም ተገዝቶ በ6 ብር ከ9953 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሚገኝ ቲንክአቢሲኒያ ተመልክቷል።
6፤የሴካፋ ውድድር የቀን ማሻሻያ ተደረገበት።
በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንዲደረግ አስቀድሞ ቀን የተቆረጠለት የሴካፋ ሴቶች ሻምፒዮሺፕ ግንቦት 24 እንደሚጀምር ይፋ ተደርጓል ። ሉሱዎቹ በምድብ ሁለት መደልደላቸው የሚታወስ ሲሆን የምድባቸውን የመጀመሪያ ጨዋታ ግንቦት 25 ከ ዛንዚባር አቻቸው ጋር የሚያካሂዱ ይሆናል ። ውድድሩ ግንቦት 24 ጀምሮ ከአስር ቀናት ቆይታ በኋላ ሰኔ 4 ፍፃሜውን እንደሚያገኝ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል ። የዘንድሮ የውድድር ዓመት የሴካፋ ሴቶች ሻምፒዮንሺፕ ሁሉም ጨዋታዎች በ ዩጋንዳ ፉፋ ቴክኒካል ሴንተር ንጄሩ የሚካሄድ ይሆናል ።
• @ThinkAbyssinia •
9.1K views07:45