Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 89

2022-05-14 22:12:26
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት እና ለሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ለጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ የክብር ዶክትሬት ሰጠ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፤ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው መርሃ ግብር ለተሸላሚቹ የክብር ዶክትሬቱን አበርክተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት ዶክተር አኪንውሚ አዴሲና በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በልማትና ሌሎችም ተግባራት የላቀ ሚና የተወጡ ናቸው።
 
የአፍሪካ ልማት ባንክ 8ኛው ፕሬዚዳንት በመሆን እየመሩ ያሉት አዴሲና በአህጉሪቷ የድህነት ቅናሳ፣ የትምህርት መስፋፋት፣ የስራ ፈጠራ እና ሌሎችም ተግባራት ላይ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸው ይታወቃል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

  የጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲቪል ስራዎች ግንባታ ስኬታማነት ሃላፊነታቸውን በብቃት የተወጡ ናቸው።

  በግድቡ ግንባታ ስኬት የላቀ ሚና ለነበራቸው ለእኒህ ታላቅ ባለውለታ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

• @ThinkAbyssinia •
1.6K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 22:04:44
ሊቨርፑል የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል !

የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በዌምብሌ ስታዲየም ቀጥሎ ሲካሄድ ቼልሲ ከ ሊቨርፑል ያደረገውን ጨዋታ በመደበኛው ዘጠና ደቂቃ 0 - 0 በሆነ ውጤት አጠናቋል ።

ወደ ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃዎች ባመራው ጨዋታ ላይ ሁለቱ ክለቦች ሊለያዩ ባለመቻላቸው በመለያያ ምት ሊቨርፑል 6 - 5 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል ።

ቼልሲ በተከታታይ ሶስት የኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታዎች ሽንፈትን አስተናግዷል ። ሊቨርፑል ለስምንተኛ ጊዜ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል ።


• @ThinkAbyssinia •
2.0K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 19:31:30 #ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ጋር በሰመራ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በአፋር ክልል ወቅታዊ ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ነው የተገለጸው። አምባሳደሯ ቱርክ የሰመራ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የሚሰሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

2፤የህወሓት ቡድን አሁንም በአማራ እና አፋር ክልሎች አለመውጣቱን መንግስት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች እንደወጣ ቢያወራም አሁንም በአማራ ክልል በወረራ ከያዛቸው አዲአርቃይ፣ ጸለምት፣ አበርገሌ እና ሌሎች አካባቢዎች እንዲሁም ከአፋር ክልል ደግሞ በራህሌ፣ ኮኖቫ፣ አብአላ፣ መጋሌ ወረዳዎች አልወጣም ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ የሰብዓዊ እርዳታ እና ሰሜኑን የኢትዮጵያን ሁኔታ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ÷ መንግስት በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የክልሉን ነዋሪዎች ለመታደግ ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔን ተከትሎ በየብስ እና በአየር ትራንስፖርት የሚጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል በመግለጫቸው፡፡

3፤ ህወሓት በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች 7 ሺህ የሚጠጉ ንፁሃንን መግደሉን ጥናት አመለከተ።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ያልነበረቸው 6 ሺህ 985 ንፁሃን ዜጎችን መግደሉን ጥናት ተደርሶበታል፡፡ አሸባሪ ቡድኑ በአማራ ክልል በወረራ በቆየባቸው አካባቢዎች ያደረሰው ጉዳት በተመለከተ ጥናት ሲያደርግ የነበረው ቡድን የጥናቱን ጥቅል ውጤት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። ቡድኑ በፈፀመው ወረራ ከ240 ሺህ በላይ ሰዎች የሰብዓዊ ጉዳት ሰለባ ሲሆኑ ÷ 7 ሺህ 460 ዜጎች ደግሞ በሃይል ታፍነው በመወሰዳቸው የት እንዳሉ አለመታወቁ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ በጦርነቱ ሚና ሳይኖራቸው ከተገደሉት 6 ሺህ 985 ዜጎች ውስጥ 1 ሺህ 797ቱ በጅምላ ተጨፍጭፈው የተገደሉ መሆናቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።

4፤የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የአንዳንድ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እስከ 50 በመቶ ሊቀንሰው እንደሚችል የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ጠቆመ

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የአንዳንድ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እስከ 50 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ተተንብይዋል። እንደ የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ገለጻ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የሚቀጥል ከሆነ የአንዳንድ ነዳጅ አስገቢ ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከ20 እስከ 50 በመቶ ሊቀንስ ይችላል። ሁለቱ ሀገራት በምግብ እና የነዳጅ/ኃይል አቅርቦት ከፍተኛ ድርሻ እንደመያዛቸው፣ ጦርነቱ በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ ካመጣው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ለመውጣት የሚያርጉትን ጥረት በማስተጓጎል ላይ ነው ብሏል።

5፤የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል።

ዛሬ አመሻሽ 12:45 የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በዌምብሌይ ቼልሲን ከሊቨርፑል የሚያገናኝ ይሆናል። ሊቨርፑል እና ቼልሲ ዛሬ በዌምብሌይ በፍፃሜው ሲገናኙ አንጋፋው የዋንጫ ውድድር 150ኛ ዓመቱን ያከብራል። ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ጀርመናዊ አሰልጣኝ የእንግሊዝ ኤፌ ዋንጫን በማሸነፍ ታሪክ ይሰራል። የርገን ክሎፕ እና ቶማስ ቱሄል በኤፍኤ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ፊት ለፊት የተገናኙ የመጀመሪያዎቹ ጀርመናዊ አሰልጣኝ ናቸዉ። ሊቨርፑል እና ቼልሲ ለመጨረሻ ግዜ በኤፌ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ የተገናኙት በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2012 ነበር። በዛ ጨዋታ ሰማያዊዎች በድሮግባ እና ሬሚሬስ ግብ ታግዘዉ ሊቨርፑልን 2-1 በማሸነፍ የዋንጫዉ ባለቤት መሆን ችለዋል። የሊቨርፑልን ብቸኛ ግብ አንዲ ካሮል ነበር ያስቆጠረዉ።

• @ThinkAbyssinia •
5.1K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 17:49:00
#Gonder

ጎንደር ከምንጊዜውም በበለጠ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ የጎንደር ከተማ ኮምኒኬሽን ገለፀ

ጎንደር ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ የጎንደር ከተማ ኮምኒኬሽን ገልጿል። ነገር ግን አንዳንድ የጥፋት ተልእኮ ያላቸው ተላላኪዎች ከተማዋ እንዳትረጋጋ ቀንና ሌሊት እየሰሩ እንደሚገኙም ጠቁሟል።

ከተማችዋ ላይ ምንም የተፈጠረ ግጭት ሳይኖር ግጭት ተፈጥሯል በማለት በተለያዩ መንገዶች የሀሰት ወሬዎችን እያናፈሱ ይገኛሉ። ለዚህም በጎንደር ከተማ የምትገኙ ነዋሪዎች ከተማዋ ላይ ምንም የተፈጠረ የፀጥታ ችግር እንደሌለ አውቃችሁ ሰላማዊ እንቅስቃሴአችሁን እንድታደረጉ እናሳስባለን የሚል መልእክትም ተላልፏል።

ህብረተሰቡም የሀሰት ወሬዎችን የሚያናፍሱ ግለሰቦችን ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲያደርጉ የጎንደር ከተማ ኮምኒኬሽን ገልጿል።


• @ThinkAbyssinia •
6.4K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 17:27:33 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የሃላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የሀላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እና አገሪቱን ወደ ተሻለ እድገት እና ብልጽግና የሚያሻግሩበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን የሀገሪቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡


• @ThinkAbyssinia •
6.1K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 17:27:08
በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በቦንጎታ ቀበሌ አንዲት እናት ሶስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

በወላይታ ዞን በሆቢቻ ወረዳ በቦንጎታ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ አበበች ጀንበሬ ሦስት ልጆችን ያለምንም ጤና ችግር በሰላም ተገላግላለች፡፡

አሁን ላይ ልጆቹና የልጆች እናት ፍፁም ጤነኛ መሆናቸውም የተገለፀ ሲሆን የሆቢቻ ወረዳ ጤና ጣቢያ ባለሞያዎች ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት አስደናቂ ክስተት እንዳልተፈጠረና እንግዳ መሆኑን ተናግረዋል።

የሦስት ልጆች እናት ወ/ሮ አበበች ጀንበሬ ሦስት ሴት ልጆችን በሰላም መገላገሏን ፈጣሪን አመሰግናለች። መረጃዉን ከወላይታ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ተመልክተነዋል።

• @ThinkAbyssinia •
6.2K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 14:10:37
በሊቢያ በተቀናቃኝ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው ተባለ

በሊቢያዋ የባሕር ዳርቻ ከተማ ሳባርታ ከተማ በተቀናቃኝ ታጣቂዎች መካከል ብርቱ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ስፑትኒክ ፅፏል፡፡

በከተማዋ እና በአቅራቢያዋ ከባድ ፍንዳታም እየተሰማ ሲሆን የውጊያው ምክንያት ምን እንደሆነ ግን አልታወቀም ተብሏል፡፡

በሊቢያ የቀድሞው መሪ የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ አስተዳደር ከ11 ዓመታት በፊት በትጥቅ አመፅ ከተወገደ ወዲህ አገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንደራቃት ነው፡፡


Sputnik

• @ThinkAbyssinia •
4.0K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:28:29
#Update

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የዩናይትድ አረብ ኤሜሬቶች ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የአቡ ዳቢው ልዑል አልጋ ወራሽ፤ ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ ትናንት ማረፋቸውን ተከትሎ ነው ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት፡፡

al ain Amharic

• @ThinkAbyssinia •
1.7K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 11:57:44
ኢዜማ ምክትል ሊቀመንበሩ ጨምሮ 4 አባላቱን አገደ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው አሰራጭተዋል ብሎ የተጠረጠራቸውን የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ጨምሮ 4 አባላቱን አገደ፡፡

ግለሰቦቹ የሳምንት ሥራ መከታተያ ቅፅ በሚል ህገ-ወጥ ሰነድ አዘጋጅተው ግንቦት 2፣ 2014 በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የዋትስ አፕ ግሩፕ ላይ በመላክ ተጠናክረው መታገዳቸው ሸገር ኤፍኤም ዘግቧል፡፡

የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴውም ከትናንት በስትያ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል። ሰነዱ ፍፁም ስህተት እና የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሂደት ዲሞክራሲያዊነትን የሚያቀጭጭ ብሎታል በውሳኔው፡፡

በመሆኑም ሰነዱን አዘጋጅተዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 የፓርቲው አባላት በሰነዱ ላይ ያላቸውን ተሳትፎና የህግ ጥሰታቸው ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለፓርቲው ህገ ደንብ ትርጉምና ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተመርቷል ተብሏል፡፡

ጉዳዩ በኮሚቴው ተመርምሮ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስም የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ የፋይናንስ መምሪያ ሀላፊው አቶ አንድነት ሽፈራሁ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደና አባል የሆኑት አቶ ኢዮብ መሳፍንት ከሀላፊነታቸው ለጊዜው እንዲታገዱ ተወስኖባቸዋል፡፡

sheger fm

• @ThinkAbyssinia •
2.7K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 11:39:53
አዲስ መታወቂያ ከመታገዱ በፊት ዲጂታል መታወቂያ በ7 ሺሕ ብር ሲሸጥ እንደነበር ተጋለጠ

አዲስ ማለዳ በአዲስ አበባ አስተዳደር ስር በተለያዩ ወረዳዎች ከአንድ ወር በላይ በፈጀ ጊዜ ባደረገችው የማጣራት ሥራ፣ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ከተቋረጠበት ሚያዝያ 21/2014 በፊት በአምስት ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ የነበረው ዲጂታል መታወቂያ በወሳኝ ኩነት ሠራተኞችና በአዲስ አበባ ነዋሪዎች መካከል በሚፈጸም የቤተሰብ አካቶ ስምምነት ሲሰጥ እንደነበር አረጋግጫለሁ ብላለች።

የዲጂታል መታወቂያ ሕጋዊ መስመር ተከትለው ማውጣት ለማይችሉ ሰዎች ሲሠራ የነበረው የአንድ አዲስ አበባ ነዋሪ በሆነ አባወራ እና በወሳኝ ኩነት ሠራተኞች ስምምነት ሲሆን፣ ስምምነቱ የሚፈጸመው በሕገ ወጥ መንገድ መታወቂያ የሚሠራለት ሰው አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነው አባወራ የቤተሰብ አካል አድርጎ በመመዝገብ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነ አንድ አባወራ ወይም እማወራ ከወሳኝ ኩነት ሠራተኞች ጋር በሚፈጥሩት ስምምነት መታወቂያ የማውጣት ሥራውን ሕጋዊ ለማስመሰል መታወቂያ የሚወጣለት ሰው የዚህ አባወራ ወይም እማወራ የቤተሰብ አካል ሆኖ በወሳኝ ኩነት መዝገብ ላይ እንደሰፈረ ይቀጥላል። ይህ ዓይነቱ ሥራ የሚፈጸመው የወሳኝ ኩነት ሠራተኞች አስቀድመው ለዚሁ ተግባር ተስማምተው ባስቀመጧቸው ነዋሪዎች ሲሆን፣ በቤተሰብ መረጃ ምዝገባ ላይ የሌላቸውን የቤተሰብ ቁጥር ቀድመው የሚያስመዘግቡ ነዋሪዎች አሉ።

በወሳኝ ኩነት ሠራተኞችና በአዲስ አበባ ነዋሪ ስምምነት መሠረት የሚወጣው መታወቂያ ከቅርብ ወራት በፊት የተጀመረው ዲጂታል መታወቂያ ብቻ ሳይሆን፣ ወረቀት መታወቂያም በዚሁ መንገድ እንደሚሠራ አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።


addis maleda

• @ThinkAbyssinia •
3.1K views08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ