Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 92

2022-05-13 09:26:12 #Update

በአዲስ አበባ ፊሊፖስ ኢንዱስትሪ መንደር ትላንትና ምሽት የደረሰ የእሳት አደጋን ለመቆጣጠር ከ7 ሰዓት በላይ መጠየቁ ተነገረ

ትላንት ምሽት 3:05 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታዉ ፊሊፖስ ኢንዱስትሪ መንደር በተነሳ እሳት በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን እሳቱንም ለመቆጣጠር ከሰባት ሰዓት በላይ መፋጀቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

እሳቱንም ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት ድረስ ርብርብ ተደርጎ እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዉሏል።

አደጋዉ ሰፋ ያለ የነበረ በመሆኑ 15 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ከ75 በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩበት ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱ ተዛምቶ የበለጠ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ ተችሏል።

ምሽቱን ከደረሰው የእሳት አደጋ ተያይዞ ቲንክአቢሲኒያም ወቅታዊ መረጃዎችን ሲያደርሳችሁ ቆይቷል ተጨማሪ የንብረት ጉዳትን የሚመለከት መረጃም እንደደረሰን እናቀርባለን።


• @ThinkAbyssinia •
2.6K viewsedited  06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 09:25:15
#ቲንክአቢሲኒያ_እለታዊ_የአየር_ትንበያ_መረጃ

ለውሎዎ ጠቃሚ የሆኑ እለታዊ የአየር ትንበያ መረጃዎችን እናድርስዎ


ዛሬ በአንዳንድ የሀገራችን ከተሞች ያለውን ያየር ሁኔታ ስንመለከት መዲናችን አዲስ አበባ ዝቅተኛው 14 ከፍተኛው 29 ድግሪ ሲልሽየስ ፀሀያማ ሆና ትውላለች።

ባህርዳር ዝቅተኛው 15 ከፍተኛው 32 ከፊል ደመናማ ሀዋሳ ዝቅተኛው 13 ከፍተኛው 32 በአመዛኙ ፀሀያማ እንዲሁም መቀሌ ዝቅተኛው 12 ከፍተኛው 29 ፀሀያማ ሆነው እንደሚውሉ ቲንክአቢሲንያ ከቤሄራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ ድረገፅ ተመልክቷል።


• @ThinkAbyssinia •
2.6K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 07:27:03
መንግስት ለቀጣዩ ዓመት 780 ቢሊየን ብር በጀት ማዘጋጀቱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ፌዴራል  መንግስት በብርቱ የኢኮኖሚና የፀጥታ ፈተና ውስጥ ሆኖ ከሁለት ወር በኋላ ለሚጀምረው አዲሱ የበጀት ዓመት 780 ቢሊየን ብር በጀት ማዘጋጀቱን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ስምታለች። 

አዲሱ በጀት ካለፈው ዓመት በጀት ጋር ሲነፃፀር የአንድ መቶ ቢሊያን ብር ያህል ብልጫ አለው። የ 2014 ዓ.ም በጀት የአጋማሽ አመቱ ጭማሬ ተዳምሮ 680 ቢሊየን ብር ነበር።

ዘንድሮን በበርካታ መሰናክሎች ያሳለፈው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣዩ ዓመት የበለጠ ፈተና የሚጠብቀው ሲሆን መንግስት አሁን ያሰናዳው 780 ቢሊየን ብር በጀት ከፍ ያለ ጉድለት ሊገጥመው እንደሚችል በበጀት ዝግጅቱ ወቅት በተደረጉ ምክክሮች ላይ መነሳቱን ስምተናል። 

ለ2015 ዓ.ም የተያዘው በጀት ከ 2014 ዓ.ም የ100 ቢሊየን ብር ጭማሬ ይኑረው እንጂ በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሲሰላ ብዙም ለውጥ የሚታይበት አይሆንም።


wazema radio

• @ThinkAbyssinia •
4.8K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 07:26:11
#Update!
ዋልያዎቹ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ስታዲየም ታወቀ

ኢትዮጵያ በሜዳዋ የምታደርገውን ጨዋታ በገለልተኛ ስታዲየም እንድታካሂድ ካፍ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቡድናችን የሚጫወትበትን ስታዲየም ከወዲሁ አሳውቋል ።

ይህንንም ተከትሎ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከ ግብፅ የሚያደርጉትን ጨዋታ በማላዊ ለማድረግ ከውሳኔ መደረሱ ይፋ ሆኗል ።


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

• @ThinkAbyssinia •
4.5K views04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 07:20:15
የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ከሰኞ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደመቱ ተነገረ


በአዲስ አበባ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ከሰኞ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደመቱ መሆናቸውን ሸገር ራዲዮ ዘግቧል።

የሕዝብ ማመላላሻ አውቶብሶቹ ሥራ ያቆሙት፣ ከሁለትና ሦስት ወራት በላይ ውል እንደማይታደሰላቸውና ተገቢው ክፍያ በወቅቱ እንደማይተከፈላቸው በመግለጽ ነው። የከተማው አስተዳደር ግን አውቶብሶቹ በዛሬው ዕለት ሥራቸውን እንዲጀምሩ አዟል።

ከቀናት በፊት አስተዳደሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ምክንያት በማድረግ ታሪፍ በሚጨምሩ ወይም በነባሩ የስምሪት መስመራቸው የማይቀጥሉ ከሆነ የሥራ ውላቸውን እንደሚያቋርጥ መግለጡ ይታወሳል።


sheger_fm

• @ThinkAbyssinia •
4.6K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 00:26:11 #Update!
የእሳቱ እስካሁን አልጠፋም

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ኢንዱስትሪ መንደር ከፍተኛ የእሳት አደጋ የተነሣ ሲሆን ቃጠሎው ተባብሶ በርካታ ሼዶችንና መጋዘኖችን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል።

የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ መኪኖችና አባላት በቦታው የተገኙ ቢሆንም ቦታው አመቺ ባለመሆኑ አደጋውን መቀነስ ባይቻልም ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመተባበር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛሉ።

የወረዳው ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጽ/ቤት እንደገለጸው እሳቱ አሁንም ድረስ ያልጠፋ ሲሆን አሁን ባለው መረጃ ከሦስት በላይ ሼዶች ተቃጥለዋል።

• @ThinkAbyssinia •
1.2K views21:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 23:16:47
#እሳት_አደጋ

ኮልፌ አጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ኢንደስትሪ መንደር አካባቢ ከፍተኛ የእሳት አደጋ እንደደረሰ ከቦታው የሚገኙ የቲንክ አቢሲኒያ ቤተሰቦች መረጃዎችን አድርሰውናል።

ብዛት ያላቸው የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና መኪኖች እንዲሁን ህዝቡ አደጋውን ለመከለከል ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እስካሁን አለታወቀም ተጨማሪ መረጃዎችን እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።


• @ThinkAbyssinia •
2.7K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 20:39:36
የቻይና ኩባንያ ስራውን ሳይጨርስ የተከራያቸውን ሼዶች አስረክቦ ለቆ መውጣቱ ተሰማ

በጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ሲሰራ የነበረው ሁዋጂያን ግሩፕ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በአለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት ስራውን ካቆመ ከአንድ አመት በኋላ የተከራየውን ሼዶች በሙሉ አስረክቦ ፓርኩን ለቆ መውጣቱን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳንዶካን ደበበ ተናግረዋል።


Capital

• @ThinkAbyssinia •
6.4K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 20:08:11
ሉሲዎቹን በሴካፋ ውድድር የሚመራው አሠልጣኝ ታውቋል

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው በሴካፋ የሴቶች ዋንጫ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን የሚመራ አሰልጣኝ መምረጡን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ለውድድሩ በቅርቡ ዝግጅት የሚጀምረው ቡድኑ ለዚህም እንዲረዳው የ20 ዓመት በታች ቡድኑን አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ተጨማሪ ኃላፊነት ይዞ እንዲሰራ መምረጡን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫን ያሸነፈው አሠልጣኝ ፍሬው በዓለም ዋንጫ ማጣርያም እስከ መጨረሻው ዙር መድረሱ የሚታወስ ሲሆን ዋናውን ብሔራዊ ቡድን ውጤታማ እንዲያደርግ ኃላፊነት እንደተሰጠው ከመገለፁ በቀር የኮንትራቱ ዝርዝረ ይፋ አልሆነም ኢትዮጵያ በምድብ ለ ከታንዛንያ ፣ ዛንዚባር እና ደቡብ ሱዳን መደልደሏ ይታወሳል።


ሶከር ኢትዮጵያ

• @ThinkAbyssinia •
6.8K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 19:42:10
ተመድ አቢዬ ግዛት ባሰማራው የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል


የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት አቢዬ ግዛት ባሰማራው የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ላይ ዛሬ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ለ6 ወራት የተራዘመው የተልዕኮው ቆይታ ግንቦት 7 ያበቃል። ምክር ቤቱ ሁለቱ አገራት ለቋቋሙት የጋራ ድንበር መቆጣጠሪያ ሥርዓት የሚሰጠውን ድጋፍም ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች በቅርቡ በሱዳን ጥያቄ ከግዛቲቷ ወጥተዋል።

ዋዜማ ራዲዮ

• @ThinkAbyssinia •
6.6K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ