Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-10-07 12:21:14
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለሜትር ታክሲ ተሸከርካሪዎች የቀረጥ ነጻ ድጋፍ ማቆሙን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ አስማረ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እስኪ ተጠየቁ ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት፣ ቢሮው ከዚህ ቀደም በሜትር ታክሲ አገልግሎት ዘርፍ ለመሰማራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ለነበሩ ማህበራትና ግለሰቦች ተሸከርካሪዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ለገንዘብ ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ሲጽፍ ቆይቷል።

ሆኖም፣ ቢሮው በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የሜትር ታክሲ ተሸከርካሪዎች ቁጥር በቂ ሆኖ በማግኘቱ የቀረጥ ነፃ ድጋፍ መስጠት ስለማቆሙ ኃላፊው ተናግረዋል። በሜትር ታክሲ ዘርፍ መሰማራት የሚፈልግ ማንኛውም አካል የቀረጥ ነጻ መብት ሳይጠይቅ ተሸከርካሪዎችን ማስገባት ይችላል ያሉት ኃላፊው፣ በብዙሃን ትራንስፖርት ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ግለሰቦችና ማህበራት ግን የቀረጥ ነጻ መብት እንዲያገኙ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት።

via - ebc
• @ThinkAbyssinia •
6.1K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 12:09:27
ብሄራዊ ባንክ በጥቁር ገበያው ተዋንያን ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሕገወጥ የሐዋላ ስራ የተሰማሩ ሰዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል። በዚህም 391 የሚደርሱ ሕገወጥ የሐዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው መዘጋቱንና የግለሠቦቹ ስም ዝርዝር ለፍትሕ ሚኒስቴር ተልኮ ክስ የመመስረት ሂደቱ እንደሚጀመር አስረድተዋል።

በህገ ወጥ መልኩ በጥቁር_ገበያ ላይ በተሠማሩ አካላት ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል። አክለውም በባንክ ቤቶች ውስጥ ያሉ የባንክ ኃላፊዎችና ሰራተኞችም በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አሉ በነዚህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ነው በመግለጫቸው ያነሱት። ይህን ሕገወጥ ድርጊት ለሚጠቁሙ ዜጎች የወሮታ አከፋፈል ስርዓት መዘጋጀቱም ተነግሯል።

via - EPA
• @ThinkAbyssinia •
6.0K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 08:17:38
ወተት ውስጥ ውኃ ጨምረው ለሽያጭ ሊያቀርቡ የነበሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።

በሰሜን ሸዋ ኩዩ ወረዳ ወተት ውስጥ ውኃ ጨምረው የወተቱን ጣዕም እንዲለቅ አድርገው ለሽያጭ ሊያቀርቡ ሲያጓግዙ የነበሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን መንግስት ገልጿል።

• @ThinkAbyssinia •
7.8K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 22:31:25
ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ስንዴ እንድትልክ የሚያስችል ስምምነት ተደረሰ።

ስምምነቱ የተደረሰው የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ የኬንያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ የስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በኬንያ የተከሰተውን የምግብ ምርቶች የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ከስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ በተጨማሪ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አቅም ለመጠቀም በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡በአጠቃላይ የሁለቱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የድንበር ተሻጋሪ ንግድን ለማሳደግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

via - fbc
• @ThinkAbyssinia •
4.2K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 19:45:27
ማርክ ዙከርበርግ ከሰባት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካ ምርጥ አስር ቢልየነሮች ዝርዝር ውጪ ሆነ።

የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ እኤአ ከሴፕቴምበር 2021 ጀምሮ 76.8 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ሀብቱን በማጣቱ፣ ከ400 የአሜሪካ ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ከ3ኛ ወደ 11ኛ ደረጃ መውረዱን ፎርብስ ዘግቧል። ዙከርበርግ ለመጨረሻ ጊዜ ከአሜሪካ ምርጥ አስር ቢልየነሮች ዝርዝር ውጪ የነበረው እአአ በ2015 ነበር።

• @ThinkAbyssinia •
3.3K views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 19:27:53
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ፈቃድ አገኘ

የፋይናንስ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ባለው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የብሔራዊ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንደተሰጠው አስታውቀዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ከሚጀምረው የቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ M-Pesa የተባለውን ታዋቂና አለም አቀፍ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎቱን በኢትዮጵያ ለመጀመር የብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት መመሪያ ማሻሻያ እስኪደረግበትና ፈቃድ እስኪሰጠው በመጠበቅ ላይ እንደነበር ይታወሳል።

via - አዲስ ዘይቤ
• @ThinkAbyssinia •
4.0K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 18:00:26
የኢትዮጵያ የእንቁላል የነፍስ ወከፍ ፍጆታ በዓመት 7 እንቁላል ነው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የእንቁላል የነፍስ ወከፍ ፍጆታቸው ሰባት እንቁላሎች ብቻ መሆኑ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው ጥናት አመላከተ። ከአፍሪካ አማካኝ ዓመታዊ የእንቁላል ፍጆታ አንፃር ሲታይም በ37 እንቁላሎች እንደሚያንስ ተጠቁሟል፡፡ የዶሮ ስጋ ፍጆታም በዓመት አንድ ኪሎ እንኳን ሳይሞላ 0.8 ኪ.ግ ብቻ መሆኑም ታውቋል።

በኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት ከ15 እስከ 17 በመቶ ድርሻ እንዳለው ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ቁጥርም በአፍሪካ አንደኛ እንዲሁም በዓለም ሰባተኛ ደረጃን የያዘች አገር ነች፡፡ አገሪቱ እምቅ የእንስሳት ሃብት ቢኖራትም ዜጎቿ በዓመት ማግኘት የሚገባቸውን የእንስሳት ተዋፅዖ እያገኙ አንዳልሆነ የተደረጉ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

የአገሪቱ የወተት ዓመታዊ የፍጆታ መጠን በዓመት 70 ሊትር ሲሆን የዓለም ጤና ድርጅት የአንድ ሰው ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ወደ 2 መቶ ሊትር ከፍ ማለት እንዳለበት ይመክራል፡፡ በእንስሳት ተዋፅዖዎች ላይ የሚታየው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ዜጎች ምረቶቹን ይበልጥ እንዳይጠቀሙ ማድረጉን የህብሩት ስራ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡

via - ባላገሩ ቲቪ
• @ThinkAbyssinia •
5.4K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 17:07:19
በመዲናዋ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁለት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት ተፈረመ

የመጀመሪያው ከ6 ነጥብ 1ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት ፕሮጀክትና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የሚገነቡ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ግንባታ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በመዲናዋ አስተማማኝ የግብርና ምርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያግዝና ገበያውን በማረጋጋት ለአምራቹ እና ለሸማቹ ተመጣጣኝ ምርቶች እንዲቀርቡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁለተኛው በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በሆነ ወጪ የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግ በተያዘው ቁርጠኝነት የሚገነባው የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ የB+G+8 ፕሮጀክት ግንባታ መሆኑ ተመላክቷል። ፕሮጀክቶቹ ኦቪድ ግሩፕ እና በተስፋዬ ኃይሌ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ይገነባሉም ተብሏል። የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በታቀደው ጊዜ ገደብ በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ ከንቲባ አዳነች አሳስበዋል።

via - mayor office of Addis Ababa 
• @ThinkAbyssinia •
5.9K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 11:27:05
ሳፋሪኮም በአዲስ አበባ የቴሌኮም አገልግሎት በይፋ አስጀመረ።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሳኡሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣  ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴሌኮም ኩባንያ በርካታ ቅድመ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሳፋሪኮም ትልቅ ሚና ይኖረዋል ያሉት ስራ አስፈጻሚው፣ ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር በጋራ በመስራት በሁሉም ቦታ ተደራሽ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል። የሳፋሪኮም ቴሌኮምኒኬሽን ኢትዮጵያ ምርቃት ስነስርዓት ላይ ለመታደም የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶም  አዲስ አበባ መግባታቸው ተሰምቷል።

ሳፋሪኮም ለደረሰበት ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮ ቴሌኮም እገዛ ትልቅ መሆኑን በመግልጽ አመስግነዋል።  ኩባንያው ባለፉት ሳምንታት በድሬዳዋ፣ በባህርዳር፣ በአወዳይ፣ ጎንደር ፣ሞጆ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ሀረር፣ ቢሾፍቱና ደብረ ብርሃን የኔትዎርክ ሙከራ አገልግሎቱን መጀመሩ ይታወሳል።

via - ENA
• @ThinkAbyssinia •
8.2K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 18:46:46
የዓለም ንግድ መጠን በእጅጉ እንደሚቀንስ የዓለም ንግድ ድርጅት በትንበያው አመለከተ።

የዓለም ንግድ ድርጅት የዓለም ኢኮኖሚ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ በ2023 የሚኖረው የዓለም ንግድ መጠን በእጅጉ እንደሚቀንስ በትንበያው አመላክቷል፡፡ የድርጅቱ ኢኮኖሚስቶች ጥናት እንደሚያመለክተው፤ በዚህ አመት የንግድ መጠኑ በ3 ነጥብ 5 በመቶ የሚያድግ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከተጠበቀው ትንሽ ከፍ ያለ ነው ተብሏል። ጥናቱ በ2023 የሚኖረው ዓለም አቀፍ የንግድ መጠን በአንድ በመቶ ብቻ እንደሚገደብና ይህም በሚያዝያ ወር ከነበረው የ3.4 በመቶ ትንበያ በእጅጉ እንደሚቀንስ አመላክቷል፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ በቅረቡ በጄኔቫ በተካሄደው ዓለም አቀፉ የንግድ ፎረም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር “ወደ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ድቀት ከመግባታችን በፊት ስለ ማገገም ማሰብ መጀመር አለብን ፤እድገትን መመለስ አለብን” ሲሉ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡

via - Al ain
• @ThinkAbyssinia •
10.0K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ