Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-10-04 09:05:46 ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል

በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል።

ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው ?

ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችን በተንጣለለ ስፍራ ላይ ቢያሳርፍም 80 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ከ4ሺህ በላይ በሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና ባሸበረቁ አበቦች የተሸፈነ ስፍራ በመሆኑ አረንጓዴነቱ ጎልቶ ይታያል።

ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

የአትክልት ስፍራዎቹ ጎብኚዎች አረፍ ብለው ንፋስ የሚቀበሉባቸው ምቹ መቀመጫዎችን እንዲሁም በጥበብ ስራዎች የሚዝናኑባቸውን የስነ ጥበብና የመዝናኛ ቦታዎችን የያዙ ናቸው።

ትልቁ ህንጻ ከ15ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ነው።

via - EBC
• @ThinkAbyssinia •
9.0K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 09:05:36
8.5K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 19:47:01
አንድ ኢትዮጵያዊ በዓመት በአማካይ 4 ኪሎ ግራም ስጋ ብቻ እንደሚመገብ ተነገረ

ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ሃብት ብዛት በአለም አስረኛ ደረጃ ላይ የምትቀመጥ በአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዝ ብትሆንም በምእራብ አፍሪካ ካሉ ሃገራት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ የሆነ የሥጋ ምርትና አቅርቦት እንዳላት ይነገራል፡፡ በአሁኑ ወቅት አንድ ኢትዮጵያዊ በዓመት በአማካይ 4.06 ኪሎ ግራም ስጋን ብቻ እንደሚመገብ የሥጋ ቆዳና ሌጦ ዴስክ ኃላፊ አቶ በርሄ አስመላሽ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ለምርቱና አቅርቦቱ ማነስ ምክንያት ተብለዉ ከተለዩት ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ዘመናዊ የከብት እርባታ ስርዓትን እንደ ሌሎች ሀገራት ተግባራዊ አለማድረግ ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በ2014 በጀት አመት 505 ሺህ ቶን ስጋ ለሃገር ውስጥ ፍጆታ እንዲውል ታስቦ ቢመረትም የዜጎችን የሥጋ ምርት ፍላጎት ማሟላት ሳይቻል ቀርቷል። የሥጋ ምርትን ለማሳደግ መንግስት እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ በርሄ የሀገረሰብ እንስሳቶችን  በሰው ሰራሽ ዘዴ ዝርያቸውን ለማሻሻልና ችግሩን ለመቅረፍ ታስቧል ሲሉ አክለዋል፡፡

ከፍተኛ የሆነው የእንስሳት ቁጥር በአርብቶ አደሮች አካባቢ የሚገኝ እንደመሆኑ ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲውሉ መደረጋቸው ሌላኛው የችግሩ መንስኤ መሆኑን አንስተው እንስሳቱን ለዚሁ አላማ እንዲውሉ ለማድረግ በተለያዩ የኢትዮጲያ ክፍሎች የእንስሳት እርባታ ማዕከላትን ለሟቋቋም እቅድ ተይዟል።

via - bisrat fm
• @ThinkAbyssinia •
7.0K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 19:00:04
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጠች።

የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ጠቅላላ ጉባኤውን በሮማኒያ ቡካሬስት አካሂዷል። ጉባኤው ድርጅቱን በቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ቢሮ ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩትን ዶረን ቦግዳንን ዋና ፀሃፊ አድርጎ መርጧል።

በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የተገኙት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ኢትዮጵያ በቴሌኮም ልማት ዘርፍ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በዘርፉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እየሰራቻቸው ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ለጉባኤው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ያረጋገጡት አምባሳደሩ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ላይ ያተኮረ የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ፣ የቴሌኮም ዘርፉን በከፊል ወደ ግል የማዞር ስራዎች እና ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

via - FBC
• @ThinkAbyssinia •
7.2K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 18:26:31
የምንዛሬ መናር የከተማ አስተዳደሩ በሚያስገነባው የጋራ ቤቶች ልማት ላይ እንቅፋት መፍጠሩ ተነገረ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ሲሲኢሲሲ) ጋር በመተባበር 1ሺህ 876 ቤቶችን ለማስገንባት ከሰባት ወራት በፊት የጀመረውን ውል በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርተር ዘግቧል። በዉሉ መሰረት ኮርፖሬሽኑ ከራሱ በቅድሚያ 500 ሚሊዮን ዶላር በማውጣት ቤቶቹን ገንብቶ ለቢሮ ለማስተላለፍና ከዚያም ቢሮው ቤቶቹን ለመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ለመሸጥ ከሰባት ወራት በፊት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ነገር ግን ፕሮጀክቱ አሁንም በሁለት ዋና ዋና አከራካሪ ነጥቦች ምክንያት ዘግይቷል። የመጀመሪያው ኮርፖሬሽኑ የጠየቀው ዋጋ በከተማው ቤቶች አስተዳደር ከሚቀርበው አማካይ ዋጋ በብዙ እጥፍ በልጦ በመገኘቱ ነው። በዚህም የተነሳ አሃዙን ለመቀነስ ድርድር ላይ መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ሁለተኛው ዋነኛ ችግር የምንዛሪ መለዋወጥ ጉዳይ ነው። ሲሲኢሲሲ ገንዘቡን በዶላር እንዲከፈለው ቢጠይቅም የከተማው አስተዳደር ውሉን ማክበር አልቻለም። ቢሮው ከአጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ 30 በመቶውን በዶላር እንዲሁም ቀሪውን 70 በመቶውን በብር ለመክፈል የጠየቀ ሲሆን በኮርፖሬሽኑ ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ ምናልባት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ስምምነቱ ሊፈፀም እንደሚችል ሪፖርተር በቢዝነስ አምዱ አስነብቧል።

የቻይናው ሲሲኢሲሲ የድሬዳዋ ኢንደስትሪ ፓርክን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት ተሳትፏል። ኩባንያው እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች አካል ሆኖ ቆይቷል። ነገር ግን በቤቶች ልማት ፕሮጀክት ሲሰማራ ይህ የመጀመሪያው ነው።

• @ThinkAbyssinia •
7.3K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 14:10:30
የኢትዮጵያ የኢ-ኮሜርስ ኤክስፖርትን ማሻሻል በሚቻልበት መንገድ ከአሊባባ ጋር ውይይት ተካሄደ።

በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ የኢ-ኮሜርስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው አሊባባ ከኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ባለድርሻ አካላት ጋር በቤጂንግ ኤምባሲ ባሳለፍነው ሳምንት በነበረ ዝግጅት ላይ የኤክስፖርት ምርቶች ለአለም አቀፍ ገበያ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያን ቡና በቻይና ገበያ በስፋት ለማስተዋወቅ የሚያስችል የመግባቢያ ሥምምነት የተፈረመ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያን የውጭ ንግድ ምርቶች የኢ-ኮሜርስ ግብይት ተደራሽነትን የበለጠ ለማሳደግ ከአሊባባ ጋር ያለውን ግንኙነት ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የልዑካን ቡድኑ ምክትል ኃላፊ አምባሳደር ደዋኖ ከድር ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው በቻይና የኢትዮጵያ የቡና ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው የባለስልጣኑ ፅህፈት ቤት ከአሊባባ ጋር በቅርበት በመስራት የኢትዮጵያን ጥቅም እውን ለማድረግ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

• @ThinkAbyssinia •
8.6K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 13:05:37
ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በመጪው ሕዳር ወር ላይ በሚዘጋጀው ዓለም ዓቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ላይ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አሳውቀዋል። አክለውም እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማዕድን ዘርፍ እድገት ዋና ባለድርሻ ናቸውም ብለዋል።

የማዕድን ዘርፉ የብዙዎችን ትብብር ይጠይቃል ያሉት ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ እንዲሁም ከአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ጋር በማዕድን ዘርፍ ከአየር መንገዱ ጋር በትብብር በምንሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረናል ብለዋል።

• @ThinkAbyssinia •
8.5K views10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 12:06:13
የአፍሪካ ባንኮች ዓመታዊው የደረጃ ምዘና ሪፖርት ይፋ ሆነ።

የአፍሪካ ባንኮችን በየዓመቱ በመመዘንና ደረጃ በመስጠት የሚታወቀው አፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት እ.ኤ.አ. የ2022 ዓመት ሪፖርቱንና ምርጥ ያላቸውን አንድ መቶ የአፍሪካ ባንኮች ዘርዝሮ ከሰሞኑ ይፋ ማድረጉን ሪፖርተር ዘግቧል። በዚህ ዓመታዊ ሪፖርት ውስጥ ውስጥ ሁለት የኢትዮጵያ ባንኮች ብቻ ተካተዋል።

መጽሔቱ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከአንድ መቶ አፍሪካ ባንኮች ውስጥ ስማቸውን በሰንጠረዥ ውስጥ ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ ባንኮች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዋሽ ባንክ ናቸው፡፡ በ2021 ሪፖርቱ ላይም ከመቶዎቹ ቀዳሚ ባንኮች ውስጥ እነዚሁ ሁለት የኢትዮጵያ ባንኮች ተካተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ2022 የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 31ኛ አዋሽ ባንክ ደግሞ 91ኛ ደረጃ ላይ ማገኘታቸው ታውቋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁለት ባንኮች የዘንድሮ የተቀመጡበት ደረጃ ባለፈው ዓመት አግኝተውት ከነበረው ደረጃ ዝቅ ያለ መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል። የመጽሔቱ ዋነኛ መመዘኛ ተደርጎ የሚወሰደው የባንኮች የካፒታል መጠን ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባንኮች በዘንድሮው ሰንጠረዥ ከደረጃው ዝቅ ያሉትም ከዚሁ ካፒታል ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

• @ThinkAbyssinia •
8.7K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 10:38:19
የንብረት ታክስ ጉዳይ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባዔ ቀዳሚ አጀንዳ ይሆናል ተባለ

መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዓመታዊ የጋራ ጉባዔ እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በዕለቱም የንብረት ታክስ የመሰብሰብ ሥልጣንን አስመልክቶ የውሳኔ ሐሳብ ለሁለቱ ምክር ቤቶች እንደሚቀርብ፣ ምክር ቤቶቹም በዕለቱ ወይም በማግሥቱ ውሳኔ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ  ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሁለቱ ምክር ቤቶች በሚያደርጉት የጋራ ጉባዔ ላይ የሚያቀርበውና የንብረት ታክስ በማን ይሰብሰብ የሚለውን የተመለከተ የውሳኔ ሐሳብ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን የምክር ቤቱ የፊስካል ጉዳዮችና የክልሎች የተመጣጠነ ዕድገት ጥናት ዳይሬክተር አቶ ዋቅቶሌ ዳዲ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡ ሁለቱ ምክር ቤቶች የየራሳቸውን የውሳኔ ሐሳብ የሚያዘጋጁ ቢሆንም፣ በጋራ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

ይሁንና ሁለቱ ምክር ቤቶች የሚያዘጋጇቸውን የውሳኔ ሐሳቦች በጋራ ጉባዔው ላይ ከማቅረባቸው በፊት፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎቻቸው ያፀድቃሉ፡፡ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚመለከተው ሲሆን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ይዞታል፡፡

• @ThinkAbyssinia •
8.7K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 09:10:03
ኢንቨስተሮች የሰብል ምርቶቻቸውን በስድስት ወራት ውስጥ ለገበያ እንዲያቀርቡ ግዴታ ተጣለባቸው

ወደ ውጭ የሚላኩ የሰብል ምርቶች የመሸጫ ዋጋቸው ከፍ ይላል በሚል ግምት ተጨማሪ ትርፍ ለማግኘት በመጋዘን ውስጥ እየተከማቹ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚገልጸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ኢንቨስተሮች በራሳቸው ማሳ ከሚያመርቱትም ሆነ በኮንትራት እርሻ የሚያገኙትን ምርት በስድስት ወራት ውስጥ ለገበያ እንዲያቀርቡ ግዴታ መጣሉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ ምርታቸውን ያላስመዘገቡም ሆኑ አስመግበው ለገበያ ያላቀረቡ ኢንቨስተሮች፣ በቀጣዩ የምርት ዘመን ምርታቸውን ማስመዝገብም ሆነ ወደ ውጭ መላክ እንደማይችሉ ጠቁሟል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ኢንቨስተሮቹ በራሳቸው ማሳ ካመረቱት ወይም በኮንትራት እርሻ ካስመረቱት ምርት ውጪ ለገበያ ማቅረብ፣ ማጓጓዝ ወይም ማከማቸት እንደማይችሉ ተደንግጓል፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን መመርያ ያወጣው በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የተመረቱ ምርቶች ግብይት ሥርዓት ውስጥ የሚታዩ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል፣ እንዲሁም በውድድር ላይ የተመሠረተ የግብይትን ሥርዓት ለማሳለጥ በመፈለጉ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ይህንን አሠራር በመዘርጋትም ከኤክስፖርት ምርቶች የውጭ ገበያ የሚገኘውም ገቢ የማሳደግ ዓላማ አለው፡፡

• @ThinkAbyssinia •
9.3K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ