Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-10-02 19:57:41
ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ የኦንላይን የስርጭት አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

መንግስታዊው የኮምኒኬሽን ተቋም  ኢትዮ ቴሌኮም "ሊድ" በተሰኘው በአዲሱ የሶስት አመት ስትራቴጂ ውስጥ የኦንላይን የሙዚቃ እና ቪዲዮ ስርጭት ለመጀመር ማቀዱን ሪፖርተር ዘግቧል።

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ መሪነት በቅርቡ ይጀምራል የተባለው የኦላይን ስርጭት አገልግሎቱ አለምአቀፍ እና ሀገራዊ ሙዚቃዎች፣ የድምጽ መረጃዎች፣ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችና ቶክ ሾዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ሌሎች አገልግሎቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት ለተጠቃሚዎች ይፋ ይደረጋሉ የተባለ ሲሆን ደንበኞች በአንድ መሳሪያ ላይ ከአንድ በላይ አገልግሎት እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸው የኤሌክትሮኒክስ ስማርት ካርድ (ኢሲም) ኩባንያው በቅርቡ ካስጀመራቸው አገልግሎቶች ተጠቃሹ ነወ።

• @ThinkAbyssinia •
11.1K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 15:34:51
ለኢንተርፕራይዞች 200 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የብድር በጀት ተፈቀደ

ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ዶላር የብድር በጀት መያዙን የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክትን ዋቢ በማድረግ አዲስ ማለዳ ዘግቧል። በጀቱ የተገኘው ከዓለም ባንክ በብድር ሲሆን፣ ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ ለመደገፍ ከተያዘው መስከረም ወር ጀምሮ ለሦስት ዓመት ተግባራዊ ይሆናልም ነው የተባለው።

ብድሩ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ሆኖ፣ የተፈቀደውን ብድር በሊዝ ፋይናንስ እና በሥራ ማስኬጃ ብድር ለመስጠት የቢሮ ሥራዎች ብቻ እንደሚቀሩ ተገልጿል። ብድሩን በአምራችነት ዘርፍ የተሰማሩና በአነስተኛና መካከለኛ ምድብ ውስጥ የሚገኙ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ኢንተርፕራይዞች እንደሚያገኙ ነው የተባለው።

• @ThinkAbyssinia •
2.2K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 08:10:11
"ከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ሰሞኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ካደረገ ወዲህ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚደረግ ጥቆማ የደረሰው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በታለመለት የነዳጅ ድጎማ የታቀፉ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል በወጣላቸው ታሪፍ ብቻ ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም ያለው ሚኒስትሩ ህብረተሰቡ ይህን አውቆ መንግስት ካስቀመጠው ታሪፍ ውጪ ባለመክፈል ተባባሪ እንዲሆን ጠይቋል።

በተጨማሪም ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ የማይወጡ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ላሉ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ መብቱን እንዲያስከብር ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መልዕክት ተላልፏል።

• @ThinkAbyssinia •
6.7K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:12:50
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ማንኛውንም የሰው ልጅ ስራ ሊሰራ የሚችል ሮቦት ይፋ አደረገ።

በዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ኤሎን መስክ የሚዘወረው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ሞተርስ በትላንትናው የኤአይ(AI) ቀን ዝግጅቱ ላይ ኦፕትመስ የተሰኝውን ሰው መሳይ ሮቦት ይፋ አድርጓል።

ለእይታ የቀረበው ሮቦቱ እንደ ሰው ማሰብ የሚችልና እንደ ሰው የተለያዩ  ስራዎች መስራት የሚችል ነው ተብሏል። የቴስላ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢለን መስክ በመድረኩ ባደረገው ንግግር ይህ ሮቦት በብዛት መመረት ቢጀምር ዋጋው ከ20,000$ ዶላር በታች ነው ብሏል። ኤአይ(AI) ቀን የተሰኘው ዝግጅትም ዋና አላማው በ ዓለም አቀፍ ደረጃ በ ሮቦቲክስ ተስጦ ያላቸው ወጣቶች ተስላን ተቀላቅለው እንዲሰሩ ጥሪ የሚቀርብበት ነው።

• @ThinkAbyssinia •
10.2K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 10:14:27
ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማ ተግባራዊ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለው ወቅታዊ የኑሮ ውድነት ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማ አበል እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አዲስ ማለዳ ዘግባለች። የመንግሥት ሠራተኞች የሚያነሱትን የኑሮ ውድነት ለማቃለል እንዲቻል የቤት ኪራይ ድጎማ፣ ሙያዊ የሥራ ኃላፊነት አበል፣ የሞባይል ካርድና የትራንስፖርት አበል ጭማሪ እንዲደረግ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ነሐሴ 27/2014 የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉ ታውቋል። ሆኖም የቤት ኪራይ ድጎማና አበል ክፍያ ቀደም ሲል የተፈቀደላቸው የሥራ መደቦችን አያካትትም።

የኃላፊነት አበል ክፍያ ተፈጻሚ የሚሆነውም በሆስፒታል እና ጤና ጣቢያዎች በሥራ ኃላፊነት ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች ነው። ሰነዱ አክሎም የትራንስፖርት አበል ተፈጻሚ የሚሆነው በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በሆስፒታልና ጤና ጣቢያ ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ላይ ነው። የሞባይል ስልክ ክፍያ አበል ተፈጻሚ የሚሆነው በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ደረጃ መሆኑን መረጃው ያትታል።

የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች  ደሞዛቸው ከ4 ሺሕ ብር በታች ለሆነ ሠራተኞች የቤት ኪራይ 1 ሺሕ 500 ብር ጭማሬ አድርጓል። ደሞዛቸው ከ4 ሺሕ ብር በላይ ለሆነ ሠራተኞችም ከተደረገው የቤት ኪራይ ድጎማ በተጨማሪ፣ ለጽዳትና የጥበቃ ሠራተኞች እንደየሁኔታው የወተት አበል ተብሎ ተጨማሪ ብር ያገኛሉ።የተፈቀደው የቤት ኪራይ ድጎማ አበል እና የጥቅማ ጥቅም አበል ክፍያ ከሥራ ግብር ነጻ ነው።

• @ThinkAbyssinia •
10.5K views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 09:30:04
ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በአንድ ዳቦ 36 ሳንቲም እየከሰረ ለገበያ እያቀረበ መሆኑ ተገለጸ።

በቀን 1.3 ሚሊዮን ዳቦ ለተጠቃሚዎች የሚያደርሰው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ እያንዳንዱ ዳቦ 36 ሳንቲም እንደሚያከስረው የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የምርት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አካለወልድ አድማሱ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል። መጀመሪያ ከነበረው የዳቦ መሸጫ የዋጋ ማስተካከያ ከተደረገም በኋላም ይህ ኪሳራ ቀጥሏል ብለዋል።

ፋብሪካው ከተያያዥ ኪሳራና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች ጋር በተያያዘ ለአንድ ወር የምርት ሂደቱን ካቋረጠ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ዳቦ የሚያደርገውን ድጎማ እስከ አንድ ብር ከአስራ አራት ሳንቲም ድረስ ከፍ ማድረጉን ተከትሎ፤ አንዱ ዳቦ ይሸጥ ከነበረበት የአንድ ብር ከኻያ ሳንቲም ዋጋ ወደ ኹለት ብር ከአስር ሳንቲም ዋጋ ከፍ ቢልም ኩባንያው አሁንም ከኪሳራ አላመለጥኩም ብሏል።

ዳቦዎችን ከማምረትም ባለፈ በየሰፈሩ ተደራጅተው የዳቦ ሽያጩን ለሚያካሂዱት ወጣቶች የማድረሱን ሥራ የሚሠራው ፋብሪካው፣ ዳቦ የሚያጓጉዙ መኪናዎች እጥረትና የመለዋወጭ ችግሮች እንዳሉበት የተሰማ ሲሆን፣ መኪናዎችን በመጨመርና መለዋወጫዎችንም በማሟላት ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ አካለወልድ ጨምረው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

• @ThinkAbyssinia •
9.9K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 12:11:50
ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ አይሸሽም ተካ “የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢዩልደርስ አዋርድስ” ሽልማትን አሸነፉ።

12ኛው አፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢዩልደር ፎረምና አዋርድስ  “በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ዘመን የኢኮኖሚ ውህደት” በሚል መሪ ቃል ትናንት ማምሻውን በኮትዲቭዋር አቢጃን ሲካሄድ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ አይሸሽም ተካ በኢትዮጵያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት በምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ላደረጉት አበርክቶ ሽልማት አግኝተዋል።

ባለሀብቱ ሽልማቱን ከቀድሞ የኮትዲቭዋር ጠቅላይ ሚኒስትር ፓስካል አፊ ንጉዌሳን እጅ ተቀብለዋል። አቶ አይሸሽም ተካ በቀን ሰራተኝነት ሰባት ብር ደመወዝ ተቀጥረው ስራን ሳይንቁ በመስራት ወደ ባለሀብትነት የተሸጋገሩ ሰው መሆን መቻላቸው በሽልማቱ ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል።

ላለፉት 15 ዓመታት ኑሯቸውን በደቡብ ሱዳን በማድረግ የተለያዩ የንግድ ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙት ባለሀብቱ በጁባ ቆይታቸው በሰላም፣ ልማትና ሰብአዊ ድጋፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እ.አ.አ በ2019 ከደቡብ ሱዳን መንግስት የክብር ዜግነት እንደተሰጣቸው ኢዜአ ዘግቧል።

• @ThinkAbyssinia •
12.0K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 17:52:57
በ1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የተገነባው የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ተመረቀ።

ፒሲኢ ቬንቸር ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ ኢንዱስተሪያል ፓርክ ውስጥ በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የገነባውን የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት የኢንዱስትሪ ሚንስትር መላኩ አለበል በተገኙበት አስመርቋል።

ድርጅቱ የኢትዮጵያን ምርት በዓለም ገበያ ላይ እንዲተዋወቅ በማድረግ ሜዲን ኢትዮጵያ በሚል ምርት በማምረት የአገሪቱን ኢንቨስትመንት በተለይ ደግሞ የቆዳ ውጤቶችን በማስተዋወቅ ረገድ እንደ አምባሳደር ሆኖ እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በምርቃቱ ላይ ፒሲኢ ቬንቸር ማኑፋክቸሪንግ ከአንድ መቶ ሰማንያ በላይ ወጣት ወንድና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉ የተነገረ ሲሆን በአሁንም ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠርና በቀጣይ አስር ዓመት ከዘርፉ እስከ አንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ገበያ ለማስገባት አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

• @ThinkAbyssinia •
3.1K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 17:52:26 Think አቢሲንያ pinned a GIF
14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 17:51:56
ኪያድ ዳቦ እና ኬክ
Kiyad Bakery and Coffee

ለልደት፣ ለሰርግ እና ለምርቃት በፈለጉት ዲዛይን እና መጠን እናዘጋጃለን።

Bring us your cake designs! We prepare cakes for every occasion!

0911467026
0913911679

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

https://t.me/kiyad_bakery

አድራሻ: ልደታ ፍሊንት ስቶን አካባቢ
      የልደታ የፍታብሔር ምድብ ችሎት ፊት ለፊት

https://maps.app.goo.gl/4hYtermcawkxksDH7
3.0K viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ