Get Mystery Box with random crypto!

ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማ ተግባራዊ ተደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለው | Think Abyssinia

ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማ ተግባራዊ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለው ወቅታዊ የኑሮ ውድነት ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማ አበል እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አዲስ ማለዳ ዘግባለች። የመንግሥት ሠራተኞች የሚያነሱትን የኑሮ ውድነት ለማቃለል እንዲቻል የቤት ኪራይ ድጎማ፣ ሙያዊ የሥራ ኃላፊነት አበል፣ የሞባይል ካርድና የትራንስፖርት አበል ጭማሪ እንዲደረግ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ነሐሴ 27/2014 የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉ ታውቋል። ሆኖም የቤት ኪራይ ድጎማና አበል ክፍያ ቀደም ሲል የተፈቀደላቸው የሥራ መደቦችን አያካትትም።

የኃላፊነት አበል ክፍያ ተፈጻሚ የሚሆነውም በሆስፒታል እና ጤና ጣቢያዎች በሥራ ኃላፊነት ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች ነው። ሰነዱ አክሎም የትራንስፖርት አበል ተፈጻሚ የሚሆነው በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በሆስፒታልና ጤና ጣቢያ ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ላይ ነው። የሞባይል ስልክ ክፍያ አበል ተፈጻሚ የሚሆነው በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ደረጃ መሆኑን መረጃው ያትታል።

የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች  ደሞዛቸው ከ4 ሺሕ ብር በታች ለሆነ ሠራተኞች የቤት ኪራይ 1 ሺሕ 500 ብር ጭማሬ አድርጓል። ደሞዛቸው ከ4 ሺሕ ብር በላይ ለሆነ ሠራተኞችም ከተደረገው የቤት ኪራይ ድጎማ በተጨማሪ፣ ለጽዳትና የጥበቃ ሠራተኞች እንደየሁኔታው የወተት አበል ተብሎ ተጨማሪ ብር ያገኛሉ።የተፈቀደው የቤት ኪራይ ድጎማ አበል እና የጥቅማ ጥቅም አበል ክፍያ ከሥራ ግብር ነጻ ነው።

• @ThinkAbyssinia •