Get Mystery Box with random crypto!

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በአንድ ዳቦ 36 ሳንቲም እየከሰረ ለገበያ እያቀረበ መሆኑ ተገለጸ። በቀን | Think Abyssinia

ሸገር የዳቦ ፋብሪካ በአንድ ዳቦ 36 ሳንቲም እየከሰረ ለገበያ እያቀረበ መሆኑ ተገለጸ።

በቀን 1.3 ሚሊዮን ዳቦ ለተጠቃሚዎች የሚያደርሰው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ እያንዳንዱ ዳቦ 36 ሳንቲም እንደሚያከስረው የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የምርት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አካለወልድ አድማሱ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል። መጀመሪያ ከነበረው የዳቦ መሸጫ የዋጋ ማስተካከያ ከተደረገም በኋላም ይህ ኪሳራ ቀጥሏል ብለዋል።

ፋብሪካው ከተያያዥ ኪሳራና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች ጋር በተያያዘ ለአንድ ወር የምርት ሂደቱን ካቋረጠ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ዳቦ የሚያደርገውን ድጎማ እስከ አንድ ብር ከአስራ አራት ሳንቲም ድረስ ከፍ ማድረጉን ተከትሎ፤ አንዱ ዳቦ ይሸጥ ከነበረበት የአንድ ብር ከኻያ ሳንቲም ዋጋ ወደ ኹለት ብር ከአስር ሳንቲም ዋጋ ከፍ ቢልም ኩባንያው አሁንም ከኪሳራ አላመለጥኩም ብሏል።

ዳቦዎችን ከማምረትም ባለፈ በየሰፈሩ ተደራጅተው የዳቦ ሽያጩን ለሚያካሂዱት ወጣቶች የማድረሱን ሥራ የሚሠራው ፋብሪካው፣ ዳቦ የሚያጓጉዙ መኪናዎች እጥረትና የመለዋወጭ ችግሮች እንዳሉበት የተሰማ ሲሆን፣ መኪናዎችን በመጨመርና መለዋወጫዎችንም በማሟላት ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ አካለወልድ ጨምረው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

• @ThinkAbyssinia •