Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ አይሸሽም ተካ “የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢዩልደርስ አዋርድስ” ሽልማትን አሸነ | Think Abyssinia

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ አይሸሽም ተካ “የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢዩልደርስ አዋርድስ” ሽልማትን አሸነፉ።

12ኛው አፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢዩልደር ፎረምና አዋርድስ  “በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ዘመን የኢኮኖሚ ውህደት” በሚል መሪ ቃል ትናንት ማምሻውን በኮትዲቭዋር አቢጃን ሲካሄድ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ አይሸሽም ተካ በኢትዮጵያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት በምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ላደረጉት አበርክቶ ሽልማት አግኝተዋል።

ባለሀብቱ ሽልማቱን ከቀድሞ የኮትዲቭዋር ጠቅላይ ሚኒስትር ፓስካል አፊ ንጉዌሳን እጅ ተቀብለዋል። አቶ አይሸሽም ተካ በቀን ሰራተኝነት ሰባት ብር ደመወዝ ተቀጥረው ስራን ሳይንቁ በመስራት ወደ ባለሀብትነት የተሸጋገሩ ሰው መሆን መቻላቸው በሽልማቱ ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል።

ላለፉት 15 ዓመታት ኑሯቸውን በደቡብ ሱዳን በማድረግ የተለያዩ የንግድ ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙት ባለሀብቱ በጁባ ቆይታቸው በሰላም፣ ልማትና ሰብአዊ ድጋፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እ.አ.አ በ2019 ከደቡብ ሱዳን መንግስት የክብር ዜግነት እንደተሰጣቸው ኢዜአ ዘግቧል።

• @ThinkAbyssinia •