Get Mystery Box with random crypto!

በ1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የተገነባው የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ተመረቀ። ፒሲኢ ቬ | Think Abyssinia

በ1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የተገነባው የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ተመረቀ።

ፒሲኢ ቬንቸር ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ ኢንዱስተሪያል ፓርክ ውስጥ በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የገነባውን የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት የኢንዱስትሪ ሚንስትር መላኩ አለበል በተገኙበት አስመርቋል።

ድርጅቱ የኢትዮጵያን ምርት በዓለም ገበያ ላይ እንዲተዋወቅ በማድረግ ሜዲን ኢትዮጵያ በሚል ምርት በማምረት የአገሪቱን ኢንቨስትመንት በተለይ ደግሞ የቆዳ ውጤቶችን በማስተዋወቅ ረገድ እንደ አምባሳደር ሆኖ እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

በምርቃቱ ላይ ፒሲኢ ቬንቸር ማኑፋክቸሪንግ ከአንድ መቶ ሰማንያ በላይ ወጣት ወንድና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉ የተነገረ ሲሆን በአሁንም ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠርና በቀጣይ አስር ዓመት ከዘርፉ እስከ አንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ገበያ ለማስገባት አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

• @ThinkAbyssinia •