Get Mystery Box with random crypto!

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ማንኛውንም የሰው ልጅ ስራ ሊሰራ የሚችል ሮቦት ይፋ አደረ | Think Abyssinia

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ማንኛውንም የሰው ልጅ ስራ ሊሰራ የሚችል ሮቦት ይፋ አደረገ።

በዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ኤሎን መስክ የሚዘወረው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ሞተርስ በትላንትናው የኤአይ(AI) ቀን ዝግጅቱ ላይ ኦፕትመስ የተሰኝውን ሰው መሳይ ሮቦት ይፋ አድርጓል።

ለእይታ የቀረበው ሮቦቱ እንደ ሰው ማሰብ የሚችልና እንደ ሰው የተለያዩ  ስራዎች መስራት የሚችል ነው ተብሏል። የቴስላ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢለን መስክ በመድረኩ ባደረገው ንግግር ይህ ሮቦት በብዛት መመረት ቢጀምር ዋጋው ከ20,000$ ዶላር በታች ነው ብሏል። ኤአይ(AI) ቀን የተሰኘው ዝግጅትም ዋና አላማው በ ዓለም አቀፍ ደረጃ በ ሮቦቲክስ ተስጦ ያላቸው ወጣቶች ተስላን ተቀላቅለው እንዲሰሩ ጥሪ የሚቀርብበት ነው።

• @ThinkAbyssinia •