Get Mystery Box with random crypto!

'ከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ ' - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሰሞኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስ | Think Abyssinia

"ከታሪፍ ውጪ አትክፈሉ " - የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

ሰሞኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ካደረገ ወዲህ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚደረግ ጥቆማ የደረሰው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በታለመለት የነዳጅ ድጎማ የታቀፉ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል በወጣላቸው ታሪፍ ብቻ ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም ያለው ሚኒስትሩ ህብረተሰቡ ይህን አውቆ መንግስት ካስቀመጠው ታሪፍ ውጪ ባለመክፈል ተባባሪ እንዲሆን ጠይቋል።

በተጨማሪም ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ የማይወጡ አሽከርካሪዎች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ላሉ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ መብቱን እንዲያስከብር ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር መልዕክት ተላልፏል።

• @ThinkAbyssinia •