Get Mystery Box with random crypto!

ለኢንተርፕራይዞች 200 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የብድር በጀት ተፈቀደ። ለአነስተኛ እና መካከለኛ | Think Abyssinia

ለኢንተርፕራይዞች 200 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የብድር በጀት ተፈቀደ

ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ዶላር የብድር በጀት መያዙን የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክትን ዋቢ በማድረግ አዲስ ማለዳ ዘግቧል። በጀቱ የተገኘው ከዓለም ባንክ በብድር ሲሆን፣ ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ ለመደገፍ ከተያዘው መስከረም ወር ጀምሮ ለሦስት ዓመት ተግባራዊ ይሆናልም ነው የተባለው።

ብድሩ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ሆኖ፣ የተፈቀደውን ብድር በሊዝ ፋይናንስ እና በሥራ ማስኬጃ ብድር ለመስጠት የቢሮ ሥራዎች ብቻ እንደሚቀሩ ተገልጿል። ብድሩን በአምራችነት ዘርፍ የተሰማሩና በአነስተኛና መካከለኛ ምድብ ውስጥ የሚገኙ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ኢንተርፕራይዞች እንደሚያገኙ ነው የተባለው።

• @ThinkAbyssinia •