Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ የኦንላይን የስርጭት አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። መንግስታዊው የ | Think Abyssinia

ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ የኦንላይን የስርጭት አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

መንግስታዊው የኮምኒኬሽን ተቋም  ኢትዮ ቴሌኮም "ሊድ" በተሰኘው በአዲሱ የሶስት አመት ስትራቴጂ ውስጥ የኦንላይን የሙዚቃ እና ቪዲዮ ስርጭት ለመጀመር ማቀዱን ሪፖርተር ዘግቧል።

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ መሪነት በቅርቡ ይጀምራል የተባለው የኦላይን ስርጭት አገልግሎቱ አለምአቀፍ እና ሀገራዊ ሙዚቃዎች፣ የድምጽ መረጃዎች፣ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችና ቶክ ሾዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ሌሎች አገልግሎቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት ለተጠቃሚዎች ይፋ ይደረጋሉ የተባለ ሲሆን ደንበኞች በአንድ መሳሪያ ላይ ከአንድ በላይ አገልግሎት እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸው የኤሌክትሮኒክስ ስማርት ካርድ (ኢሲም) ኩባንያው በቅርቡ ካስጀመራቸው አገልግሎቶች ተጠቃሹ ነወ።

• @ThinkAbyssinia •