Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-26 09:34:56
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የእንኳን አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክትን ከምስሉ ይመልከቱ።

• @ThinkAbyssinia •
6.4K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:03:59
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የቦታውን ክብረ-ወሰን በመስበር አሸነፈች

አትሌቷ ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን  2:15:37 በሆነ ሰዓት በመግባት ያሸነፈች ሲሆን በዚህም በዓለም ሦስተኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበች ሴት አትሌት መሆን መቻሏን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በወንዶቹ ኬንያዊው የማራቶን ንጉስ ኪፕቾጌ ከአራት ዓመት በፊት በበርሊን ማራቶን ያሻሻለውን የማራቶን ሪከርድ በድጋሚ ዛሬ እዛው በርሊን አዲስ የማራቶን ሪከርድ በማስመዝገብ አሻሽሏል።

• @ThinkAbyssinia •
3.2K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:02:13
ኪያድ ዳቦ እና ኬክ
Kiyad Bakery and Coffee

ለልደት፣ ለሰርግ እና ለምርቃት በፈለጉት ዲዛይን እና መጠን እናዘጋጃለን።

Bring us your cake designs! We prepare cakes for every occasion!

0911467026
0913911679

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

https://t.me/kiyad_bakery

አድራሻ: ልደታ ፍሊንት ስቶን አካባቢ
      የልደታ የፍታብሔር ምድብ ችሎት ፊት ለፊት

https://maps.app.goo.gl/4hYtermcawkxksDH7
3.2K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:26:34 #ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና ታሳቢ በማድረግ፣ በቅጥር ገቢ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ እንዲቀንስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ አአቅርቧል፡፡ ለኑሮ ውድነቱ መንግሥትን ‹‹በጀት አውጥተህ ደጉም›› ማለት ስለማይቻል በሌሎችም አገሮች የኑሮ ውድነት ሲከሰት እንደሚደረገው ሁሉ የሥራ ግብር ምጣኔ እንዲቀነስ ኮርፖሬሽኑ ጠይቋል።

2፤ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት ለአፍሪካ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ጠየቀች።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት 77ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት በቂ ቦታ ሊሰጣትና ትክክለኛው የአፍሪካ ድምጽ ሊሰማ ይገባል ብለዋል። በመድረኩ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያካሄደች ላለችው ጥረት እውቅና እና ድጋፍ ሊሰጠው እንደሚገባም አንስተዋል።

3፥የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ እየዋለ ነው ተባለ።

ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው ተልዕኮ ውጪ ለሆነ የፖለቲካ ሥራ እንደሚውል፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በተመረጡ 61 ተቋማት ላይ ያደረገው የጥናት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ከመምህራን ልማትና ከአሠልጣኞች ምልመላ ጋር በተገናኘ፣ የዘመድና የፓርቲ አሠራር፣ እንዲሁም አድልኦና ጉቦ የመቀበል አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል ብሏል፡፡

4፤በሶማሊላንድ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተራዘመ።

በተገንጣይ ሶማሊላንድ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ “በቴክኒካል እና በፋይናንሺያል ምክንያቶች” መራዘሙን ምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ምርጫውን ለካሄድ የሚችልበትን ቀን ባይቆርጡም የሚካሄድበትን ጊዜ ግን በዘጠኝ ወራት አራዝሟል።

5፤የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን ያገኛል።

አስራ ስድስተኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚደረጉ መርሐ ግብሮች ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል። ለሶስተኛ ደረጃ በሚደረግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ከቀኑ 7:00 ላይ ሲጫወቱ ፈረሰኞቹ ለዋንጫው ከመቻል ጋር ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይፋለማሉ።

• @ThinkAbyssinia •
4.3K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:25:17 Think አቢሲንያ pinned a photo
08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 11:25:06
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን  እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ዪፈልጋሉ ፤ እንግዲያውንስ ይሄን ሊንክ ይጫኑ፡፡ከላይ ያሉትን የጫማዎች ዋጋ እና ብዙ አማራጮችን ለማግኘት  ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ


https://t.me/joinchat/AAAAAElITjwlFLHHO8h7Sg


ይዘዙ በውስጥ መስመር የመረጡትን ፎቶ  ይላኩልን በቀላሉ እናስተናግዳለን ግዜዎን ቆጥበን።
inbox 1         inbox2
    @businesslidu   @businesslidu2

online shopping is always a good idea!!
አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ መ/ም ኤድናሞል አደባባይ ዞሮ ሬድዋን ህንጻ ጎን ራክሲም ህንጻ 3ኛ ፎቅ በስተቀኝ ዞር ሲሉ ያገኙናል።

0919998383
በውስጥ መስመር ለመፃፍ    @businesslidu & @businesslidu2
4.0K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 09:06:32
ለሀገር የሚከፈል መስዋእትነት

ትናንት ምሽት በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ ፖርቹጋል ቼክ ሪፐብሊክን አራት ለባዶ ባሸነፈችበት ጨዋታ የቼክ ሪፐብሊኩ በረኛ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ከባድ ፋወል ሰርቶበት ከአፍንጫ ደም ሲፈስ ታይቷል።

ምንም እንኳን ደም እስከ መድማት የሚያደርስ ጉዳት በሮናልዶ ለይ በረኛው ቢያደርስበትም ሮናልዶ በተደረገለት ህክምና ጨዋታውን ቀጥሎ ለዲያጎ ጆታ ጎል ምርጥ አሲስት ማድረግ ችሏል።

• @ThinkAbyssinia •
5.6K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 07:59:33
በዎላይታ ብሔር ዘንድ የሚከበረው የጊፋታ ክብረ በዓል

"ጊፋታ" የእርቅ መሰረትና የሰላም ተምሳሌት ሲሆን በዓሉን በቁርሾና ጥላቻ ማክበር የማይቻል በመሆኑ በጊፋታ ፍቅር ይቀነቀናል፤ የጊፋታን በዓል በዓለም በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

በዎላይታ ብሔር ዘንድ የሚከበረው የጊፋታ ክብረ በዓል ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ በዓል ነው። መስከረም ወር በገባ ከ14-20 መካከል በሚውለው እሁድ ዕለት አዲሱን ዓመት በድምቀት ይቀበሉታል። ይህ እሁድ እለት የአዲስ ዓመት ቀን ሲሆን ስሙም "ሹሃ ወጋ" ይሰኛል ትርጉሙም የእርድ እሁድ እንደማለት ነው፡፡

ጊፋታ ማለት ባይራ (ታላቅ)፣ “መጀመሪያ” እንደ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ጊፋታ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡  ከቆጮ የሚሰራው “ባጭራ” የተባለው የሆድ መፍታቻ ምግብ ደግሞ ለበዓሉ ዋዜማ ይዘጋጃል፡፡

• @ThinkAbyssinia •
6.2K views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 21:31:35
የአርቲስት ጎሳኤ ተስፋዬ ልጅ፤ አሜን ጎሣዬ ተስፋዬ ደብተር ለመግዛት አቅም ለሌላቸው የገጠር ተማሪዎች ድጋፍ አደረገች

የአርቲስት ጎሳኤ ተስፋዬ ልጅ፤ አሜን ጎሣዬ ተስፋዬ ለገጠር ተማሪዎች በዘንድሮ የደብተር ማሰባሰብ እኔም የበኩሌን በማድረግ ግዴታዬን እወጣለው ብላ ከ500 በላይ ደብተር (50) ደርዘን በላይ ደብተር አቅም ለሌላቸው እኩያ ተማሪዎቿ እንዲደርስላት አበርክታለች።

በኩሉ በጎ አድራጎት የምናዉቀዉ ወጣት ያሬድ ወልደፃዲቅ (ያያ ዘልደታ)  ደብተሩን ተሰብስቦ አዲስ ዘመን ለሚባል  ገጠር አካባቢ ትምህርት ቤት እገዛ መደረጉን አስታውቋል።

• @ThinkAbyssinia •
8.7K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 21:20:34 የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ተቸግረዋል

(በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)

መስፍን ጌታቸው " ሰው ለሰው "ን ሲጀምር "ሎሚ ፒክቸርስ" የሚባል ድርጅት ነበረው። በሚወዳቸው እናቱ ስም ያቋቋመው ነው። ሎሚናት የእናቱ ስም ነው ።

አሁን ወ/ሮ ሎሚናት ገ/መስቀል ተቸግረዋል። አንድ የሚደግፋቸው ልጃቸው ትልቁ ደራሲ መስፍን ጌታቸው ሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም. ሞተባቸው ። መስፍኔ አንድ የማይደራደርበት መሀላ ነበረው ፤ " ሎሚናት ትሙት ! " የሚል ። እሳቸው ናቸው የተቸገሩት ። የተቸገሩት የሚኖሩበት ቤት ነው ። በወር 3,500 ብር የሚከፈልባት አንዲት ክፍል ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት ። ምንም ቋሚ ገቢ ለሌላቸው እናት በወር 3,500 ብር ማግኘት ጭንቅ ሆኖባቸዋል ።
"ልጄ ቤት ኪራዩ ከመቸው እንደሚደርስ አላውቅም " ነው ያሉኝ ።

ወ/ሮ ሎሚናት ከልጃቸው መስፍን ጌታቸው ሞት በኋላ በወዳጅ ጓደኞቹ ተረስተው ፣ ማንም " እንዴት ነው የሚኖሩት ? " የሚላቸው አጥተው የበጎ አድራጊዎችን እጅ እያዩ ለመኖር ተገደዋል ።

ልጃቸው መስፍን ጌታቸው ስለቋሚ ንብረት ሳያስብ ፣ በሰው እንደተከበበ ፣ ወዳጀ ብዙ ሆኖ ነው የኖረው ። እናቱ ግን አሁን ማንም ጠያቂ አጥተው በአንዲት 3 × 3 በሆነች ቤት ውስጥ ይኖራሉ ። እሷን ቤትም ከግለሰብ የተከራዩዋት ናት ። ከልጃቸው ጓደኞች ተዋናይት ረቂቅ ተሾመ እስካሁን በሁለት ዙር መቶ ሀያ ስምንት ሺህ ብር ልካ ሕይወታቸውን ከከፋ ውድቀት ታድጋለች ። ጣሊያን ሀገር የሚኖረው አብሮ አደግ ጓደኛው ባዩ ተሾመ የቻለውን እያደረገ የጓደኝነት ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል ። ሌሎች ጥቂት ወዳጆቹም መጠነኛ እገዛ አድርገዋል ።

እናት ሎሚናት መስፍኔ ካረፈ ዓመት ከአምስት ወር የኖሩት በዚህ ነው ። ወ/ሮ ሎሚናት የረቂቅ እና ባዩን ስም አንስተው አይጠግቡም ። ማንም ደጋፊና የእኔ የሚሉት ቤት የሌላቸው እናት በወር ይህቺኑ ኪራይ መክፈል አቅቷቸው በሰቀቀን ሕይወታቸውን እየገፉ ይገኛሉ ። እኚህ እናት ችግራቸውን ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲያቀርቡላቸው ለመስፍኔ የቅርብ ወዳጆች እየደወሉ ቢማፀኑም ማንም ይህን ሊያደርግላቸው አልቻለም ።

ሚዲያ ላይ ቀርበው ችግራቸውን ለመግለጽ ቢፈልጉና ቢሞክሩም ሆን ተብሎ በሚሰራ ተንኮል ይህም እንዳይሳካ ተደርጓል። በርካታ ችግረኛ ዜጎች በሚዲያው እየቀረቡ ሲታገዙ ብናይም የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ግን ለጥቂት ሰዎች ክብር ሲባል በኔትዎርክ የትም ሚዲያ ላይ እንዳይቀርቡና ከችግራቸው ጋር እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል።

እኔ ራሴ ለሁለት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ( አዘጋጆች ) አሳውቄ በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ እንዲዳፈን ተደርጓል ። ያሳዝናል ። እጅግ ልብ ይሰብራልም ። ጉዳዩ ብዙ ዝርዝር አሳዛኝ ገጽታ አለው ። ለጊዜው እንለፈው ። ለዚህ ነው  ወደዘጋሁት የፌስቡክ ገጽ ያለጊዜዬ እንድመለስ የተገደድኩት ። ለምን ይህ በደል ይሰራል ? ትናንት መስፍን ጌታቸው በሕይወት ነበረ ፤ ዛሬ የለም ። ነገ ደግሞ የቀን ጉዳይ ካልሆነ ሁላችንም የለንም ።

ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ፦
****

እኔ አይደለሁም ይህን የምለው ። " ልጄ ልጄ እንደምንም ችግሬን ለአዳነች አቤቤ የሚያደርስልኝ ቢገኝ ደሳሳ ማዕድ ቤት እንኳ ብትሰጠኝ አጽድቼ እገባበታለሁ ። ቤት ኪራዩን አልቻልኩትም ። ከመቼው አለፈ ሳልለው ወሩ ይደርሳል ። ምን ላድርግ ? ጨነቀኝ ። ሰዎች የሚሰጡኝን ለሆዴ ላድርገው ለቤት ኪራይ ? እንደው ለአዳነች ብትነግሩልኝ አትጨክንብኝም ።

ቢሮዋ የሚወስደኝ ባገኝ እግሯ ስር ወድቄ በተማጸንኳት " ያሉኝ አጋዥ ያጡት የአንድ ትልቅ ደራሲ እናት ናቸው ። መስፍን ጌታቸው ( ነፍሱን ይማርና ) ከእርስዎ ጋር የብዙ ሚሊዮን ብር ስራ ተነጋግሮ ( ምናልባትም ተፈራርሞ ) ሞት ቀደመው ። አሁን የእሱ እናት ናቸው መጠጊያ ቤት አጥተው ችግር ላይ የወደቁት ።

ክብርት ከንቲባ ደራሲ መስፍን ጌታቸው የሀገርና የጥበብ ባለውለታ ፣ የብዙዎቻችን ወዳጅ ፣ ባለውለታና ለበርካታ ተዋንያን መታወቅና ዝና መጨመር ባለድርሻ ቢሆንም እኛ ሁላችን ወዳጅነቱን ክደናል ። ውለታውን በልተናል ። ( ለመዋጥ ቢመርም እውነታው ይህ ነው ) ለዚህ ነው ጉዳዩ እርስዎ ዘንድ የደረሰው ። የደራሲ መስፍን ጌታቸው እናት ድምጽ ለዓመት ከአምስት ወር ቢታፈንም አሁን ግን ይበቃል ። እባክዎ ክብርት ከንቲባ ሌላ ሳይሆን አንዲት ክፍል የቀበሌ ቤት እንኳ ይስጧቸውና ለእኚህ እናት እፎይታን ይስጡልን ። ሌላ ምንም ባያደርጉም በፀሎታቸው ሁሉ አይረሱዎትም ። እባክዎ ክብርትነትዎ ።

ለወዳጆቹና የስራዎቹ አድናቂዎቹ ፦

የደራሲው እናት " ዋና ጉዳዬ አንዲት አንገት ማስገቢያ ደሳሳ ጎጆ ናት " ይበሉ እንጂ እውነታው መከታቸው የነበረው ልጃቸውን በሞት ተነጥቀው ማንም ደጋፊ የላቸውም ። እስከዛሬ አውቀን ምንም ያላደረግን ወዳጆቹም እንሁን ምሥጢሩ ባለመውጣቱ ያላወቃችሁ ከስር ባለው የባንክ ቁጥር የቻልነውን እናድርግላቸው ። በስም ባይለዩዋችሉም ለሰጪዎቻቸው ሁሉ ይፀልዩላችኋል ። እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉን ያያል ።

ሎሚናት ገ/መስቀል ቢራቱ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000034499865

ስለ ፈጣሪ ብላችሁ ፦

1 - ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምትቀርቡ ሁሉ ይህን የተማጽኖ አቤቱታ አድርሱላቸው ።

2 - ብዙሀን መገናኛዎች ከግለሰቦች ሳይሆኑ ከእውነትና ከፍትሕ ጎን ቁሙ ።

3 - ይህን መልዕክት ያያችሁ ሁሉ ሼር ሳታደርጉ አትለፉ ። በእግዚአብሔር ስም።

#SHARE
• @ThinkAbyssinia •
8.5K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ