Get Mystery Box with random crypto!

Think Abyssinia

የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thinkabyssinia — Think Abyssinia
የሰርጥ አድራሻ: @thinkabyssinia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 157
የሰርጥ መግለጫ

➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @Contact_Thinkabyssinia

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-09-26 20:17:19
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከብሯል

በመላው የክርስት እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል።

መልካም የደመራ በዓል በድጋሚ
• @ThinkAbyssinia •
5.2K views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 18:26:26 #ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤በትግራይ በድሮን ጥቃት ፍንጣሪ ተሽከርካሪው መመታቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የድሮን ጥቃቱን ተከትሎ በተፈጠረ ፍንጣሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሠራተኛ በሆነው አሽከርካሪ ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በተሽከርካሪው ላይም ቀላል ጉዳት ማጋጠሙን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ተሽከርካሪው ጦርነቱን ተከትሎ በትግራይ ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች ምግብ እያደረሰ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።

2፤አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከተመድ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ።

ምክክሩም በክልሉ እየተከናወነ ያለው የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችና በክልሉ የሚኖሩ የአቅመ ደካማ ማህበረሰብ ክፍል ኑሮ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። የሁለቱ ወገኖች የስራ ኃላፊዎች በአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ምላሽ በሚሰጥበትና በክልሉ የሚገኙና ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ህይወትን በዘላቂነት የሚቀይርበት ሁኔታዎች ላይ ከመግባባት መደረሱም ነው የተገለጸው።

3፤ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ  "ሊድ" የተሰኘ የሶስት አመት አዲስ  የዕድገት ስትራቴጂ ይፋ አደረገ።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ አዲሱ ስትራቴጂ ከ2011 ጀምሮ እስከ ሰኔ 2014 ድረስ ሲያገለግል የነበረውን ብሪጅ የተሠኘው ስትራቴጂ  የተካ ነው ብለዋል። አዲሱ ሊድ የተሰኘው የኢትዮ ቴሌኮም የሶስት አመት ዕቅድ ስትራቴጂ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

4፤በኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ እየተስፋፋ መሆኑ ተነገረ።

ከአንድ ሳምንት በፊት በበሽታው የተያዘ ግለሰብ በተገኘባት ኡጋንዳ በኢቦላ እንደተያዙ የሚጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳለው አስካሁን 34 በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ ሲገልጽ፣ 21 ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መሞታቸውን ገልጿል። ኡጋንዳ የኢቦላ ወረርሽኝ ሲያጋጥማት ይህ ለአራተኛው ጊዜ ነው።

5፤የኬንያው ፕሬዝደንት የድርቅ ተጽእኖን ለመቋቋም ግብረኃይል እንዲቋቋም አዘዙ።

በቅርብ የተመረጡት የኬንያወ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ድርቅ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችል ግብረኃይል እንዲያቋቁም ለምክትላቸው ትእዛት ሰጥተዋል፡ ዊሊያም ሩቶ ይህን ያሉት ምርጫ ማሸነፋቸውን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የምስጋና መርሃግብር ላይ ነው፡፡ በኬንያ ከ36 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በድርቅ ተጠቅተዋል

6፤ኢትዮጵያና ሱዳን በወዳጅነት ጨዋታ አቻ ተለያዩ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአቋም መለኪያ ጨዋታ ከሱዳን ጋር ዛሬ ከቀኑ 10:00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጫውቶ ሁለት አቻ ተለያይቷል። ለዋልያዎቹ ሁለቱን ጎሎች ዳዋ ሆቴሳና ቸርነት ጉግሳ አስቆጥረዋል።

መልካም የደመራ በዓል
• @ThinkAbyssinia •
6.3K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 16:47:30
ኢትዮጵያውያኑ ሰዓልያን በጀርመን በተካሄደ የስዕል ውድድር አሸነፉ

በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስነ ጥበብ ትምህርት ክፍል ሠልጣኝ የሆኑት  ፍሬወይኒ እንድሪያስ እና ኢዮብ እሸቱ በጀርመን ሌፕዥግ ከተማ በተካሄደ የስዕል ውድድር ላይ አንደኛና ሁለተኛ ደረጀን ይዘው ማሸነፋቸውን የአዲስ አበባ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ የሆነው ኪነ ቅርፅም የአዲስ አበባ እህት ከተማ በሆነችው የጀርመኗ ሌፕዥግ ከተማ በሚገኘው የአዲስ አበባ አደባባይ ተብሎ በተሰየመው ቦታ ላይ የሚተከል ይሆናል ነው የተባለው።

መልካም ደመራ በዓል

• @ThinkAbyssinia •
2.2K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 15:05:18
የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በምስል

መልካም በዓል

• @ThinkAbyssinia •
4.0K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 13:49:20
እንኳን ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በዓል

• @ThinkAbyssinia •
4.9K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 12:18:48
የአለም ትልቁ ፊት በኢትዮጵያ ተገኝቷል

በዳውሮ ዞን የማረቃ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አባይነህ አበራ የአለም ትልቁ ፊት ባለቤት ተብለዋል። አቶ አባይነህ አበራ 25 ሴ.ሜ የሚረዝም ፊታቸው የአለም ትልቁ ወይም ረዥሙ ፊት ነው ተብሎ በአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍሯል።

በዚህም ምክንያት የአፍሪካን ትልቁና ረዥሙ ፊት በሚል የአፍሪካ የድንቃድንቆችን ክብረወሰን በመስበር የክብር የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡አቶ አባነህ በዳውሮ ዞን የማረቃ ወረዳ ነዋሪ ስሆን በንግድና በእርሻ ስራ የሚተዳደር ነው።

• @ThinkAbyssinia •
6.0K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 11:10:48
ከሰሃራ በታች ዝቅተኛ ኢንተርኔት ዋጋ የሚያስከፍሉ ሀገራት

አለም አቀፍ የሞባይል ዳታ ዋጋ ላይ በተደረገ ጥናት በፈረንጆቹ በ2022 በጣም ርካሹን እና በጣም ውድ የሆነውን የሞባይል ዳታ የሚያቀርቡ ሀገራት ዝርዝር ይፋ ሲሆን 5 ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ ከሚያቅርቡ 50 የዓለም ሀገራ ውስጥ መካተት መቻላቸው ተመላክቷለል።

ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ የሚያቀርቡ 5 ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት

. ጋና 1 ጊጋ ባይት የኢንትርኔት ዳታ በ0.61 ዶላር
. ሶማሊያ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.63 ዶላር
. ናይጄሪያ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.71 ዶላር
. ታንዛኒያ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.71 ዶላር
. ሱዳን 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.75 ዶላር

ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተች ሲሆን፤ ደረጃዋም ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት መካከል ኢንተርኔትን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ 10ኛ ከዓለም ደግሞ 73ኛ ላይ ተቀምጣለች። በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ የ 1 ጊጋ ባይት የኢትነርኔት ዳታ ዋጋ 1 የአሜሪካ ዶላር ወይም 52 ብር ገደማ እንደሆነ መሆኑን አልዐይን ፅፏል።

• @ThinkAbyssinia •
6.3K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 11:10:23
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን  እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ዪፈልጋሉ ፤ እንግዲያውንስ ይሄን ሊንክ ይጫኑ፡፡ከላይ ያሉትን የጫማዎች ዋጋ እና ብዙ አማራጮችን ለማግኘት  ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ


https://t.me/joinchat/AAAAAElITjwlFLHHO8h7Sg


ይዘዙ በውስጥ መስመር የመረጡትን ፎቶ  ይላኩልን በቀላሉ እናስተናግዳለን ግዜዎን ቆጥበን።
inbox 1         inbox2
    @businesslidu   @businesslidu2

online shopping is always a good idea!!
አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ መ/ም ኤድናሞል አደባባይ ዞሮ ሬድዋን ህንጻ ጎን ራክሲም ህንጻ 3ኛ ፎቅ በስተቀኝ ዞር ሲሉ ያገኙናል።

0919998383
በውስጥ መስመር ለመፃፍ    @businesslidu & @businesslidu2
5.7K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 10:29:10 #ቲንክአቢሲኒያ_የቡናቁርስ_መረጃዎች

1፤በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ሃይል ላይ ያተኮረ የትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ “ጤናማ ትራንስፖርትን ማበረታታት” በሚል መሪ ሃሳብ ምክክር እየተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስተሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት በኤሌክትሪክ ሃይል ላይ ያተኮረ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

2፤ሦስተኛ ዙር ጦርነት ባለበት አካባቢ የምግብ ፍጆታ ዋጋ በ4 እጥፍ መጨመሩ ተሰማ።

በሰሜኑ ጦርነት ቀጠና ውስጥ ባሉ ቦታዎች የተለያዩ የምግብ ፍጆታዎች ዋጋ ከነበረበት በአራት እጥፍ በላይ መጨመሩን አዲስ ማለዳ ዘግባለች። በሦስተኛው ዙር ጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚገኙት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር በኩል እና በራያ ቆቦ ወረዳ ግራና ቀኝ እንዲሁም በአፋር ክልል በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ሲሆኑ በተለይም በራያ ቆቦ ከተማ ሦስተኛው ዙር ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የነበረው የምግብ ፍጆታ ዋጋ አሁን እስከ አራት እጥፍ ጨምሯል ተብሏል።

3፤አዲሱ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር በአዲስ አበባ ተመሰረተ። 

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ለማኅበሩ ዕውቅና መስጠቱን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሙያ ማኅበሩ ማኅበሩ የተመሠረተው፣ የጤና ሙያን ለማሳደግ፣ በጤናው እና በሙያው ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማስተካከል ረገድ እገዛ ለማድረግ፣ የጤና ሙያተኞችን መብቶችና ጥቅሞች ለማስከበር እና በረጅም ጊዜ የጤና ነክ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለመንግሥት ለማቅረብ እንደሆነ ተገልጧል።

4፤ኬንያ ከሩሲያ ነዳጅ ለመግዛት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች።

የአሜሪካ ዲፕሎማት፤ የአፍሪካ ሃገራት ከስንዴ እና ማዳበሪያ ውጭ ከሩሲያ ምንም ነገር እንዳይገዙ ባስጠነቀቁበት በዚህ ሰአት የኬንያው ፐሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ሀገራቸው ከሩሲያ ነዳጅ ለመግዛተ ፍላጎት እንዳላት እና ለዚህም ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ግን ሀገራቸው ያሉትን አማራጮች ሁሉ እያጤነች ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

5፤ጣሊያን የመጀመሪያዋን ሴት ጠ/ሚ ለመሾም ተቃርባለች ተባለ።

የቀኝ አክራሪው መሪ ጆርጂያ ሜሎኒ በጣሊያን ምርጫ ለማሸነፍ መቃረባቸው መገለፁን ተከትሎ የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። ሜሎኒ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኃላ የጣሊያን ቀኝ ክንፍ መንግሥት እንደሚመሰርቱ ከወዲሁ በሰፊው እየተጠበቁ ይገኛል። ጣሊያን የአውሮፓ ህብረት ሶስተኛዋ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ስትሆን የቀኝ ዘመሟ ሜሎኒ ድል ለአብዛኛው የአውሮጳ ህብረት ስጋት ፈጥሯል።

6፤ኢትዮጵያና ሱዳን የወዳጅነት ጨዋታቸውን ዛሬ ያካሂዳሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአቋም መለኪያ ከሱዳን ጋር ዛሬ ከቀኑ 10:00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳስ ቤተሰቡ በስፍራው በነፃ በመታደም ብሔራዊ ቡድናችንን እንዲያበረታቱ ጥሪውን አቅርቦዋል።

• @ThinkAbyssinia •
5.4K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 10:27:03
ኪያድ ዳቦ እና ኬክ
Kiyad Bakery and Coffee

ለልደት፣ ለሰርግ እና ለምርቃት በፈለጉት ዲዛይን እና መጠን እናዘጋጃለን።

Bring us your cake designs! We prepare cakes for every occasion!

0911467026
0913911679

የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ

https://t.me/kiyad_bakery

አድራሻ: ልደታ ፍሊንት ስቶን አካባቢ
      የልደታ የፍታብሔር ምድብ ችሎት ፊት ለፊት

https://maps.app.goo.gl/4hYtermcawkxksDH7
5.3K viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ